ይህ ስትራቴጂ ከሐምሌ 2013 እስከ ሰኔ 2016 ያለውን ጊዜ የሚሸፍን ሲሆን ዓመታዊ እቅዱ ከሐምሌ 2013 እስከ ሰኔ 2014 ያለውን ጊዜ ይሸፍናል፡፡
ኩባንያችን ላለፉት 127 ዓመታት የቴሌኮም አገልግሎት በመስጠት በሀገራችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ እድገት እንዲሁም በዜጎች ኑሮ መሻሻል ላይ ከፍተኛ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል፡፡ የቴሌኮም ዘርፍ ለውድድር ክፍት እንዲደረግ መንግስት የወሰደውን የፖሊሲ ለውጥ ያገናዘበና ብቁ፣ ተወዳዳሪ እና ተመራጭ የቴሌኮም አገልግሎት ሰጭ ተቋም ሆኖ ለመቀጠል የሚያስችለንን የሦስት ዓመት የእድገት ስትራቴጂ ቀርጸን ወደ ተግባር መግባታችን ይታወሳል፡፡ ይህ አዲሱ በጀት ዓመት የስትራቴጂ ዘመኑ ሦስተኛ ዓመት ሲሆን ስትራቴጂው ወቅታዊ ሁኔታን ከግምት ያስገባ እና ማሻሻያዎችን በማድረግ የተዘጋጀ ነው፡፡
የቴሌኮም ዘርፍ በፍጥነት እያደገና ተለዋዋጭ በመሆኑ ከወቅቱ ጋር በፍጥነት የሚራመድ ተቋም የመሆን ትልም በመንደፍ ይህ ዕቅድ ቋሚ (Static) ሳይሆን በየወቅቱ በኢንዱስትሪው ላይ የሚታዩ እድገትና ለውጦች እንዲሁም ከውድድርና የባለቤትነት ድርሻ ከማስተላለፍ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችንና የሀገራችን ነባራዊ ሁኔታዎችን ታሳቢ በማድረግ ‘deliberate’ እና ‘emergent strategy approach’ በመከተል የተዘጋጀ ሲሆን ታሳቢ የተደረጉ ጉዳዮች ሲለወጡ በድጋሚ ታይቶ እቅዱ በለውጡ መሰረት የሚሻሻል ይሆናል፡፡
ስትራቴጂው ሲዘጋጅ የኩባንያችንን ተወዳዳሪነት እና አስተማማኝ እድገት ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ ተቋሙ ላይ ፍላጎትና ተጽዕኖ ሊኖራቸው የሚችሉ የመንግስት የፖሊሲ ሰነዶችን፣ የውስጥና የውጭ ባለድርሻ አካላት ፍላጎትና ተጽዕኖ (የደንበኞች፣ የሠራተኞች፣ የተቆጣጣሪ አካላት፣ የቴክኖሎጂ አቅራቢዎችና የተለያዩ የመንግስት አካላት እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት) በተጨማሪም በቴሌኮም ዘርፍ የተሰማሩ ሌሎች ተቋማት ያላቸውን የገበያ እንቅስቃሴና ልምድ፣ የቴሌኮም ኢንዱስትሪ እድገት ዋና ዋና አዝማሚያዎችና የዓለም አቀፍ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመተንተን፣ የተወዳዳሪ ኩባንያዎችን ስትራቴጂዎች እንዲሁም የኩባንያችን ውስጣዊ ጥንካሬና ውስንነቶችን በመለየት፣ ውጫዊ መልካም አጋጣሚዎችና ስጋቶችን በመለየትና በመተንተን የተቋሙን ተጨባጭ አቅምና ለተወዳዳሪነት የሚያበቃውን ተግባራት በመቃኘት የተዘጋጀ እቅድ ነው፡፡
የሦስት ዓመት ስትራቴጂውና የ2014 በጀት ዓመት ቢዝነስ እቅድ በማኔጅመንቱና በሰራተኞቹ ሰፊ ውይይት ተካሂዶ ግብዓት ከተወሰደ በኋላ በማኔጅመንቱና በስራ አመራር ቦርዱ የጸደቀ ሲሆን ከዚህ ጎን ለጎን የበጀት ዓመቱ እቅድ ማስፈጸሚያ በጀት የተዘጋጀ ሲሆን ስትራቴጂውን ለትግበራ ዝግጁ ከማድረግ አኳያ በሥራ ክፍሎች መካከል ተገቢውን ትስስርና መንሰላሰል በመፍጠርና ካስኬድ በማድረግ ከበጀት ዓመቱ መጀመሪያ ወር (ሐምሌ 2013) አንስቶ ሥራ ላይ ውሏል፡፡
ስትራቴጂው በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ የመጣውን የደንበኛ ፍላጎትን ለማርካት፣ የቴሌኮም ስርጸትን በማሳደግ የዲጂታል ኢኮኖሚን ለመደገፍና አጠቃላይ የሀገሪቱን ምርታማነት ለማሳደግ እንዲሁም የተቋሙን የገቢ ምንጭ ከተለመደው መሠረታዊ የቴሌኮም አገልግሎቶች ወደ ዳታና የይዘት አገልግሎቶች (Contents and Value Added Services) ትኩረት በማድረግ፣ የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት ላይ አዳዲስ አገልግሎቶችን በመጨመር እና አዳዲስ የስራ መስኮችን በማስጀመር በሁሉም ዘርፍ ዝግጅት በማድረግና ያሉትን መልካም ተሞክሮዎች በማጠናከር የተቋሙን ቀጣይነትና እድገት አስተማማኝ ለማድረግ ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡
የኩባንያችን ህልውና የሆኑትን ደንበኞቹን ለማርካትና ለማቆየት የሚያስችሉ ልዩ ልዩ የአገልግሎት አማራጮችን ከቅናሽ ጋር በማቅረብ የመረጡትን የአገልግሎት አይነት መጠቀም እንዲችሉ የማድረግ (Empowering customers)፣ ተጨማሪ የሽያጭ ማዕከሎችን በመክፈት እና የ24/7 አገልግሎትን በማስጀመር ተደራሽነትን የማሳደግ፣ የድህረ-ሽያጭ አገልግሎቶችን በማሻሻል ደንበኞቻችን የተሻለ ተሞክሮ እንዲኖራቸው የማስቻል፣ እንዲሁም የደንበኝነት ፕሮግራሞችን (loyalty program) በመቅረጽ የደንበኞችን እርካታ ለማሳደግ የሚያስችሉ ስራዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የደንበኞቻችንን ፍላጎት ለማርካት ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለንን አጋርነት አጠናክሮ በመቀጠል፣ የኔትወርክ እና የሲስተም ማስፋፊያ ፕሮጀክቶችን በማከናወን፣ እንዲሁም የደንበኛ መገልገያ መሳሪያዎች በቅናሽ ዋጋ እና በተራዘመ ጊዜ የክፍያ አማራጮች (installment plan) በመጠቀም ልዩ ልዩ አማራጮችን ለገበያ በማቅረብ የደንበኛን ተሞክሮ የማሻሻል ስራዎች ለማከናወን ታቅዷል፡፡
የሰው ኃይል ከማልማት አንጻር የኢንዱስትሪውን በፈጣን ሁኔታ ማደግና ተለዋዋጭነትን በሚገባ የሚገነዘብ፣ ከእድገቱ የሚገኙ ትሩፋቶችንና መልካም አጋጣሚዎችን በአግባቡ የሚጠቀም እንዲሁም ከኢንዱስትሪው ባህሪ ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ ፈታኝ ሁኔታዎችንና መጭውን የውድድር ገበያ በበቂ ዝግጅትና በጥንቃቄ ለመምራት የሚያስችል እውቀትና ክህሎት ያለው የሰው ኃይል መገንባት የስትራቴጂው ዋነኛው የትኩረት አቅጣጫ ነው፡፡
የኩባንያችንን ስትራቴጂ በተባበረ ጥረት እውን ለማድረግ በኢንዱስትሪው ላይ ያሉ ባለድርሻ አካላት ጋር በተለይም የቴክኖሎጂ መሳሪያ አቅራቢዎች፣ ከኩባንያችን ምርት አከፋፋይ አጋሮች፣ የይዘት አገልግሎት አቅራቢዎችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት የሚደረግበት ይሆናል፡፡ ይህም ምርትና አገልግሎቶቻችንን ወደ ገበያ የምናቀርብበትን ጊዜ የሚያሳጥርና የደንበኞቻችንን እርካታ ለማረጋገጥ የምናደርገውን ጥረት የሚደግፍ ከመሆኑም ባሻገር በውድድር ገበያው በባለድርሻ አካላትና በአጋሮቻችንም ጭምር ተመራጭ ኩባንያ ለመሆን የሚያስችል እና ተጨማሪ ግብዓቶችን በማግኘት የተሻለ አጋርነት የሚፈጠርበት ይሆናል፡፡
የውድድር ገበያውን በብቃት ለመወጣት በተለዩት ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮች ማለትም ምርጥ የደንበኛ ተሞክሮን ማረጋገጥ፣ ጠንካራ የፋይናንስ አቅም መፍጠር፣ የአገልግሎትና የቴክኖሎጂ ልህቀት ማረጋገጥ፣ ሰው ተኮርና የሚማር ተቋም መገንባት፣ የኦፕሬሽን ልህቀት እና ተቋማዊ ገጽታ ግንባታ ሥራዎች ኩባንያው ዕውን ለማድረግ ያለውን የሰው ኃይል፣ እውቀትና ሀብት በአግባቡ በመምራት በደንበኞቹ፣ በአጋሮቹና በባለድርሻ አካላት ተመራጭ ኩባንያ ለመሆን የምንንቀሳቀስ ይሆናል፡፡
በ2014 በጀት ዓመት ለማከናወን የታቀዱ ዋና ዋና ግቦች
የአገልግሎት ጥራትን፣ ተደራሽነትን እና የደንበኞች ተሞክሮን ለማሻሻል የሚያስችል የኔትወርክና የሲስተም አቅም ማሳደጊያ ፕሮጀክቶች እንዲሁም አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች በበጀት አመቱ የሚተገበሩ ይሆናል፡፡ በዚህም የዳታ ትራፊክ እድገትን መሠረት ያደረገ የ4G/LTE እና የ4G/LTE Advanced አገልግሎት ማስፋፊያ ሥራዎችን በቀሪ የክልል ዋና ዋና ከተሞች ይከናወናል፡፡ በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ 3.88 ሚሊዮን ተጨማሪ ደንበኞችን ማስተናገድ የሚችል የሞባይል ኔትወርክ አቅም፣ የ5G ሞባይል ቴክኖሎጂ ሙከራ፣ የሞባይልና የመደበኛ ብሮድባንድ አገልግሎት ለማስፋፋት የሚያስችሉ መሠረተ ልማቶች ግንባታ፣ የኦፕሬሽንስ ሰፖርት እና የኮርፖሬት ሶልዩሽንስ ፕሮጀክቶች እንዲሁም አዳዲስ አገልግሎቶችን ለመስጠት የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች እና የተለያዩ የሲቪል ግንባታ ፕሮጀክቶችን ለመተግበር እቅድ ተይዟል፡፡
በ2014 በጀት ዓመት የደንበኛ ብዛትን በ14% በመጨመር 64 ሚሊዮን ለማድረስ የታቀደ ሲሆን በሞባይል 13% በመጨመር 61.37 ሚሊዮን፣ የሞባይል ዳታና ኢንተርኔት ተጠቃሚ በ16.2% በመጨመር 28.5 ሚሊዮን፣ የፊክስድ ብሮድባንድ ደንበኛ በ48% በመጨመር 554 ሺህ በማድረስ አጠቃላይ የቴሌኮም ስርጸት መጠንን 61% ለማድረስ ታቅዷል፡፡
ገቢን ከማሳደግ አኳያ ከተለመደው የቴሌኮም የገቢ ምንጮች በተጨማሪ ሌሎች እሴት የሚጨምሩ አገልግሎቶችን በመጨመር፣ ከ100 በላይ አዳዲስ እና የተሻሻሉ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ አገልግሎቶችን ለገበያ በማቅረብ፣ የአገልግሎት አሰጣጡን በማሻሻል እና የደንበኛ እርካታን፣ ቆይታንና ታማኝነትን በማሳደግ የ2014 በጀት ዓመት አጠቃላይ የገቢ መጠንን በ24 በመቶ በማሳደግ 70 ቢሊዮን ብር ለማድረስ ታቅዷል፡፡
የኩባንያችንን ስትራቴጂ በታቀደው መሠረት በመተግበር የኦፕሬሽን ልህቀትን በማምጣትና የአገልግሎት ጥራትን በማረጋገጥ፤ የደንበኛ እርካታን ለማሳደግ የሠራተኛውን የመፈጸም አቅም በማሳደግና በማሳተፍ፣ የሠራተኛውንና የኩባንያችንን ዓላማ በማስተሳሰርና በማጣጣም እንሰራለን፡፡ ስትራቴጂው ስድስት የትኩረት መስኮችን በ17 ስትራቴጂካዊ ግቦችና በርካታ ስትራቴጂካዊ እርምጃዎችን (Strategic Initiatives) በመቅረጽ ተግባራዊ ለማድረግ የታቀደ ሲሆን የኮርፖሬት ስትራቴጂካዊ ግቦች ተገቢውን መለኪያና ዒላማ ተዘጋጅቶላቸው ወደ የሥራ ክፍሎች ካስኬድ በማድረግ ትግበራ ተጀምሯል፡፡ የኩባንያችንን ቀጣይነት ያለው እድገት ከማረጋገጥ ባሻገር በሀገራችን ሁለንተናዊ ለውጥና እድገት ላይ ያለንን ሚና የበለጠ እናሳድጋለን፡፡
ኩባንያችን በበጀት ዓመቱ የዘርፉ ሪፎርም ላይ ያለውን ተሳትፎ በማሳደግ፣ ለውጡን ተከትለው የሚመጡ ፈታኝ ሁኔታዎችን በብቃት በመወጣት በ2014 በጀት ዓመት በእቅድ የያዝናቸውን ሰፊ የፕሮጀክትና የኦፕሬሽን ግቦችን በሙሉ ስኬት ለማጠናቀቅ ዝግጁና ቁርጠኛ መሆኑን እየገለጽን የኩባንያችን የሥራ አጋሮችና ባለድርሻ አካላት ለያዝናቸው መጠነ ሰፊ የለውጥና የእድገት ውጥኖች መሳካት የበኩላችሁን ሚና እንድትወጡ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
13 ቀን ነሐሴ 2013
ኢትዮ ቴሌኮም
This strategy covers a time period from 1 July 2021 to 30 June 2024 and a business plan from 1 July 2021 to 30 June 2022.
Ethio telecom, as an enabler for the socio-economic development of the nation, has been serving Ethiopia for the last 127 years. It is recalled that Ethio telecom management took the initiative to develop a three- year strategic plan to meet the market dynamism, reshaping and leading the company with a competitive mindset with the ultimate aim of making the company a Preferred Operator. As this budget year is the third year of the strategic plan, the strategy is enhanced and enriched taking the current conditions and new developments into account.
Ethio telecom follows rolling strategy with deliberate and emergent strategy development approaches to accommodate a changing reality, considering the nature of the business and the ongoing market conditions. To ensure competitiveness and sustainable growth of the company, this strategy has been developed by considering and reviewing relevant government policies, international best practices, and Industry trends. Various important analyses have also been made such as internal and external stakeholders’ interests and expectations (Customers, Employees, Vendors/suppliers and various government organs), past company performances, internal strengths, organizational resources and capacities, and weaknesses, opportunities and threats in the outer environment and the market dynamics.
The three-year strategy and the 2021/22 business plan have been reviewed at senior and middle management levels, consulted, and validated by Ethio telecom Board of Directors. Following validation, communication, cascading, and alignment of the strategy have been conducted to improve strategy execution among stakeholders.
The strategy addresses ever changing customer demand, digital inclusion to create better digital economy, financial inclusion, enhance productivity, shift the revenue from traditional revenue streams to value added and content driven services by introducing new business streams and solutions including mobile financial services.
To boost customer’s satisfaction and ensure customer loyalty, we are working on creating easy customer journey by simplifying offers, availing multiple products and services, empowering our customers, enhancing after sales services and introducing loyalty programs.
In addition, we are working on improving our services accessibility, facilitating digital channels, engaging more partners, opening additional shops and commencing 24/7 services in some selected areas. We are also working on affordability by offering discounted package offers, subsidized and installment based handsets, availing credit services, and providing free EPON to GPON swap etc.
The strategy will also continue to focus on the most important company asset – employees, to equip them with relevant knowledge and develop high performance culture, with skill that will enable them to grasp and catch up with the telecom industry dynamism, to exploit opportunities arising from development of the industry and cope with the challenges.
Telecom business needs collaboration and concerted efforts of all players in the ecosystem, to this end, the strategy will be discussed with partners including vendors and distributors, content providers and other stakeholders. This will further enhance strategy execution, shortening of TTM, meet customer demands by adopting new solutions and insights.
Major Business Plan Objectives and Targets in 2014 EFY (July 2021 – June 2022)
In the new budget year, we will deploy various projects to expand network and systems capacity, new technologies and additional new features so as to enhance customer experience, quality of services, service accessibility and to cater unserved demands of our customers. Accordingly, 4G/LTE Advanced network capacity expansion will be carried out in Addis Ababa and in regional towns following data traffic growth and demand. To improve network coverage and capacity, more than 3.88 Million additional Mobile network capacity will be installed in Addis Ababa and Regions. Furthermore, new operations support system and corporate solutions projects that improve service provisioning, automation, operational efficiency will be deployed. 5G mobile technology will be introduced as a pilot.
Ethio telecom has also planned to increase total subscribers by 14% to 64M, Mobile Voice subscribers by 13% to 61.37 M, Data and Internet users by 16.2% to 28.5M, Fixed broadband subscribers by 48% to 554K. This is expected to bring telecom penetration to 61%.
By engaging in new business streams and shifting revenue source from traditional to value-added services and by offering more than 100 new and revamped local and international products & services, Ethio telecom aims to generate 70 B Birr revenue, an increment of 24%.
With enhanced employee engagement, empowerment, skill development and goal alignment, Ethio telecom aspires and works to become a Preferred Operator by its customers, partners and stakeholders. On this occasion, we would like to respectfully call upon all partners and stakeholders to join hands in realizing our company’s strategic objectives and initiatives.
19 Agust 2021
Ethio telecom