ስለ መጭበርበር ግንዛቤ ማጭበርበር ምንድን ነው? ሆን ተብሎ የሚፈፀም የማታለል ድርጊት ሲሆን አጭበርባሪው ህገ ወጥ ጥቅም እንዲያገኝ ወይም የተጎጂውን መብት ለመንፈግ የሚደረግ ተግባር ነው፡፡ በብዛት የሚፈፀሙ የማጭበርበር አይነቶች የትኞቹ ናቸው ማህበራዊ ምህንድስና (Social engineering) ፡ በዚህ ዘዴ አጭበርባሪዎች ያልሆኑትን ማንነት በመላበስ (ተቋማትን ወይም ሌሎች ግለሰቦችን በመምሰል) ሚስጥራዊ ቀጣዩን ለማንበብ የማጭበርበር ድርጊቶችን ለመከላከል መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች ምንድን ናቸው? ሲም በመለወጥ የሚደረግን ማጭበርበር ለመከላከል... ሲም ካርድዎ የይለፍ ቃል ስለመኖሩ ያረጋግጡጠንካራ የይለፍ ቃል በመጠቀም እና የግል መረጃዎችን በቀላሉ እንዳይገኙ ማድረግ በተለይም ከማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ አያስቀምጡየይለፍ ቃልዎን ወይም የሚስጥር ቁጥርዎን ለሌላ ሰው አለማጋራትየግል መረጃዎን ለማንም ሰው አለማጋራት በተለይም የአንድ ጊዜ የይለፍ ቁጥርዎን፣ የማይ ኢትዮቴል ወይም ቴሌ ብር አካውንቶችዎን የመሳሰሉበስህተት ጥቅል ልከንለዎታል እባከዎት መልሰው ይላኩ ለሚሉ መልእክቶች ምላሻ አለመስጠትከማያውቁት ሰው ከቴሌብር አካውንትዎ ላይ ገንዘብ ወይም የአየር ሰዓት ያስተላልፉልኝ ጥያቄ ምላሽ አለመስጠት የአጭበርባሪዎች ዒላማ የትኞቹ አገልግሎቶች ናቸው? የቴሌብር አካውንትየሞባይል ባንኪንግ ዋሌትየቅድመ ክፍያ ክሬዲትዓለም አቀፍ እና ልዩ አጭር ቁጥር ጥሪየማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችማንነትን በመጥለፍ የሚሰልሉ ማጭበርበርን እንዴት መጠቆም ይችላሉ የማጭበርበሪያ መልዕክቶች ሲደርስዎ ወይም ሲጠራጠሩ 994 ወይም 127 ላይ በመደወል እንዲሁም ወደ 9090 አጭር መልዕክት በመላክ ማሳወቅ ይችላሉ፡፡በተጨማሪም በሁሉም የኢትዮ ቴሌኮም የማህበራዊ ድረ-ገፆች አማካኝነት ጥቆማዎን ማድረስ ይችላሉ፡፡