ከ 39% ልዩ ቅናሽ ጋር
አስተማማኝ የመጠባበቂያ ኤሌክትሪክ ኃይል
የላቀ የመጠባበቂያ ኃይል አቅርቦት አማራጮች
5 ኪሎ ዋት 560,000 ብር | 10 ኪሎ ዋት 850,000 ብር | 15 ኪሎ ዋት 1,142,000ብር |
---|---|---|
1 ኢንቨርተር 1 ፓወር ሞጁል 1 ባትሪ ሞጁል 1 የመጠባበቂያ ሳጥን 1 ሜትር 1 4ጂ ዶንግል |
1 ኢንቨርተር 1 ፓወር ሞጁል 2 ባትሪ ሞጁል 1 የመጠባበቂያ ሳጥን 1 ሜትር 1 4ጂ ዶንግል |
1 ኢንቨርተር 1 ፓወር ሞጁል 3 ባትሪ ሞጁል 1 የመጠባበቂያ ሳጥን 1 ሜትር 1 4ጂ ዶንግል |
20 ኪሎ ዋት 1,525,000 ብር | 25 ኪሎ ዋት 1,820,000 ብር | 30 ኪሎ ዋት 2,110,000 ብር |
1 ኢንቨርተር 2 ፓወር ሞጁል 4 ባትሪ ሞጁል 1 የመጠባበቂያ ሳጥን 1 ሜትር 1 4ጂ ዶንግል |
1 ኢንቨርተር 2 ፓወር ሞጁል 5 ባትሪ ሞጁል 1 የመጠባበቂያ ሳጥን 1 ሜትር 1 4ጂ ዶንግል |
1 ኢንቨርተር 2 ፓወር ሞጁል 6 ባትሪ ሞጁል 1 የመጠባበቂያ ሳጥን 1 ሜትር 1 4ጂ ዶንግል |
ማስታወሻ
- ተጨማሪ መለዋወጫዎች ማለትም ኢንቨርተር፣ ፓወር ሞጁል፣ ባካፕ ሞጁል፣ መጠባበቂያ ሳጥን፣ እና የላቀ ኃይል ማከማቻ (Intelligent electric quantity collector) በመግዛት ለተጨማሪ ሰዓታት የሚሆን በቂ ኃይል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ደንበኞች ክፍያውን በአንድ ጊዜ ወይም በ12 ወራት በተራዘመ ክፍያ መፈፀም ይችላሉ፡፡
ደንብና ሁኔታዎች
- ለአገልግሎቱ በሲንግል ፌዝ (220 V) የቀረበ ሲሆን ደንበኞች ቸርችል ጎዳና ሊሴ ገብረማሪያም ት/ቤት የሚገኘውን ፕሪሚየም የድርጅት አገልግሎት መስጫ ማዕከላችን በመምጣት አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡፡
- 4ጂ ዳታ ብቻ የሚያስጠቅም የቅድመ ክፍያ ሲም ካርድ ከወርሃዊ 1 ጊ.ባ ዳታ ጋር ለ10 ዓመት ይቀርብላቸዋል፡፡ ሲም ካርዱን ቢጠፋ ደግመው ሲያወጡ የሚከፈለው አገልግሎት ክፍያ በደንበኞች የሚሸፈን ይሆናል፡፡
- የተራዘመ የመጠቀሚያ ጊዜ ከፈለጉ የባትሪ ኃይል መቆጣጠሪያ ሞጁል ብቻውን መግዛት ይችላሉ፡፡ ሽያጩ የሚፈቀደው ሙሉ የኃይል አቅርቦቱን ከዚህ በፊት ገዝተው ለነበሩ ደንበኞች ብቻ ነው፡፡
- ደንበኞች የሚጠቀሙት የኃይል አቅርቦት መጠን ማሻሻል ከፈለጉ በቅድሚያ በእኛ ባለሞያዎች በኩል አስፈላጊው ጥናት ተደርጎላቸው ማሳደግ የሚችሉት መጠን እንዲያውቁት መደረግ አለበት፡፡
- የኢትዮ ቴሌኮም በኩል የቀረቡ መገልገያዎችን ለመቀየር ከዚህ በታች በተጠቀሱት የመቀየሪያ/የጥገና የዋስትና ጊዜ ውስጥ ብቻ ይሆናል፡፡
- ኢንቨርተር- ለ10 ዓመት
- መጠባበቂያ ሳጥን፣ ፓወር እና ባትሪ ሞጁል-ለ5 ዓመት
- 4ጂ ዶንግል እና የላቀ ኃይል ማከማቻ (Intelligent electric quantity collector)--ለ1 ዓመት
- መገልገያዎቹ በደንበኛ የአያያዝ ጉድለት፣ በአጠቃቀም ችግር እና ሆን ተብሎ የተፈጠረ ከሆነ በዋስትና የማይስተናገድ ይሆናል፡፡
- ኢትዮ ቴሌኮም የዝርጋታ እና ከሽያጭ በኋላ ያሉ አገልግሎቶችን ማለትም ጉድለት ያለባቸውን ዕቃዎች ከደንበኛው ቦታ የማንሳት እና የመግጠም ስራ በዋስትና ቀነ ገደብ ውስጥ በነፃ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
- አንድ ጊዜ ገጠማው ከተጠናቀቀ በኋላ ደንበኞች የቦታ ለውጥ ማድረግ ቢፈልጉ ኢትዮ ቴሌኮም ኃላፊነቱን አይወስድም፡፡
ለተጨማሪ መረጃ የድርጅት አገልግሎት መስጫ ማዕከሎቻችንን ይጎብኙ!