አስደሳች ዜና ለቴሌብር ወኪሎች!

ለቴሌብር ወኪሎቻችን እስከ 250 ሺህ ብር የሚያሸልም ለ3ወር የሚቆይ የግብይት ማነቃቂያ ፕሮግራም ማስጀመሩን በደስታ እንገልጻለን

በየወሩ ለ229 ከፍተኛ የግብይት መጠን ለሚያስመዘግቡ እና በዕጣ ለሚለዩ 114 ወኪሎች የ10 ሺህ ብር ሽልማት፤
እንዲሁም በቀጣዮቹ 3 ወራት መጨረሻ በሃገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የግብይት መጠን ለሚያስመዘግቡ 3 ወኪሎች 
ለ1ኛ 250 ሺህ ብር፣
ለ2ኛ 150 ሺህ ብር እና
ለ3ኛ 100 ሺህ ብር ሽልማት አዘጋጅቷል።
የቴሌብር ግብይትዎን  ያሳድጉ፤ ይሸለሙ!

                የሽልማቱ መስፈርቶች

  • በየወሩ ከ30 ጊዜ በላይ ግብይትና እና ከ30 ሺህ ብር በላይ የገንዘብ መጠን መገበያየት፡፡
  • በየወሩ የሚሰጠው ሽልማት በኢትዮ ቴሌኮም ዞኖችና ሪጅኖች በተቀመጠው ኮታ መሰረት ሆኖ ወኪሎች የሚወዳድሩት በሚገኙበት የኢትዮ ቴሌኮም ዞን እና ሪጅን ከሚገኙ ወኪሎች ጋር ብቻ ይሆናል፡፡
  • የግብይቱ መጠን 50% ከኤሌክትሮኒክስ ገንዘብ ገቢና ወጪ አገልግሎት እንዲሁም ቀሪው 50% ከሌሎች አገልግሎቶች ማለትም የአየር ሰዓት፣ የጥቅል ሽያጭ፣ የቢል ክፍያ እና ሌሎችም የሚሰላ ይሆናል፡፡

በግብይት ማጭበርብር ድርጊት ተሳትፎ የሚገኝ ወኪል በሽልማት ሂደቱ ተሳታፊ አይሆንም፡፡

ደንብና ግዴታዎች ተፈፃሚ ናቸው፡፡

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives