ሞባይል ካርድ ሲሞሉ ቁጥሩ ከተፋቀብዎ በኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከል ቀርበው በማሳወቅ በ2 የሥራ ቀናት ውስጥ መፍትሄ ያግኙ

ሞባይል ካርድ ሲሞሉ ቁጥሩ ከተፋቀብዎ በኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከል ቀርበው በማሳወቅ በ2 የሥራ ቀናት ውስጥ መፍትሄ ያግኙ” 

 ክቡራን ደንበኞች የሞባይል አየር ሰዓት ለመሙላት ካርድ ሲፍቁ አልፎ አልፎ ጥራት የጎደላቸው የሞባይል ካርዶች በሚገጥማቸው ጊዜ በሽያጭ ማዕከላችን በመቅረብ የሚስተናገዱ ቢሆንም በሚፈለገው ፍጥነት ምላሽ እያገኙ እንዳልሆነና እስከ ወር ድረስም የሚቆይበት አጋጣሚም እንዳለ ለመረዳት ችለናል፡፡

በዚሁ መሠረት ኢትዮ ቴሌኮም ለችግሩ ዋነኛ ምክንያት የሆነውን ደረጃውን ያልጠበቀ ካርድ ለገበያ እንዳይቀርብ ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት እየሰራ የሚገኝ ሲሆን ይህ ችግር እስኪቀረፍ ድረስ ደንበኞች የሞባይል አየር ሰዓት ሲሞሉ ጥራቱን ያልጠበቀ ካርድ በሚያጋጥማቸው ጊዜ በአቅራቢያቸው በሚገኝ የኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከል በመቅረብ ጥያቄውን ባቀረቡ ከሁለት የሥራ ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ም ላሽ ማግኘት የሚችሉበት የአሰራር ስርዓት ዘ ርግቷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ደንበኞች የሞባይል አየር ሰዓት ለመሙላት ካርድ መጠቀም ሳያስፈልጋቸው ኢትዮ ቴሌኮም በሁሉም የሽያጭ ማዕከላቱ እንዲሁም በአጋር ድርጅቶች አማካኝነት በቅርቡ በሥራ ላይ ባዋለው ይሙሉ ኤሌክትሮኒክ የሞባይል የአየር ሰዓት መሙያ አገልግሎት የአየር ሰዓት መሙላት የሚችሉ ሲሆን ኩባንያችንም ይህን አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ በስፋት እየሰራ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን፡፡

ማስታወሻ ፡ ጥራት የጎደለው ካርድ አጋጥምዎት በኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከል ጥያቄ ባቀረቡ በሁለት የሥራ ቀናት ውስጥ ምላሽ ካላገኙ 994 የጥሪ ማዕከል ላይ በመደወል ወይንም በማህበራዊ ሚድያ ገፆቻችን ላይ ጥቆማ እንዲሰጡን እንጠይቃለን፡፡

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives