በቫውቸር ካርድ እና ይሙሉ የአየር ሰዓት የማከፋፈል ስራ መስራት ለምትፈልጉ ከታች ባለው መስፈርት መሰረት መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን በአክብርት እንገልጻለን፡
መስፈርት:-
- ከዚህ በፊት በጥቁር መዝገብ ዝርዝር/blacklist/ ውስጥ ያልገባ፤
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል እና በአዲስ አበባ ክልል ብቻ መስራት የሚችል፤
- በንግድ ፈቃዱ ላይ ብር200,000.00 እና ከዛ በላይ ካፒታል ያለው፤
- የቫውችር ካርድና ይሙሉ አየር ሰዓት ግዥ ሁኔታ
- ውል ከተፈረመ በኋላ ቢያንስ የ 2 ሚሊዮን ብር ባንክ ዋስትና (unconditional bank guaranty) በማቅረብ ለአንድ ወር በሚቆይ የዱቤ ሽያጭ ወይም ቢያንስ የ2ሚሊዮን ብር ሲፒዮ (CPO) በማቅረብ በካሽ በመግዛት፡፡
- ውርሃዊ እቅድ/target/
- ኢትዮ ቴሌኮም በየጊዜው የሚሰጠውን የግዥ እቅድ እንደሁኔታው የመቀየር ስልጣን አለው፤
- አዲስ አከፋፋዮች ያለ ግዥ እቅድ የሚሰሩበት የአንድ ወር የእፎይታ ጊዜ አላቸው፡፡
- ኮሚሽን
- በኢተዮ ቴሌኮም በተቀመጠው ኮሚስን መሰረት ተስማምቶ መስራት የሚችል፤
- የኮሚሽኑ ምጣኔ በኢትዮ ቴሌኮም ሊቀየር ይችላል፡፡
- ኢትዮ ቴሌኮም ሙሉ ኮሚሽኑን ለአከፋፋዩ ይከፍላል
- አከፋፋዩ በተዋረድ ለሚገኙ በስሩ ላሉ ንዑስ አከፋፋዮች ኮሚሽን የመክፍል ኃላፊነት አለበት፡፡
ከላይ በተጠቀሰው መስፍርት መሰረት መስራት ከፈለጉ ወይም ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ 6ኪሎ ያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት ዝቅ ብሎ በሚገኘው ሰሜን አዲስ አበባ ዞን ኢትዮ ትቴኮም ቢሮ በመቅረብ ማነጋገር ይቻላል፡፡
ስልክ ቁጥር፡- 0111243081/0911609988/0930377172