በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች

የደንበኞች አገልግሎት

ዘወትር እስከ ምሽቱ 5፡00 ሰዓት የደንበኞች ድጋፍ እንሰጣለን፡፡

HTB1128uNXXXXXcKaXXXq6xXFXXX4

ጂ.ኤስ.ኤም ምህፃረ ቃሉ ግሩፕ እስፔሻል ሞባይል (Group Special Mobile) ማለት ሲሆን በጣም ታዋቂ የሞባይል ግንኙነት ስርዓት ነው፡፡  አሁን አሁን የሞባይል ግሎባል ሲስተም ተብሎ ይጠራል ፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም የሞባይል ቁጥሮች 10 አሃዞች ያላቸው ሲሆን ይህም የሚጀምረው በ 911…, 912…, 913…, 920…, 921…, 922…, 930…931….932…. 933.. …. እና በመቀጠል ስድስት (6) አሃዝ የደንበኝነት ተመዝጋቢ ቁጥሮች አሏቸው :: ለምሳሌ 911-xx-xx-xx

የድህረ ክፍያ የሞባይል አገልግሎት እንደማንኛውም የሞባይል ስልክ ግንኙነት በኢትዮ ቴሌኮም ሲም ካርድ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን የአገልግሎቱን ወርሃዊ ክፍያ አገልግሎቱን ካገኙ በኋላ የሚከፍሉ ይሆናል፡፡

የቅድመ ክፍያ የሞባይል አገልግሎት በሽያጭ ማዕከሎቻችን ወይም በማንኛውም የኢትዮ ሲም ካርድ ወኪሎች ማግኘት ይችላሉ።

የኢትዮ ቴሌኮም ለቅድመ ክፍያ/ድህረ ክፍያ ሞባይል አገልግሎት ምዝገባ 30ብር የሚያስከፍል ሲሆን በተጨማሪም ለድህረ ክፍያ አገልግሎት ከ250 ብር ጀምሮ እንደ አጠቃቀማችሁ ተቀማጭ በማድረግ አገልግሎቱን ማግኝት ይችላሉ፡፡

የቢዝነስ ሞባይል 100፣ 250፣ 500፣ 1000 እና 2500 አማራጮች ያሉት  ሲሆኑ የቢዝነስ ሞባይል አገልግሎት ሲጠቀሙ ለድምጽ ጥሪዎች ፤ለመልዕክት  እና የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት ከመደበኛው ታሪፍ ጋር ሲነጻፀር ከፍተኛ ቅናሽ አለው።

  • ሁሉም ገቢ ጥሪዎች ነጻ ናቸው።
  • በመደበኛ ሰአት በደቂቃ 0.50 ሳንቲም ሲሆን ከመደበኛ ሰዓት ውጪ እንዲሁም በሀገራዊ በአላት ቀን እሁድን ጨምሮ 0.35 ሳንቲም በደቂቃ ቫትን ጨምሮ ነው።

ሮሚንግ የሞባይል አገልግሎት ተንቀሳቃሽ ስልክዎን ከኢትዮጵያ ውጪ መጠቀም የሚያስችል አገልግሎት ነው ።

ኢትዮ ቴሌኮም በአለም አቀፍ ደረጃ ከ460 በላይ አጋሮች ጋር አለም አቀፍ የሮሚንግ ስምምነት ያለው ሲሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የሚሄድ ይሆናል።

እባክዎን የቅርብ ጊዜ የሮሚንግ ክፍያዎችን ለማግኘት የኢትዮ ቴሌኮምን የሞባይል ሮሚንግ ታሪፍ ሰንጠረዥ ይመልከቱ።

ኢትዮ ቴሌኮም ለአንድ የሀገር ውስጥ መልዕክት በተመሳሳይ ኔትወርክ 12 ሣንቲም፣ ወደ ሌላ የሀገር ውስጥ ኔትወርክ 20 ሣንቲም እንዲሁም ለአለም አቀፍ መልዕክት (160 ካራክተር) 3.99 ብር የሚያስከፍል ይሆናል።

ተንቀሳቃሽ የሞባይል ስልክ አጭር የፅሁፍ መልዕክት መላክ እና መቀበል ያስችላል፡፡ የሞባይል ቀፎዎ ላይ “ሜይል ወይም መልእክት” የሚለውን አማራጭ ይጫኑ ፣ ከዚያ ወደ ‘settings’ ይሂዱ እና የአገልግሎት ማእከል ቁጥሩ +251911299708/07 መሆኑን ያረጋግጡ ፣ ካልሆነ ይህንኑ ቁጥር በመጠቀም የአገልግሎት ማእከሉን ያዘጋጁ። ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ብቻ የሚደረግ ነው፡፡ አሁን አጭር የፅሁፍ የመልክት አገልግሎት መጠቀም መጀመር ይችላሉ።

በኢትዮ ቴሌኮም ኔትወርክ መልዕክት አጭር የፅሁፍ መልዕክት መቀበል ነፃ ነው።

በአድቫንስ ፐይመንት (የቅድሚያ ክፍያ) በመክፈል ወደፊት ከሚከፍሉት ጋር የሚስተካከልልዎት ይሆናል

በድምጽ መልእክት ሳጥን ውስጥ መልእክቶችን ለመቅዳት ቫትን ጨምሮ 0.50 ሳንቲም ሲሆን ይህም ከወጪ ጥሪ ዋጋ ጋር ተመሳሳይ ነው። ከመልዕክት ሳጥኑ ውስጥ መልዕክቶችን ለማድመጥ ለሁለት ጊዜ ነጻ ነው፣ ከሁለት ጊዜ በላይ ሲያዳምጡ ለ30 ሰከንድ 0.12 ሳንቲም የሚከፍሉ ይሆናል።

ሲ.ኤል.አይ.ፒ የጥሪ መስመር መታወቂያ ሲሆን  የሚደወልሎትን የስልክ ቁጥር በተንቀሳቃሽ ስልክዎ ላይ እንዲታይ ያደርጋል።

ኮል ዌይቲንግ (Call waiting) / የጥሪ ማቆያ አገልግሎት ከሌላ ሰው ጋር እየተነጋገሩ ገቢ ጥሪን ለመቀበል እና ለመያዝ የሚያስችል አገልግሎት ነው።

እነዚህን አገልግሎቶች በነጻ ማግኘት ይችላሉ።

የጥሪ ማስተላለፍ አገልግሎት ጥሪዎን ወደ ሌላ ማንኛውም የኢትዮ ቴሌኮም ስልክ (ወደ ሞባይል ወይም ወደ መደበኛ/ገመድ አልባ ስልክ) እንዲያስተላልፉ ያስችልዎታል።

ለሁሉም የኢትዮ ቴሌኮም ሞባይል አገልግሎት ምድቦች የክፍያ ጊዜ ወርሃዊ ነው። ለበለጠ መረጃ እባኮትን ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ።  https://www.ethiochatroom.et/csp-magent-client/index2.jsp

  • ቀሪ ሂሳብዎ ዝቅተኛ ሲሆን
  • የመሙያ አማራጭ በአካባቢው በማይገኝበት ጊዜ
  • የአየር ሰአት ለመግዛት ገንዘብ በለሌለዎት ሰዓት

• የአገልግሎት ጊዜአቸው ያላለፈ የቅድመ ክፍያ የሞባይል አገልግሎት ደንበኞች ብቻ
• በደንበኝነት ቢያንስ ለ3 ወራት የቆዩ ደንበኞች፣
• የአገልግሎት ቁጥራቸው በክፍያ ምክንያት ያልተቆረጠ ደንበኞች፣
• የቀድሞ የአየር ሰዓት ብድራቸውን ሙሉ በሙሉ የከፈሉ ደንበኞች
• ለምን ያክል የክሬዲት አገልግሎት ብቁ እንደሆኑ ለማወቅ

 
*810# ይደውሉ
ለተጨማሪ አገልግሎት 5 ቁጥር ይምረጡ
1ን በመምረጥ “ብቁ መሆንዎን ያረጋግጡ” የሚለውን ይምረጡ
በአጭር የፅሁፍ መልዕክት የምናሳውቅዎ ይሆናል

ሲም ካርድዎን ለማዘጋት ወዲያውኑ ወደ ኢትዮ ቴሌካም  የጥሪ ማእከል 994 ይደውሉ ።

የሲም ካርዱ የግል መለያ ቁጥር (ፒን) ባለ አራት አሃዝ ሚስጥራዊ ቁጥር ሲሆን ይህም ሲም ካርዱን ለመስጀመር (To activate the SIM Card) ያገለግላል። በስልክ ቀፎ ማኑዋል ውስጥ የተሰጡትን መመሪያዎች በመከተል ፒኑን መቀየር ይችላሉ።

  • የፒን ቁጥርዎትን ከ3 ጊዜ በላይ በስህተት ደጋግመው ከሞሉ ሲም ካርድዎ በቀጣይ ፒዩኬ እንዲያስገቡ ይጠይቅዎታል፡፡ የፒዩኬ ቁጥርዎ ከጠፋብዎት *994# በመደወል የሚመጣልዎትን መመሪያ መከተል ወይም 994 በመደወል በተደጋጋሚ የሚደውሉባቸውን ስልክ ቁጥሮች
    እና የሲም ካርዱን ባለቤት ሙሉ ስም በመንገር ማግኘት ይችላሉ፡፡

የተጎዳው ሲም መተኪያ ብር 15 ከፍሎ በተመሳሳይ የሞባይል ቁጥር ይተካል።

  • ያሉበት አካባቢ ደካማ ወይም ምንም አይነት የኔትወርክ ሽፋን ስለሌለው ይሆናል፡፡ በስልክዎት ስክሪን ያሉት መስመሮች ይህንን ጠቋሚ ናቸው፡፡ እባክዎ የተሻለ የኔትወርክ ሽፋን የሚያገኙበት ቦታ ይሁኑ፡፡

  • በቀጥታ የኦንላይን ምልልስ ለማድረግ ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከ ምሽት 5 ሰዓት ድረስ ከዚህ በታች ባለው ሊንክ እኛን ማግኘት ይችላሉ፡፡

  • ከተለያዩ አከፋፋዮች እና ቸርቻሪዎች ላይ በስፋት ተሰራጭቶ ይገኛል፡፡ አቅራቢያዎ ያለ የኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከላችን ያገኛሉ፡፡

በገበያ ላይ የባለ  5፣ የ10፣ 15፣ 20፣ 50፣ 100፣ 250፣ 500 እና 1000 ብር የካርድ ክፍልፋዮች አሉ፡፡

ሀገር ውስጥ ለሚኖሩ ወዳጅ ዘመዶችዎ ከውጪ ሀገር የአየር ሰዓት ለመሙላት የአጋሮቻችንን ዝርዝር ከታች ያለውን ሊንክ በመጠቀም ያግኙ፡፡

www.ethiotelecom.et/international-airtime-top-up/

የድኅረ-ክፍያ መስመሬን የአየር ሰዓት በመሙላት አገልግሎቱን ለማስቀጠል ምን ላድርግ?

በአጭር የጽሑፍ መልዕክት

• ለራስዎ ለመክፈል፡ * የአየር ሰዓቱን ቁጥር# በመጻፍ ወደ 805 ይላኩ
• ለሌላ ቁጥር ለመክፈል፡ *የአየር ሰዓቱን ቁጥር*የሞባየል ቁጥር# በመጻፍ ወደ 805 ይላኩ                                 

ለምሳሌ: *የአየር ሰዓቱን ቁጥር*09xxxxxx# በመፃፍ ወደ 805 ይላኩ

በአጭር ቁጥር

• ለራስዎ ለመክፈል፡ *805*የአየር ሰዓቱን ቁጥር# በመጻፍ ይደውሉ
• ለሌላ ቁጥር ለመክፈል፡ *805*የአየር ሰዓቱን ቁጥር*የሞባየል ቁጥር# በመጻፍ ይደውሉ

ለምሳሌ: *805*የአየር ሰዓቱን ቁጥር*09xxxxxx# በመፃፍ ይደውሉ

ማሳሰቢያ:

  • መክፈል እንደሚፈልጉት የቢል መጠን የተለያዩ የሞባይል ካርድ ክፍልፋዮች መጠቀም ይችላሉ ለምሳሌ ባለ 1000፣ 500፣ 250፣ 100 እና 50 ብር ወዘተ…የሞሉት የቅድመ ክፍያ የካርድ መጠን ከቢል ክፍያዎት የበለጠ ከሆነ የቀረው መጠን ተቀማጭ በመሆን የቀጣይ ወር ቢል ላይ እንዲቀናነስ ይደረጋል፡፡
  • የቢል ሂሳብዎን በተሳካ ሁኔታ ለመክፈልዎ አጭር የፅሁፍ ማረጋገጫ እንዲደርስዎት ይደረጋል፡፡