በኢትዮ ቴሌኮም እና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መካከል የቴሌኮም አገልግሎቶች የክፍያ መፈጸሚያ አማራጮች ላይ የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ

[et_pb_section fb_built=”1″ admin_label=”section” _builder_version=”3.0.47″][et_pb_row admin_label=”row” _builder_version=”3.0.47″ background_size=”initial” background_position=”top_left” background_repeat=”repeat”][et_pb_column type=”4_4″ _builder_version=”3.0.47″ parallax=”off” parallax_method=”on”][et_pb_text admin_label=”Text” _builder_version=”3.0.47″ background_size=”initial” background_position=”top_left” background_repeat=”repeat”]

ኢትዮ ቴሌኮም የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትና እና ቅልጥፍናን በማሳደግ የደንበኛን እርካታ ለመጨመር በርካታ የማሻሻያ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡  ከዚሁ ጋር በተያያዘ የድህረ ክፍያ አገልግሎት ደንበኞች የአገልግሎት ሂሳባቸውን በቀላሉ መክፈል እንዲችሉ በቅርቡ ተግባራዊ ከተደረጉ የክፍያ አማራጮች በተጨማሪ ሌሎች አማራጭ የክፍያ ዘዴዎችን ለመተግበር ዛሬ  መስከረም 12 ቀን 2012 ዓ.ም በኢትዮ ቴሌኮም እና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መካከል ስምምነት ተከናወነ፡፡ ስምምነቱን የተፈራረሙት  የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ት ፍሬሕይወት ታምሩ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚደንት አቶ ባጫ ጊና ናቸው፡፡

በዚህም ስምምነት መሠረት፤ ደንበኞች ወርሃዊ የቴሌኮም አገልግሎትሂሳባቸውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል ከመስከረም 24 ቀን 2012 ጀምሮ፤

  • በሲ.. ብር
  • ሞባይል ባንኪንግ
  • በኢንተርኔት ባንኪንግ
  • ..ኤም
  • ቀጥታ ባንክ ማዘዣ እንዲሁም በማንኛውም የባንኩ ቅርንጫፍ በአካል በመቅረብ ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ በቀላሉ መክፈል ያስችላቸዋል፡፡

በባንክ በኩል ካሉን የመክፈያ አማራጮች በተጨማሪ ደንበኞቻችን በአቅራቢያቸው በሚገኙ በኢትዮ ቴሌኮም፣ በፍራንቻይዝ የሽያጭ ማዕከላት እና አጋር የንግድ ማዕከላት እንዲሁም በይሙሉ ኤሌክትሮኒክ የአየር ሰዓት መሙያ አማካኝነት ወይም በሞባይል ካርድ፣ ወርሃዊ የአገልግሎት ሂሳባቸውን መክፈል የሚችሉበትን አማራጮች ማቅረባችን ይታወሳል፡፡

ቀደም ሲል በለሁሉ የክፍያ ማዕከል ሲሰበሰብ የነበረው የቴሌኮም አገልግሎት ክፍያ የተቋረጠ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን በተጨማሪም በቅርቡ በህዳሴ ቴሌኮም ሲሰበሰብ የነበረውም የአገልግሎት ክፍያ መቋረጡን እያሳወቅን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተጨማሪ ሁሉንም አማራጮች በሌሎች ባንኮች በስፋት ለማስጀመር ኩባንያችን በሥራ ላይ የሚገኝ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

[/et_pb_text][/et_pb_column][/et_pb_row][/et_pb_section]

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives