የኢትዮ ቴሌኮም ኢ.አር.ፒ ቁልፍ ባህሪያት እና ጥቅሞች፡
• የተቀናጁ የሥራ ሂደቶች፡ በሁሉም የሥራ ክፍሎች ውስጥ ቁልፍ ሂደቶችን ማቀላጠፍ እና አውቶሜት ማድረግ ያስችላሉ።
• የላቀ የደንበኞች አገልግሎት፡ አገልግሎቶችን ለደንበኞች እንደፍላጎታቸው በማዘጋጀት በማቅረብ ተሞክሮን ያሳድጋል።
• ለትግበራ ፈጣን መሆን፡ ፈጣን ትግበራን በማመቻቸት የአሰራር ቅልጥፍናን ያሻሽላል።
• ምርታማነትን መጨመር፡ ለፈጣን የውሳኔ አሰጣጥ ትክክለኛ ዳታ ለማግኘት ያስችላል።
• የወጪ ቆጣቢነት፡ እጅግ ውድ ከሆነ (on-premises) የአይቲ መሠረተ ልማት ግንባታ ወጭ ያድናል።
• ሊያድግ የሚችል ሞዴል፡ እንደ ቢዝነስ ዕድገት ፍላጎት ተጨማሪ አቅምን በማግኘት ለሚጠቀሙት አገልግሎት ብቻ ክፍያ መፈጸም ያስችላል።
• በቴሌክላውድ የሚስተናገድ፡ ደንበኞች በኢትዮ ቴሌኮም አስተማማኝ ክላውድ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ መፍትሄ ማግኘት ይችላሉ።
• የባለሙያ ድጋፍ፡ ከኢትዮ ቴሌኮም የባለሙያዎች ቡድን ቀጣይነት ያለው ስልጠና እና ሙያዊ እገዛ ማግኘት ያስችላል።