በክላውድ የታገዘ የኮር ባንኪንግ ሶሉሽን

ቁልፍ ባህሪያት እና ጥቅሞች
• የተሳለጡ አሰራሮች፡ የደንበኛ ምዝገባን፣ የሂሳብ አያያዝን፣ የብድር አሰጣጥ ሂደትን እና ሪፖርት አደራረግን ጨምሮ ቁልፍ የአሠራር ሂደቶችን አውቶሜት በማድረግ ወይም በማዘመን ስህተቶችን ይቀንሳል።
• የአሁናዊ/ቅጽበታዊ ግብይት መከታተያ፡– ወቅታዊና ፈጣን የግብይት ዳታ ተደራሽነትን በማረጋገጥ የተሻለ ክትትል እና ቁጥጥር ለማድረግ እና ውሳኔ ለመስጠት ያስችላል።
• የተሻለ የደንበኛ ተሞክሮ፡ ለአባላት የሞባይል መተግበሪያን ጨምሮ በሁሉም የአገልግሎት ቻናሎች ላይ ተከታታይ እና ለተጠቃሚ ምቹ የሆነ ተሞክሮ ለማቅረብ ያስችላል።
• ለተሻለ የዳታ አስተዳደር፡ ከፍተኛ መጠን ያለው የደንበኛ ዳታን በአስተማማኝ ሁኔታ በማከማቸትና በማስተዳደር ረገድ የዳታ ተዓማኒነትን እና ተደራሽነትን ያረጋግጣል።
• ማጭበርበርን ለመከላከል እና የሕግ ተገዢነትን ለማስፈን፡– የማጭበርበር ድርጊቶችን ለመለየት እና ለመከላከል የሚያስችሉ ገጽታን በማካተት ተቋማት የቁጥጥር መስፈርቶችን እንዲያሟሉ ይረዳቸዋል።
• ወጪ ቆጣቢነት፡– በክላውድ የታገዘ ሞዴል በሃርድዌር እና በሶፍትዌር ላይ የሚወጣውን ከፍተኛ የሆነ የመዋዕለ ንዋይ ፍሰትን በግልጽ የሚያስቀር በመሆኑ አጠቃላይ የባለቤትነት ወጪ እንዲቀንሰ ያደርጋል።
• የሚጎለብት/ሊሻሻል የሚችል (Scalability)፡ ከዕድገት ደረጃቸው ጋር የሚፈጸም የክፍያ ሞዴል ተቋማት ፍላጎታቸው እያደገ ሲመጣ የአጠቃቀም ፍጆታቸውንም በቀላሉ እንዲያሳድጉ ያስችላቸዋል።
• የቴሌብር ትስስር፡– ያለምንም እንከን ከቴሌብር ጋር በማስተሳሰር ለብድር አሰጣጥ ፣ለክፍያ አገልግሎት እና ለቁጠባ ምቹ እና አስተማማኝ የሞባይል ክፍያ ዘዴን መጠቀም ያስችላል።
• ሁለንተናዊ ሞጁሎች፡ የምዝገባ፣ የምርት ዝግጅት፣ የብድር አስተዳደር፣ የሒሣብ ሠንጠረዥ (Chart of Accounts) የአሁናዊ/ቅጽበታዊ የዳሽቦርድ ሪፖርት እና ክፍያዎችን ጨምሮ የተለያዩ ኮር/አብይ ሞጁሎችን ለማቅረብ ያስችላል።
• የሞባይል መተግበሪያ፡– አባላት ሂሳባቸውን እንዲመለከቱ፣ ገንዘባቸውን እንዲያስተላልፉ፣ ብድር እንዲጠይቁ እና ክፍያ እንዲፈጽሙ የሚያስችል ምቹ አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላቸዋል።