የካቲት 22 ቀን 2016 ዓ.ም

በድጋሚ የወጣ ያገለገሉ ፈርኒቸሮች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምሥራቅ ሪጅን በሞጆ ከተማ ቴሌ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኝ የተለያዩ ያገለገሉ ፈርኒቸሮችን ግዢ ፍላጎቱ ላላቸው ድርጅቶች/ግለሰቦች/ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ግለሰብ/ድርጀት የጨረታ ሰነድ ለመግዛት በሚመጡበት ወቅት ድርጅት ከሆነ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ የንግድ ፍቃድ፤ ግለሰብ ከሆነ የታደሰ መታወቂያ ወይም ማንነታቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ዋናውን እና ኮፒ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል::

  1. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ከመጋቢት 2 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮእስከ መጋቢት 11 ቀን 2016 ዓ.ም  ከሰኞ እስከ ዓርብ በሥራ ሰዓት አዳማ ከተማ ኦሮሚያ ልማት ማህበር ህንጻ 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመስሪያ ቤቱ ሶርሲንግ ክፍል በመቅረብ ስለጨረታው መረጃ ማግኘትና የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሠነድ በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ውጤቱ እንደታወቀ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ከታወቀ ባንክ ተረጋግጦ በሚቀርብ ዋስትና (CPO) ለተጠቀሱት ላገለገሉ ዕቃዎች የሚያቀርቡትን ጠቅላላ ዋጋ (የሚጫረቱበትን ዋጋ) 5% (አምስት ከመቶ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል
  3. የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከገዙበት አድራሻ የበር መግቢያ ፍቃድ በመውሰድ እና የታደሰ መታወቂያ በመያዝ ጨረታው አየር ላይ እስከሚቆይበት ዕለት ድረስ ዕቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ ማየት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የተጠቀሱት ያገለገሉ ዕቃዎች የሚገዙበትን ዋጋ ተ.እ.ታ (VAT) ጨምረው በዋጋ ማስገቢያ ቅጽ ላይ በማካተት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውን እና የጨረታውን ቁጥር በመጥቀስ በኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን ፅ/ቤት፣ አዳማ ከተማ ኦሮሚያ ልማት ማህበር ህንጻ 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመስሪያ ቤቱ ሶርሲንግ ክፍል መጋቢት 11 ቀን 2016 ዓ.ም 5፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል:: 
  5. ጨረታው ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሰነዱን ባስገቡበት አድራሻ 7ኛ ፎቅ በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ በዕለቱ መጋቢት 11 ቀን 2016 ከቀኑ 

  8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡

  • ተጫራቾች የወሰዱትን የጫረታ ሰነድ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ያለዉ ሰነድ ተቀባይነት የለዉም፡፡

መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 022-111-0994 /022-111-3550 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives