በጠፉ የሞባይል አገልግሎት ቁጥሮች (ሲም ካርዶች) ከሚፈፀሙ ወንጀሎች እራስዎን ይጠብቁ!

 

ኩባንያችን የተለያዩ የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል ድርጊቶችን ለመከላከል የሚያስችሉ የአደረጃጀት፣ የአሰራር ስርዓት ፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ የቁጥጥርና የክትትል ሥራ እንዲሁም ከፀጥታ እና ከፍትህ አካላት ጋር በመቀናጀት በድርጊቱ የተሰማሩ አካላትን ለፍርድ እንዲቀርቡ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

በዚህ የማጭበርበር ድርጊት ላይ የተሰማሩ ወንጀለኞች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ከደንበኞች እጅ የጠፉ የሞባይል መስመሮችን (ሲም ካርዶችን) በመጠቀም በተቀናጀ ሁኔታ የቴሌኮም ማጭበርበር እና ሌሎች ከባድ ወንጀሎችን እየፈፀሙ እንደሆነ ለመረዳት ችለናል፡፡

እነዚህ አካላት ከደንበኞች እጅ በጠፋ የሞባይል ስልክ መስመር የቴሌኮም ማጭበርበር እና ሌሎች ከባድ ወንጀሎች ሊፈፅሙበት የሚችሉ በመሆኑ የሞባይል ስልክ ሲጠፋብዎ ዛሬ ነገ ሳይሉ መስመርዎን ወዲያውኑ በማዘጋት ሊፈፀሙ ከሚችሉ ወንጀሎች እራስዎንና ህብረተሰባችንን እንዲጠብቁ እናሳስባለን፡፡

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives