ቪዛ ዳይሬክት

ከ190 አገራት በላይ በቴሌብር ቨርቹዋል ካርድ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ዝወውር፤

ለቨርቹዋል ቪዛ ካርድ ይመዝገቡ፤ ባለ 16 አሐዝ ካርድ ቊጥሩን ለላኪው ያሳውቁ

ቪዛ ካርድ

ቨርቹዋል ቪዛ ካርድ የያዙ የቴሌብር ደንበኞች የቨርቹዋል ቪዛ ካርድ ቊጥራቸውን ውጭ ሀገር ለሚኖሮ ወዳጅ ዘመዶቻቸው በማጋራት ገንዘብ እንዲቀበሉ ያስችላል። ይህ አገልግሎት ካሉት የሐዋላ አገልግሎቶች ጋር ሲነጻጸር የተሻሻለና በከፍተኛ ፍጥነት ከገንዘብ ለመላክና ለመቀበል ያስችላል፡፡

ቪዛ ዳይሬክት ለመጠቀም ቅደም ተከተሎች፡-

  • ቴሌብር ሱፐር አፕን በመጠቀም በ”የኔ ቪዛ“’ አማራጭ ሥር ለቨርቹዋል ቪዛ ካርድ አገልግሎት ያመልክቱ
  • አገልግሎቱን ለማግኘት በስልክዎ የቴሌብር ሱፐርአፕን ማውረድ ወይም ማዘመን ይጠበቅብዎታል

  • ከተመዘገቡ በኋላ የማሳወቂያ ጽሁፍ መልእክት ሲደርስዎ በቴሌብር ሱፐር አፕ ላይ በመግባተት “የቪዛ ካርድ ቊጥሬ” በሚለው ሥር ባለ 16 አሐዝ ቨርቹዋል ቪዛ ካርድ ቊጥር ዎን ማግኘት ይቸላሉ፡፡

  • በቴሌብር ሱፐርአፕ የሚያገኙትን ባለ 16 አሐዝ ቨርቹዋል ቪዛ ካርድ ቊጥር ገንዘብ ለሚልክልዎ ወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ
  • የካርድዎን ዝርዝር መረጃ ደኅንነቱ በተጠበቀ መልኩ ለላኪው ማጋራትዎን እርግጠኛ ይሁኑ፡፡

  • ላኪው ባጋሩት የቨርቹዋል ቪዛ ካርድ ቊጥር መሰረት ገንዘብ ማስተላለፍ ይችላሉ፡፡
  • የተላከልዎትን ገንዘብ በቴሌብር አካውንትዎ ይቀበላሉ፡፡

በተደጋጋሚ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ

  • የቪዛ ዳይሬክት አገልግሎት ማለት የቪዛ ካርድ ያላቸው ደንበኞች 16 ዲጂት ቋሚ አካውንት ቁጥር (PAN) ቪዛ ካርድ ቁጥራቸውን ተጠቅመው ለሌላ የቪዛ ካርድ ደንበኛ ገንዘብ እንዲልኩ የሚያስችል አገልግሎት ነው፡፡

  • ደንበኞች ቴሌብር ሱፐርአፕን ተጠቅመው የቨርቹዋል ቪዛ ካርድ እንዲጠይቁ እና እነንዲኖራቸው የሚያስችል አገልግሎት ነው፡፡

  • ደንበኞች ለቨርቹዋል ቪዛ ካርድ ለመጠየቅ በቅድሚያ ቴሌብር ሱፐርአፕን ማዘመን/ማውረድ የሚጠበቅባቸው ሲሆን በመቀጠል በመተግበሪያው የፊት ገፅ ላይ “የእኔ ቪዛ” የሚለውን ይጫናሉ፡፡ በቀጣይ “ለቪዛ ካርድ ቁጥር ያመልክቱ” የሚለውን ይጫኑ፡፡

  • ደንበኞች ከቴሌብር በፅሁፍ መልዕክት የቪዛ ቁጥራቸው እንደደረሰ ማረጋገጫ ይላክላቸዋል፡፡

  • ቨርቹዋል ቪዛ ካርድ በአንድ ሰዓት ውስጥ ዝግጁ ይሆናል፡፡

  • ወደ ቴሌብር ሱፐርአፕ መተግበሪያ ይግቡ => በዋናው ገፅ ላይ “የእኔ ቪዛ”  የሚለውን ይጫኑ=> በመቀጠል “የቪዛ ካርድ ቁጥሬ”  የሚለውን ይጫኑ

  • አገልግሎቱ ለቴሌብር ሱፐርአፕ ተጠቃሚዎች ብቻ የቀረበ ነው፡፡

  • የቴሌብር ቨርቹዋል ካርድ ያላቸው ደንበኞች ባለ16 ዲጂት የቨርቹዋል ቪዛ ካርድ ቁጥራቸውን በውጭ ሀገራት ለሚገኙ በማጋራት ገንዘብ በቀጥታ ወደ ቴሌብር አካውንታቸው እንዲገባ ማስላክ ይችላሉ፡፡

  • ክፍያ መፈፀም የማይቻል ሲሆን ደንበኞች ከውጭ ሀገራት ገንዘብ እንዲቀበሉበት ብቻ ሆኖ ለጊዜው ያገለግላል፡፡ ድንበር ተሸጋሪ ክፍያዎችንም ጭምር መቀበል የሚችሉበትን አሰራር ለመፍጠር ከብሔራዊ ባንክ ጋር በዝርዝር ጉዳዮች ላይ እየተወያየን በመሆኑ አገልግሎቶቹን ስንጀምር የምናሳውቅ ይሆናል፡፡

  • CVC (Card Verification Code) ማለት ባለ ሦስት ዲጂት የደህንነት ቁጥር ሲሆን የተለያዩ የኦንላይን እና የስልክ ግብይቶችን ለማድረግ የሚያስችል በቪዛ ካርድ ጀርባ የሚገኝ መለያ ነው፡፡
  • የቪዛ ካርድ የአገልግሎት ማብቂያ ጊዜ ማለት የቪዛ ካርድዎ አገልግሎት መስጠት የሚያበቃበት ጊዜ ማለት ነው፡፡ ይህም የሚገኘው በካርድዎ የፊት ለፊት ገፅ ሲሆን ወር/አመት የሚገልፅ ነው፡፡

  • በጊዜያዊነት ቨርቹዋል ካርድ የሚጠቅመው ባለ16 ዲጂት ቁጥርዎን ውጭ ሀገር ለሚገኙ ወዳጆችዎ በማሳወቅ ገንዘብ እንዲላክልዎ ለማድረግ ብቻ ያገለግላል፡፡ በቀጣይ ለደንበኞች የአገልግሎት ማብቂያ እና CVC ቁጥራቸውን በቴሌብር ሱፐርአፕ እንዲያገኙ ለማስቻል እየተሰራ ነው፡፡

የአገልግሎት ማብቂያ ጊዜ እና CVC ካለዎት ከተለያዩ የአለም ሀገራት ግዢ አንዲፈፅሙ ያስችሎታል፡፡

  • የአገልገሎት ጊዜ ማብቂያ (ወር/አመት) እና CVC መኖሩ የቪዛ ካርድዎን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ግብይት እንዲያደርጉ ለማገዝ ነው፡፡ በመሆኑም እንዲህን የካርድዎን መረጃዎችን ለሶስተኛ ወገን አሳልፈው እንዳይሰጡ እንዲሁም ኦንላይን ግብይቶችንም ሲፈፅሙ ትክክለኛ ገፅ ላይ በሆንዎን ማረጋገጥ ይጠበቅብዎታል፡፡