ተቀማጭ ገንዘብ

ለሚያደርጉት እያንዳንዱ ግብይት ጥሬ ገንዘብ መያዝ ሰልችቶዎታል? አያስቡ ቴሌብር ችግርዎን ይቀርፍልዎታል!

በቀላሉ ጥሬ ገንዘብዎን ተመጣጣኝ ወደሆነ የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ በመቀየር እና የተለያዩ ወርሃዊ ክፍያዎን እንዲሁም ግዢዎችን ሲፈጽሙም ሆነ ገንዘብ ለመላክ 24/7 በቀጥታ በሞባይል ስልክዎ ማከናወን ይችላሉ።
  • ቴሌብር ገንዘብዎን ተመጣጣኝ ወደ ሆነ የኤሌክትሮኒክ ገንዘብለመለወጥየሚያስችልዎ አማራጭ ሲሆንይህም የቴሌብር አካውንትዎን ወይም የኪስቦርሳዎን የገንዘብ መጠን ይጨምርልዎታል።
  • አንዴጥሬገንዘብዎን ወደ ቴሌብር አካውንትዎ ካስገቡ ወደ ሌሎችደንበኞችዎ ገንዘብ ማስተላለፍ፣ የአገልግሎት ፍጆታ ወጪዎን መክፈል፣ የአስቤዛና የተለያዩ ሸቀጦችን ሂሳብ ለመክፈል እናየመሳሰሉትንየኤሌክትሮኒክ ገንዘብ ለመክፈል ያስችልዎታል።

የቴሌብር ደንበኞች ከአካውንታቸው በየትኛውም ቦታ የቴሌብር ህጋዊ ወኪሎች ወይም ከኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከላት ገንዘብ ለማውጣት ያስችላቸዋል።

የቴሌብር አገልግሎት ተጠቃሚ ካልሆኑ በአጭር ፅሁፍ መልዕክት በሚደርስዎት የቫውቸር የሚስጢር ቁጥር አቅራቢያዎ ወደሚገኝ የቴሌብር ወኪል ወይም የኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ መዕከል በመሄድ በማንኛውም ጊዜ ገንዘብዎን ማውጣት ወይም መውሰድ ይችላሉ።

በቴሌብር ገንዘብ እንዴት ተቀማጭ ማድረግ ይቻላል

  • በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የቴሌብር ወኪል ወይም የኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከላት በመሄድ
  • ለወኪሉወይምለኢትዮቴሌኮምሽያጭተወካይጥሬገንዘቡን በመስጠት
  • ወኪሉጥሬገንዘብዎን ተቀብሎተመጣጣኝ ወደ ሆነ የኤሌክትሮኒክ ቴሌብር አካውንትዎ ያስተላልፋልዎታል
  • ገንዘቡ ወደ አካውንትዎ ስለመተላለፉ የማሳወቂያ መልዕክት ይደርስዎታል
   ወይም

የባንክ አካውንትዎ ከቴሌብር ጋር የተገናኘ ከሆነ በቀጥታ ከባንክ ሂሳብዎ ወደ ቴሌብር አካውንትዎ ማስተላለፍ ይችላሉ፡፡

  • የባንክ አካውንትዎን የሞባይል መተግበሪያ ወይም አጭር ቁጥር (USSD) ይክፈቱ
  • ወደቴሌብር ለማስተላለፍ የሚለውን ይምረጡ፣
  • ከዚያምየሞባይልቁጥርእና የገንዘቡን መጠንያስገቡ፣
  • የባንክ የሚስጢር ቁጥርዎን (PIN) በመጠቀም ገንዘብ ማስተላለፍዎን ያረጋግጡ