ጥሬ ገንዘብ ማውጣት
ቴሌብር በአካውንትዎ ያስቀመጡትን ወይም ከሌላ የቴሌብር አካውንት የተላከልዎትን ገንዘብ በቀላሉ ለማውጣት ጥሩ አማራጭ ነው።
የቴሌብር ደንበኞች ከአካውንታቸው በየትኛውም ቦታ የቴሌብር ህጋዊ ወኪሎች ወይም ከኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከላት ገንዘብ ለማውጣት ያስችላቸዋል።
የቴሌብር አገልግሎት ተጠቃሚ ካልሆኑ በአጭር ፅሁፍ መልዕክት በሚደርስዎት የቫውቸር የሚስጢር ቁጥር አቅራቢያዎ ወደሚገኝ የቴሌብር ወኪል ወይም የኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ መዕከል በመሄድ በማንኛውም ጊዜ ገንዘብዎን ማውጣት ወይም መውሰድ ይችላሉ።
ቴሌብርን በመጠቀም እንዴት ጥሬ ገንዘብ ማውጣት ይቻላል
- በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የቴሌብር ወኪልወይም የኢትዮቴሌኮም የሽያጭ ማዕከል ይሂዱ፣
- *127# ላይ ይደውሉ ወይም ወደ ቴሌብር ሞባይል መተግበሪያ ይግቡ
- ‘ጥሬ ገንዘብ አውጣ’ የሚለውን በመምረጥ ከዚህ በታች ያሉትን አማራጮች በመጠቀም ገንዘብ ማውጣት ይችላሉ፡፡
- የወኪሉን መለያ ቁጥር በመጠቀም ገንዘብማውጣት
-
- የወኪሉን የገንዘብ መሰብሰቢያ መለያ ቁጥር ያስገቡ።
- ወጪ የሚያደርጉትን የገንዘብ መጠን ያስገቡ
- ሚስጢር ቁጥሩን (PIN) ያስገቡ
- ወጪ የሚደረገውን የገንዘብ መጠን ያረጋግጡ፣ ከዚያም ገንዘብዎን ቆጥረው ይረከቡ።
በቫውቸር ገንዘብ ማውጣት፡-
-
- 'በቫውቸር ገንዘብ ማውጣት' የሚለውን ይምረጡ
- የቫውቸርኮድ (ቁጥር) ይዘዙ/ያግኙ
- የቫውቸር ቁጥሩን እና የሚያወጡትን የገንዘብ መጠን ለቴሌብር ወኪሉ ይስጡ
- ወጪ ስለሚደረገው ገንዘብ ይሁንታዎን ይግለጹ
- ከወኪሉ ገንዘብዎን ይቀበሉ
የQR ኮድን ስካን በማድረግ ገንዘብ ለማውጣት
- QR ኮዱን ያንሱ (Scan) ያድርጉ
- ወጪ የሚያደርጉትን የገንዘብመጠንያስገቡ
- የሚስጢር ቁጥር (PIN) ያስገቡ
- ወጪ ስለሚደረገው የገንዘብ መጠን ይሁንታዎን ይግለጹ
- ገንዘብዎንከወኪሉ ይረከቡ
ለቴሌብር አገልግሎት ካልተመዘገቡ ነገር ግን ከሌሎች የቴሌብር ተጠቃሚዎች የተላለፈልዎትን ገንዘብ ለማውጣት
- በአጭርፅሁፍመልዕክትየተላከልዎትን የቫውቸርቁጥር (code) እና ማንነትዎን የሚገልጽ ማረጋገጫ ለወኪሉ በመሳየት
- ከዚያምወኪሉ የቫውቸር ቁጥሩን በማጣራት፣ ጥሬ ገንዘቡን ይሰጥዎታል።