ቴሌ ፑሽ-ቱ-ቶክ/ቪዲዮ ሶሉሽን ለድርጅት/ኢንተርፕራይዝ ደንበኞች

Connect, Collaborate, Command!
ቁልፍ ባህሪያት እና ጥቅሞች
• ፈጣን ቴሌ ፑሽ–ቱ-ቶክ (PTT) እና ፑሽ–ቱ–ቪዲዮ(PTV)፡ አንድን ቁልፍ ብቻ በመንካት/በመጫን ከግለሰቦች ወይም ቡድኖች ጋር ቅጽበታዊ የድምጽ እና የቪዲዮ ግንኙነት ማድረግ ያስችላል።
• የመልቲሚዲያ መልዕክት (Multimedia Messaging)፡ የጽሑፍ መልዕክቶችን፣ ምስሎችን፣ ቪዲዮዎችን እና ፋይሎችን መለዋወጥ ያስችላል።
• በአካባቢ ላይ የተመሰረቱ አገልግሎቶች፡ አስተናባሪዎች እና ተቆጣጣሪዎች ከተጠቃሚዎች እና ቡድኖች ጋር በካርታዎች በመመስረት፣ የማስተባበር ስራን እና የምላሽ ጊዜን ማሻሻል ይችላሉ።
• ጂኦፊንሲንግ እና የፍላጎት ትኩረቶች (Geofencing እና POI)፡ በተጠቃሚዎች አካባቢ ላይ በመመስረት የቡድኖችን፣ ማንቂያዎችንና ማስጠንቀቂያዎችን እንዲፈጥሩ ያስችላቸዋል።
• ያሉበትን ሁኔታ ጠቋሚ ማዕከል፡ ተጠቃሚዎች በጉዳዮች እና ክስተቶች ላይ ለአስተናባሪዎች መረጃ እና ወቅታዊ ግንዛቤን በቅጽበት ለመስጠት ያስችላል።·
• ብልጭ ጥፍት የሚሉ መልእክቶች (Splash Messages)፡ አስፈላጊ ማስታወቂያዎች በመተግበሪያው ላይ እንደ ብልጭ ድርግም የሚሉ መልዕክቶች ሊታዩ እንዲችሉ ስለሚያደርጉ ወሳኝ መረጃ እንዳያመልጥ ይረዳል፡፡·
• ፑሽ ቱ ቶክ ማእከል (PTT Center)፡ ከብዙ ኮንታክቶች፣ ቡድኖች እና ተጠቃሚዎች ጋር ከማእከል ቋት ጋር ግንኙነቶች እንዲፈጠሩ ያስችላል።·
• የተማከለ አመራር፡ በዌብ የታገዘ አሠራር ምቹ/ቀላል የሆነ የአገልግሎት አቅርቦትን በመስጠት፣ የመዳረሻ ቁጥጥርን እና የአቅም ድልድል እንዲኖር ያስችላል።·
• ደህንነቱ የተጠበቀ ተግባቦት/ኮሙንኬሽን፡ ፕላትፎርሙ በቴሌ ክላውድ የሚሰራ ሲሆን አካባቢያዊ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ከጫፍ እስከ ጫፍ የተጠናከረ ኮሙንኬሽን እንዲኖር ያስችላል።·
• ሊሻሻል የሚችል (Scalability)፡– “እንደ ዕድገት ደረጃ መክፈል” /”pay-as-you-grow” ሞዴል ኢንተርፕራይዞች/ድርጅቶች እንደ አስፈላጊነቱ አጠቃቀማቸውን በቀላሉ እንዲያሳድጉ ያስችላቸዋል።·
• የኤፒአይ ትስስር፡ ከሌሎች የቢዝነስ መተግበሪያዎች ጋር በቀላሉ ለማስተሳሰር ያስችላል።·
• የስማርትፎን ተስማሚነት፡– ለራዲዮ መገናኛ የሚስፈልጉ መሣሪያዎችን አስፈላጊነት በማስቀረት ያሉትን ስማርትፎኖች ለመጠቀም ያገለግላል።·
• በርካታ ፓኬጆች፡– ከተለያየ ወርሃዊ የደንበኝነት ክፍያ ጋር አማራጮችን ለማቅረብ ያስችላል።
• ሶሉሽኑ ኋላቀር የመገናኛ ዘዴዎች በከፍተኛ ሁኔታ እንዲሻሻሉ፣ ለኢንተርፕራይዞች የተሻሻለ የቡድን ትብብር፣ ደህንነት እና የተሳለጠ የአሠራር ኃይል፣ ወጪ ቆጣቢ ስርዓት እንዲኖር የሚያስችል ሲሆን የዚህ ቴክኖሎጂ መተግበር እንደ ደህንነት፣ ኮንስትራክሽን፣ ትራንስፖርት፣ ጤና አጠባበቅ እና መስተንግዶ ባሉ ዘርፎች የተሰማሩ ድርጅቶች ቅልጥፍናቸው እና ምላሽ ሰጪነታቸው ፈጣን እንዲሆን ያስችላል።
ፑሽ ቱ ቶክ፣ መልዕክት እና ቴክኒክ ድጋፍ እርዳታ የሚያገኙበት መስመር ጋር
የ 2 ወራት የተመዘገቡ መረጃዎች
አገልግሎቱን የሚያስጠቅም ያልተገደበ ዳታ
ሁሉንም የቢዚክ አገልግሎቶች ጨምሮ የመገኛ ቦታ፣ ቪዲዮና ሌሎች የደህንነት ባህሪያት አሉት
የ3 ወራት የተመዘገቡ መረጃዎች
አገልግሎቱን የሚያስጠቅም ያልተገደበ ዳታ
የመቆጣጠርና የማስተዳደር ፍቃድ ያለው
ተጠቃሚው እንደተመዘገበው የአገልግሎት አይነት ልክ የሪከርድ ታሪኩ ሊስተካከል ይችላል፡፡
አገልግሎቱን የሚያስጠቅም ያልተገደበ ዳታ