የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ፣ ከኢትዮ ቴሌኮም የባህር ዳር ፅ/ቤት ማኔጅመንት እና ሠራተኞች ጋር በባህር ዳር ከተማ በተለምዶ ዓባይ ማዶ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ አገር አቀፉን የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አስጀመሩ፡፡

አትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ፣ ከኢትዮ ቴሌኮም የባህርዳር ፅ/ቤት ማኔጅመንት እና ሠራተኞች ጋር በባህር ዳር ከተማ በተለምዶ ዓባይ ማዶ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ አገር አቀፉን የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አስጀመሩ፡፡

የኮቪድ -19 ወረርሽኝ የወቅቱ ስጋት እንደመሆኑ የአረንጓዴ አሻራ ቀን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ከሚደረገው ጥንቃቅቄ ጋር ተጣጥሞ እንዲካሔድ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ያስተላለፉትን ጥሪ ተከትሎ የኩባንያችን ዋና/ ሥራ አስፈፃሚ፣ ማኔጅመንት እና ሠራተኞች የራሳቸውን አረንጓዴ አሻራ በማሳረፍ ለሃገራዊው ጥሪ ያላቸውን ድጋፍ እና ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል፡፡

በቀጣይም ይኸው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የኮቪድ -19 ወረርሽኝ የመከላከያ መንገዶችን ተግባራዊ በማድረግ በተቋም ደረጃ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ በሃገር አቀፍ ደረጃ በሚገኙ የኩባንያችን ፅ/ቤቶች በኩል ተጠናክሮ የሚካሔድ ይሆናል፡፡

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives