ኢትዮ ቴሌኮም ሁለት ዘመናዊ ኤሌክትሪክ መኪኖችን እና አምስት ባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎችን ለዕድለኞች በሽልማት አበረከተ!

ኩባንያችን 130ኛ ዓመት ክብረ-በዓሉን ምክንያት በማድረግ ከመስከረም 12 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ለደንበኞች ባዘጋጀው የኢትዮ 130 ሜጋ ፕሮሞ እና ኢትዮ 131 ላኪ ስሎት ሽልማት መርሃግብር ልዩ ልዩ ሽልማቶችን እያበረከተ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡


ኩባንያችን በዛሬው ዕለትም በኢትዮ 130 ሜጋ ፕሮሞ መርሃ ግብር ለእጣው ብቁ ለሆኑ 393,375 ልዩ ደንበኞች አንድ ቢ.ዋይ.ዲ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪና እንዲሁም ለእጣው ብቁ ለሆኑ 540,566 ደንበኞች ሶስት ባለ 3 እግር ተሽከርካሪ ዕጣን ለእድለኞች አውጥቷል፡፡


በኢትዮ 131 ላኪ ስሎት ሽልማት መርሃግብር ደግሞ ለእጣው ብቁ ለሆኑ 226,970 ደንበኞች አንድ ቢ.ዋይ.ዲ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪና እንዲሁም ለእጣው ብቁ ለሆኑ 407,200 ደንበኞች ሁለት ባለ 3 እግር ተሽከርካሪ ዕጣን ለእድለኞች አውጥቷል፡፡


ቀደም ሲል ኩባንያችን 130ኛ ዓመት ክብረ-በዓሉን በማስመልከት ሁለት ቢ.ዋይ.ዲ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለአዲስ አበባ እና ለወሊሶ ባለ ዕድለኞች እዲሁም ሶስት ባለ 3 እግር ተሸከርካሪ ለሀረር፣ ለአርሲ ነገሌ እና ለሆሳዕና ባለ ዕድለኛ ደንበኞቻችን ቁልፍ ማስረከቡ ይታወሳል፡:


ኩባንያችን ባለፉት አምስት ወራት 141 ዘመናዊ ስማርት ስልኮችን፣ በየቀኑ እና በየሳምንቱ በድምሩ 10.56 ሚሊዮን ብር የቴሌብር ኤሌክትሮኒክስ ገንዘብ እንዲሁም 1.18 ሚሊዮን የሞባይል ጥቅሎችን በአጠቃላይ ዛሬ የሚወጡትን ሽልማቶች ሳያካትት ከ 49.45 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን ሽልማቶች አበርክቷል፡፡


መርሃ ግብሩ አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን ደንበኞች በኢትዮ 130 ፕሮሞ እና በኢትዮ 131 ላኪ ስሎት እየተጫወቱ ዘመናዊ የኤክትሪክ መኪናን ጨምሮ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን ማሸነፍ የሚችሉ መሆኑ ተገልጿል::
                                 

                                 የካቲት 26 ቀን 2017 ዓ.ም፣ ኢትዮ ቴሌኮም

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives