ኢትዮ ቴሌኮም ሁለት ዘመናዊ ኤሌክትሪክ መኪኖችን ለዕድለኞች በሽልማት አበረከተ!

ኩባንያችን 130ኛ ዓመት ክብረ-በዓሉን ምክንያት በማድረግ ከመስከረም 12 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ለደንበኞች ባዘጋጀው የኢትዮ 130 ሜጋ ፕሮሞ እና ኢትዮ 131 ላኪ ስሎት ሽልማት መርሃግብር ልዩ ልዩ ሽልማቶችን እያበረከተ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በዛሬው ዕለትም በመጀመሪያው ዙር ዕጣ ለወጣላቸው የአዲስ አበባ እና የወሊሶ ባለ እድለኞች ሁለት ዘመናዊ የቢ.ዋይ.ዲ  የኤሌክትሪክ መኪኖችን ቁልፍ በቃሉ መሠረት አስረክቧል፡፡

ኩባንያችን 130ኛ ዓመት ክብረ-በዓሉን በማስመልከት ባለፉት 19 ሳምንታት፤ 3 ባለ 3 እግር ተሸከርካሪ ለሀረር፣ ለአርሲ ነጌሌ እና ለሆሳእና ባለ እድለኛ ደንበኞቻችን ቁልፍ ማስረከቡ የሚታወስ ሲሆን በተጨማሪም 124 ዘመናዊ ስማርት ስልኮችን፣ በየቀኑ እና በየሳምንቱ በድምሩ 9.12 ሚሊዮን ብር የቴሌብር ኤሌክትሮኒክስ ገንዘብ ለ323 ደንበኞች እንዲሁም ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሞባይል ጥቅሎችን ጨምሮ እስካሁን ከ43.26 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን ሽልማቶች አበርክቷል።

በቅርቡም ተጨማሪ ሁለት ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪኖችን እንዲሁም 3 ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪዎችን(ባጃጅ) በእጣ ለማስተላለፍ በዝግጅት ላይ ይገኛል::

መርሃ ግብሩ በቀጣይ ለሁለት ወር ተኩል የሚዘልቅ ሲሆን ለዕድለኛ ደንበኞች ተጨማሪ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪና እና ባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ በየቀኑ እና በየሳምንቱ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን ባለ እድል የሚያደርጋቸዉ ይሆናል።

የካቲት 4 ቀን 2017 .

ኢትዮ ቴሌኮም

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives