ኢትዮ ቴሌኮም በአዲስ አበባ ከሚገኙ ክፍለ ከተሞች ለተውጣጡ አንድ መቶ ሴቶች በፋሽን ዲዛይን የሙያ መስክ ነፃ የትምህርት እድል መስከረም 23 ቀን 2ዐ12 ዓ/ም ሰጠ፡፡

ኩባንያችን በትምህርት ዘርፍ ከሚያደርጋቸው የማህበራዊ ኃላፊነት ሥራዎች መካከል ይህ የትምህርት እድል የተመቻቸው ሴቶች በትምህርት፣ በሥራ እንዲሁም በአጠቃላይ የኢኮኖሚ መስኮች ከወንዶች ያነሰ ተሳትፎ ያላቸው መሆኑን ከግምት በማስገባት ሴቶችን ማስተማር እና በሥራ ማሰማራት ለቤተሰብ፣ ለማህበረሰብ፣ ብሎም ለሀገር ያለውን ከፍተኛ ሚና በመገንዘብ ነው፡፡ ኩባንያችን የዚህ የትምህርት እድል ተጠቃሚ ሴቶችን በመመልመል ሂደት ውስጥ በዋነኝነት የኢኮኖሚ አቅምን ከግንዛቤ ውስጥ ያስገባ ሲሆን በተለይም ከፍለው መማር የማይችሉ ሴቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ልዩ ትኩረት ተደርጓል፡፡

ፕሮጀክቱ መስከረም 23 ቀን 2ዐ12 ዓ/ም ሰልጣኝ ተማሪዎች፣ የኢትዮ ቴሌኮም ማኔጅመንት እና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ይፋ ተደርጓል፡፡ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አሰስፈጻሚ ወ/ት ፍሬሕይወት ታምሩ ባደረጉት ንግግር ተቋማት ገቢያቸውን ከማሳደግ ጎን ለጎን ማሕበራዊ ኃላፊነታቸውን ቢወጡ የሕብረተሰቡን ችግር መቅረፍ እንደሚቻል አስገንዝበዋል::

ኩባንያችን ከሚሰጠው የቴሌኮም አገልግሎት ጎን ለጎን ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት የሚያስፈልገውን ተቋማዊ አሰራር በማጠናከር፣ እቅድ በማውጣት እና አስፈላጊውን በጀት በመመደብ፣ አመራሩና ሠራተኛው ጠንካራ፣ አዎንታዊና በተግባር የሚገለጽ አመለካከት በማዳበር በትኩረትና በቁርጠኝነት እየሠራ ይገኛል፡፡ በዚህ ረገድ ቀደም ሲል በትምህርት፣ በጤና፣ በሰብዓዊ ድጋፍ እና በሌሎች የህብረተሰብ ችግሮች እና ፍላጎቶች ዙሪያ ሲሠራ ቆይቷል አሁንም በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡
የነጻ ትመህርት ዕድሉን ያገኙ ሴት ሠልጣኞች የፋሽን ዲዛይን ሙያ ፍላጎት ኖሯቸው በአቅም እጥረት ሳይሰለጥሉ ቢቆዩም በኢትዮቴሌኮም አማካኝነት ዕድሉን ማግኘታቸው እንዳስደሰታቸው እንዲሁም ይበልጥ ኃላፊነት እንዲሰማቸው ማድረጉን ገልጸዋል፡
የዕድሉ ተጠቃሚ ሴቶችም በሚያገኙት የፋሽን ዲዛይን ሙያ ዕውቀት ታግዘው በቀጣይ ለራሳቸው የገቢ ምንጭ የሚፈጥሩ፣ ለቤተሰባቸው አጋዥ፣ ለአካባቢያቸው ምሳሌ እንዲሁም ለሀገራቸው ኩራት እንደሚሆኑ ኩባንያችን ያምናል፡፡ ሀገራችንም በሀገራዊ ምርቶች እና አገልግሎቶች ወደ ፊት ለመራመድ ከፍተኛ ጥረት የምታደርግበት ወቅት በመሆኑ በዚህ የሙያ ዘርፍ መሰልጠን የወደፊት ብሩህ ዘርፍ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ኩባንያችን ሙሉ እምነት አለው፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም ትምህርት ለሀገር እና ለማህበረሰብ ግንባታ ያለውን አገራዊ ፋይዳ በመገንዘብ ወደፊትም በተመሳሳይ መልኩ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በተጠናከረ መልኩ ለመወጣት ያላሰለሰ ጥረት እንደሚያደርግ በዚህ አጋጣሚ ይገልፃል፡፡

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives