ኢትዮ ቴሌኮም ለኩባኒያው አገልግሎት የማይሰጡ የተለያዩ የኢንቨንተሪ እና ስክራኘ ዕቃዎችን እንዲሁም ቋሚ ያገለገሉ የቢሮ ፈርኒቸሮችን ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር SC/L/WRM/002/2015

ኢትዮ ቴሌኮም አዲስ እና ያገለገሉ ልዩ ልዩ የከባድ እና ቀላል መኪና መለዋወጫዎች፣ የግንባታ መሣሪያዎች፣ የሥራ መገልገያ የእጅ መሳሪያዎችን የኢንፎርሜሽን ሲስተም እና የኔትወርክ ዕቃዎች፣ የሲሲቲቪ ካሜራዎች፣ የቢሮ ፈርኒቸር፣ የመኪና ጐማዎች፣ የፍሎረሰንት አምፖል ማቀፊያዎች፣ የቤት ክዳን ቆርቆሮዎች፣ የእንጨት ፖሌቶችና የማሸጊያ ሳጥኖች፣ አጣናዎች፣ ቁርጥራጭ ካርቶኖች፣ የፖርቲሽን ዕቃዎች፣ ንቃይ የኘላስቲክ በር እና መስኮቶችን፣ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከታህሳስ 1ዐ እስከ ታህሳስ 2ዐ ቀን 2015 ዓ.ም 11:30 ድረስ በማንኛውም ቀን እና ሰዓት በቴሌ ብር አማካኝነት የማይመለስ አንድ መቶ ብር በመክፈል ከ www.extratenders.comwww.2merkato.com እና www.afrotender.com ዌብ ሳይቶች  መግዛት የሚችሉ ሲሆን ንብረቶቹን ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች የታደሰ መታወቂያቸውን በመያዝ መስቀል ፍላወር እና አቃቂ በሚገኙት የኩባንያው ዕቃ ግምጃ ቤቶች እንዲሁም ገርጂ ሮባ ዳቦ፣ ገላን እና አስኮ በሚገኘው ኢትዮ ቴሌኮም ማዕከሎች በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡

ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአቃቂ ዕቃ ግምጃ ቤት ታህሳስ 21 ቀን 2015 ዓ.ም ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡

ኩባንያው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives