የቢሮ ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ

                                                                                  የጨረታ ቁፕር – NAAZ/FF/370/23

ኢትዮ ቴሌኮም ሰሜን አዲስ አበባ ዞን ጽ/ቤት ፈረንሳይ አካባቢ በሚገኘው ህንፃ ላይ የተወሰኑ ክፍት ክፍሎችን ማከራየት በመፈለጉ ለንግድ/ለቢሮ አገልግሎት ለመከራየት ፍላጎት ያላቸውን ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል።

  1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከመስከረም 03 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 23 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ከኤክስትራ ቴንደር (www.extratenders.com) ፣ አፍሮ ቴንደር (www. afrotender.com) እና ቱ መርካቶ ዶት ኮም (www.2merkato.com) ዽረ ገፅ (web site) የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በቴሌ ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች ከተጠቀሱት ድረ ገፆች የጨረታ ሰነድ በመግዛት ፈረንሳይ አካባቢ በሚገኘው ህንፃ ላይ የሚከራዩትን ክፍት hፍሎች ከመስከረም 03 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 22 ቀን 2016 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ማየት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የታደሰ እና አግባብነት ያለው የንግድ ሥራ ፈቃድ/ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች ከሆኑ የታደሰ የምዝገባ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  4. የግብር ከፋይ የምስhር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ (በንግድ ስራ ለተሰማሩ ድርጅቶች ብቻ)።
  5.  ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በክፍያ ማዘዣ ቼh /CPO/ ብር 10,000.00 ከጨረታ ሰነዱ ጋር ያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6.  ጨረታው መስከረም 23 ቀን 2016 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ተዘግቶ በእለቱ ጠዋት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  7. ኢትዮ ቴሌኮም የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-1243053 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

                                                                               ኢትዮ ቴሌኮም

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives