ኢትዮ ቴሌኮም ሰ/ምስ/ሪጅን የተለያዩና የተቆራረጡ የፕላሰቲክ ነክ ማተሪያሎች፤የተለያዩ መጠን ያላቸዉ ላሜራ ሽቶች፡ቱቦላሬ ብረቶች የኬብል ድራም ብረቶች ያገለገሉ የበርና መስኮቶች ፤አገልግሎት የሰጡ የታወር ብረቶች ፤ያገለገሉ የፌሮብረቶች ፤ የተነቀሉ የብረት በር እና መስኮቶች ባሉበት ሁኔታ ለሕጋዊ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

ቀን መስከረም 13, 2014 ዓ.ም

የጨረታ ቁጥር 01/2014

ኢትዮ ቴሌኮም ሰ/ምስ/ሪጅን የተለያዩና የተቆራረጡ የፕላሰቲክ ነክ ማተሪያሎች፤የተለያዩ መጠን ያላቸዉ ላሜራ ሽቶች፡ቱቦላሬ ብረቶች የኬብል ድራም ብረቶች ያገለገሉ የበርና መስኮቶች ፤አገልግሎት የሰጡ የታወር ብረቶች ፤ያገለገሉ የፌሮብረቶች ፤ የተነቀሉ የብረት በር እና መስኮቶች ባሉበት ሁኔታ ለሕጋዊ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ጨረታው የሚቆይበት ከመስከረም 14 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መሰከረም 28 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ይሆናል፡፡

በመሆኑም ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት በሚመጡበት ወቅት የዘመኑ ግብር የከፈሉበትን የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣የታደሰ መታወቂያ ወይም ማንነታቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ዋናውንና ኮፒ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል::

1. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ከመስከረም 13 ቀን 2014 እስከ መስከረም 28 ቀን 2014 ዓ.ም. ከሰኞ እስከ ዓርብ በሥራ ሰዓት ከሰ/ምስ/ሪጅን ዕቃ ግምጃ ቤት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡

2. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ውጤቱ እንደታወቀ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) ለተጠቀሱት ለኩባኒያዉ ዕቃዎች የሚያቀርቡበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% (አምስት ከመቶ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

3. የጨረታ ማስከበሪያው ዋስትና ከታወቀ ባንክ ተረጋግጦ በሚቀርብ ሲፒኦ(CPO) መሆን አለበት፡፡

4. ተጫራቾች ለሽያጭ የቀረቡትን እቃዎች ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ እና የታደሰ መታወቂያ በመያዝ መስከረም 13 ቀን 2014 እስከ መስከረም 28 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ድረስ ደሴ ካራጉቱ ወይም ኬላ አካባቢ ስ/ምስ/ሪጅን እቃ ግ/ቤት በሚገኘው የድርጅቱ ዕቃ ግምጃ ቤት በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡

5. ተጫራቾች የተጠቀሱትን ከኩባኒያዉ አገልግሎት የተመለሱ ዕቃዎችን የሚገዙበትን ዋጋ ቫትን (VAT) ጨምረው በዋጋ ማቅረቢያ ቦታው ላይ በማካተት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውን እና የጨረታውን ቁጥር በመጥቀስ በኢትዮ ቴሌኮም ሰ/ምስ/ሪጅን ፒያሳ ሁዳ ሪል ስቴት ቢሮ ቁጥር 211 2ኛ ፎቅ መስከረም 28 ቀን 2014 ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል::

6. ተጫራቾች የተጠቀሱትን ከኩባኒያዉ አገልግሎት የተመለሱ ዕቃዎችን የሚገዙበትን ዋጋ ቫትን (VAT) ጨምረው በዋጋ ማቅረቢያ ቦታው ላይ በማካተት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውን እና የጨረታውን ቁጥር በመጥቀስ በኢትዮ ቴሌኮም ሰ/ምስ/ሪጅን ፒያሳ ሁዳ ሪል ስቴት ቢሮ ቁጥር 211 2ኛ ፎቅ መስከረም 28 ቀን 2014 ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል::

7. ተጫራቾች በጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ መሳተፍ ይችላሉ፡፡

8. ኢትዮ ቴሌኮም የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

9. ለተጨማሪ መረጃ ደሴ ሪፈራል ሆስፒታል አጠገብ ስ/ምስ/ሪጅን በሚገኘው በኢትዮ ቴሌኮም ዕቃ ግምጃ ቤት ወይም በኢትዮ ቴሌኮም ሰ/ምስ/ሪጅን ፒያሳ ሁዳ ሪል ስቴት ቢሮ ቁጥር 211 2ኛ ፎቅ ሥራ አስኪያጅ ቢሮ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር፡ 0911 51 23 81 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል ፡፡

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives