ኢትዮ ቴሌኮም በማዕከላዊ ምዕራብ ሪጅን ከተሞች የላቀ ፍጥነት ያለው የኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት ጀመረ
ኩባንያችን ከፍተኛ የዳታ አጠቃቀም በሚታይባቸው 103 ከተሞች የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎትን ለማስፋፋት የያዘውን ዕቅድ ተከትሎ በዛሬው ዕለት በማዕከላዊ ምዕራብ ሪጅን በሚገኙ አምስት ከተሞች (በአምቦ፣ ሰበታ፣ ቡራዩ፣ ሆለታ እና ወሊሶ) የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ የሞባይል ኢንተርኔት ማስፋፊያ ፕሮጀክት ሥራ አጠናቆ አገልግሎቱን ማስጀመር ችሏል።
የ4ጂ አገልግሎት የላቀ ፍጥነትና ባንድዊድዝ እንዲሁም አስተማማኝ የዳታ አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ ደንበኞቻችን አገልግሎታቸውን ዲጂታይዝ ለማድረግ፣ ምርታማነትን ለማሳደግ እና በአጠቃላይ የቴሌኮም አገልግሎት ላይ ያላቸውን ተሞክሮ በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ ያስችላቸዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም እስካሁን ባደረጋቸው የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎት ማስፋፊያ ሥራዎች የዛሬውን ጨምሮ በአዲስ አበባ፣ በደቡብ ምሥራቅ ሪጅን፣ በሰሜን ምዕራብ ሪጅን፣ በምሥራቅ ምሥራቅ ሪጅን፣ በደቡብ ደቡብ ምዕራብ ሪጅን፣ በምስራቅ ሪጅን፣ በማዕከላዊ ምስራቅ ሪጅን፣ በሰሜን ምስራቅ ሪጅን፣ በሰሜን ምሥራቅ ምሥራቅ ሪጅን፣ ደቡብ ምዕራብ ሪጅን፣ ደቡብ ሪጅን እና በሰሜን ሰሜን ምዕራብ ሪጅን የሚገኙ 72 ከተሞችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ችሏል።
በቀጣይነትም ኩባንያችን በተመሳሳይ ሁኔታ የዳታ ትራፊክ እድገትና ፍላጎትን መሠረት ባደረገ መልኩ በዕቅድ ይዞ እያከናወናቸው ያሉ የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎት የማስፋፊያ ሥራዎችን በማጠናቀቅ በተለያዩ የክልል ከተሞች አገልግሎቱን በቅርቡ ለማስጀመር የሚያስችሉ ቅድመ ሥራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል።
በዚህ አጋጣሚ የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎት በተስፋፋባቸው ከተሞች የምትገኙ ደንበኞች በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የኩባንያችን የሽያጭ ማዕከል የ3ጂ ሲም ካርዳችሁን ወደ 4ጂ በነፃ በማሳደግ 4ጂ ኤል.ቲ.ኢ መጠቀም በሚያስችል የሞባይል ቀፎ፣ ታብሌት ወይም ዶንግል አማካኝነት እጅግ ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት እንድትጠቀሙ ግብዣችንን እናቀርባለን።
በተጨማሪም የቴሌኮም አገልግሎት መጠቀሚያ መሣሪያ (smart phone) እና የይዘት (content) አቅራቢዎች በመረጃ የበለፀገ ማህበረሰብና ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ እና አሁን የተዘረጋውን ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የሞባይል ኔትወርክ በስፋት ለመጠቀም የሚያስችሉ ዘመናዊ የሞባይል ቀፎዎችና ይዘቶችን ለህብረተሰቡ በስፋትና በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የበኩላችሁን አስተዋጽዖ እንድታደርጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ነሐሴ 20 ቀን 2013 ዓ.ም
ኢትዮ ቴሌኮም
Ethio telecom Launches LTE Advanced Mobile Internet Service in Central West Region
Following the company’s three years growth strategy plan to expand 4G LTE service in 103 cities with high data usage, we are thrilled to announce the launching of LTE Advanced mobile internet service in the Central West Region (Ambo, Sebeta, Burayu, Holeta and Woliso) towns where high mobile data traffic has been observed. We believe that high bandwidth, high-speed features and reliable data services of 4G LTE will enable and empower our customers to digitize their services, increase productivity and improve their experiences.
So far, Ethio telecom has expanded its 4G LTE service in Addis Ababa and 12 regions namely Southeast Region, Northwest Region, East East Region, South South West Region, East Region, Central East Region, North East Region, North East East Region, Southwest Region, South Region and North North West Regions of 72 towns including Central West Region.
Likewise, our company is about to finalize the expansion of 4G LTE service in line with the data growth and demand and is in the process of launching the service in various regional towns soon.
In this regard, we would like to call up on players in the ecosystem to capitalize this opportunity by providing useful contents & affordable handsets and join hands in realizing digital inclusion which paves the way for digital economy.
We are also pleased to request our esteemed customers who reside in those towns where the 4G LTE service is already launched and available to visit the nearby Ethio telecom shops and upgrade their 3G SIM cards to 4G for free of charge so as to enjoy the fruit of 4G LTE internet service.
26 August 2021
Ethio telecom