ኢትዮ ቴሌኮም በሰሜን ምዕራብ ሪጅን ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የ4ጂ ኤል᎐ቲ᎐ኢ አድቫንስንድ አገልግሎት ጀመረ
የLTE Advanced የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት በሰሜን ምዕራብ ሪጅን ከተሞች ማስጀመራችንን ስንገልጽ በታላቅ ደስታ ነው፡፡ በሰሜን ምዕራብ ሪጅን ውስጥ በሚገኙ ሰባት ከተሞች ማለትም በባህር ዳር፣ ደብረ ማርቆስ፣ ፍኖተ ሰላም፣ ቡሬ፣ ዳንግላ፣ እንጅባራ እና ቻግኒ የLTE Advanced አገልግሎቱን ማስጀመር ተችሏል፡፡
የLTE Advanced አገልግሎት ከፍተኛ ፍጥነትና ባንድዊድዝ እንዲሁም አስተማማኝ የዳታ አገልግሎት የሚሰጥ እንደመሆኑ ደንበኞቻችን አገልግሎታቸውን ዲጂታይዝ ለማድረግ፣ ምርታማነትን ለማሳደግ እና በአጠቃላይ የቴሌኮም አገልግሎት ላይ ያላቸውን ተሞክሮ በከፍተኛ ሁኔታ የሚያሳድግ ነው፡፡
በኩባንያችን የሦስት ዓመት የእድገት ስትራቴጂ ላይ እንዳመላከትነው በአዲስ አበባና በሁሉም ክልሎች የዳታ ትራፊክ እድገትና ፍላጎትን መሠረት ያደረገ የ4G/LTE አገልግሎት የማስፋፊያ ሥራዎችን ለማከናወን ታቅዶ እየተሰራ ሲሆን በዚህም መሠረት በቀጣይ ወራት በሌሎች የክልል ከተሞች ተመሳሳይ አገልግሎት ለማስጀመር የሚያስችሉ ቅድመ ሥራዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡
በዚህ አጋጣሚ የቴሌኮም አገልግሎት መጠቀሚያ መሣሪያ (smart phone) እና የይዘት (content) አቅራቢዎች በመረጃ የበለጸገ ማህበረሰብና ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ እንዲሁም አሁን የተዘረጋውን ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የሞባይል ኔትወርክ በስፋት ለመጠቀም የሚያስችሉ ዘመናዊ የሞባይል ቀፎዎችና ይዘቶችን ለህብረተሰቡ በስፋትና በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የበኩላችሁን አስተዋጽዖ እንድታደርጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
Ethio telecom Launches 4G LTE Advanced Service in North West Region
We are pleased to announce the launching of LTE Advanced Services in North West Region. The LTE expansion has covered towns: Bahir Dar, Debre Markos, Finote Selam, Bure, Dangila, Injibara and Chagni, where high mobile data traffic has been observed.
Given the reliability, high bandwidth and high-speed features of LTE Advanced services, we hope that it will enable and empower our customers to digitize their services, increase productivity and improve their experiences. We sincerely appreciate all our stakeholders who have provided required supports to realize the project within a short period of time.
As clearly outlined in our three-years growth strategy, data traffic growth and demand based 4G/LTE expansion in Addis and regional towns is among the major strategic initiatives. Accordingly, over the next few months, we will be launching similar services in other parts of the country, for which preparation works are underway.
In this regard, we would like to call upon players in the ecosystem to capitalize this opportunity by providing useful contents and affordable handsets and join hands in realizing digital inclusion which paves the way for digital economy.