ኩባንያችን በ3ኛው ዙር የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ በያዘው ስትራቴጂያዊ ዕቅድ መሠረት በ67 ከተሞች አዲስ የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎት እንዲሁም በ27 ከተሞች ደግሞ ተጨማሪ የማስፋፊያ ስራዎችን በማከናወን አገልግሎቱን መስጠት ጀምሯል፡፡

በተለይም በቴሌኮም ማዕከላዊ ምስራቅ ሪጂን በ6 ከተሞች፣ በማዕከላዊ ሰሜን ሪጂን በ13 ከተሞች፣ በምስራቅ ምስራቅ ሪጂን 7 ከተሞች፣ በምስራቅ ሪጂን በ8 ከተሞች፣ በሰሜን ምስራቅ ምስራቅ ሪጂን በ16 ከተሞች፣ በሰሜን ምስራቅ ሪጂን በ18 ከተሞች፣ በሰሜን ሰሜን ምዕራብ ሪጂን በ9 ከተሞች፣ በሰሜን ምዕራብ ሪጂን 16 ከተሞች እና በደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባ ከፍተኛ የዳታ አጠቃቀም በሚታይባቸው 67 ከተሞች የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎትን ያስጀመርን ሲሆን በ27 ከተሞች ደግሞ የማስፋፊያ ስራዎች መስራታችንን ስንገልጽ በታላቅ ደስታ ነው፡፡

በዚህም መሠረት ኩባንያችን በአሁኑ ወቅት ጠቅላላ የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎት ተጠቃሚ የሀገራችን ከተሞችን ብዛት ወደ 181 ማድረስ የቻለ ሲሆን፣ በቀጣይም ከፍተኛ የዳታ አጠቃቀም በሚታይባቸው ሌሎች የሀገራችን ከተሞች የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት አዲስ እና ተጨማሪ የማስፋፊያ ሥራዎችን በማከናወን አገልግሎቱን የምናስጀምር ይሆናል፡፡

የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎት የላቀ ፍጥነትና ባንድዊድዝ እንዲሁም አስተማማኝ የዳታ አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ ደንበኞቻችን አገልግሎታቸውን ዲጂታይዝ ለማድረግ፣ ምርታማነታቸውን ለመጨመር እና በአጠቃላይ የቴሌኮም አገልግሎት ላይ ያላቸውን ተሞክሮ በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ ያስችላቸዋል።

አዲስ እና ተጨማሪ 4 ኤል.. አድቫንስድ አገልግሎት ማስፋፊያ የተደረገባቸው ከተሞች ዝርዝር

የቴሌኮም ሪጅን

ከተማ

 

የቴሌኮም ሪጅን

ከተማ

 

የቴሌኮም ሪጅን

ከተማ

ማዕከላዊ ምስራቅ ሪጅን

ባቢሌ

ማዕከላዊ ሰሜን ሪጂን

አረርቲ

 

 

 

ሰሜን ምዕራብ ሪጂን

አዲስ ቅዳም

ባቲ

ጫጫ

አማኑኤል

ጉርሱም

ጫንጮ

ባህር ዳር

ሀረር

 ደብረብርሀን

ቡሬ

ሀረማያ

ደብረ ሲና

ቻግኒ

መልካ ራፋ (ኮምቦልቻ)

ደገም

ዳንግላ

ምስራቅ ምስራቅ ሪጂን

ጭናክሰን

ፍቼ

ደብረ ማርቆስ

ደገሀቡር

ገርበ ጉራቻ

ደብረ ወርቅ

ሀርገሌ

ለሚ

ደንበጫ

 ሀርትሼክ

መሀል ሜዳ

ፈንድቃ

ጅግጅጋ

ሙከጡሪ

ፈረስ ቤት

ቀበሪበያህ

ሰንዳፋ

ፍኖተ ሰላም

ተጎጫሌ

ሸዋ ሮቢት

ሉማሜ

ምስራቅ ሪጂን

በዴሳ

ሰሜን ምስራቅ ምስራቅ ሪጂን

አፍዴራ

መራዊ

ደደር

አሳይታ

መርጦ ለማሪያም

ድሬዳዋ

አዋሽ 7 ኪሎ

ሞጣ

ገለምሶ

አዋሽ አርባ

ደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባ ዞን

ሰበታ

ቁልቢ

በርታ

 

ሚኤሶ

ጭፍራ

 

ሺንሌ

 ዳልፋጊ

 

ቱሎ

ዱብቲ

 

ሰሜን ምስራቅ ሪጂን

አከስታ

ኤሊዳር

 

ባቲ

ኤሊውሃ

 

ጨፋ ሮቢት

ገዋኔ

 

ደጋን

ልዋን

 

ደሴ

መልካ ወረር

 

ገርባ

ሚሌ

 

ጊምባ (ቱሉ አወሊያ)

ናሜላፋን (ተላላክ)

 

ግሸን

ሰመራ

 

ሀርቡ

ሰሜን ሰሜን ምዕራብ ሪጂን

አዲስ ዘመን

 

ሀይቅ

ደባርቅ

 

ከሚሴ

ደብረ ታቦር

 

ኮምቦልቻ

ገንደ ውሃ

 

ኩታበር

ጎንደር

 

ላሊበላ

መተማ

 

መካነ ሰላም

ምድረገነት/አብደራፊ

 

መርሳ

ንፋስ መውጫ

 

ሰቆጣ

ወረታ

 

ሰንበቴ

 

 

 

 

ማስታወሻ

  • በሰማያዊ ቀለም የተለዩት ከተሞች ተጨማሪ የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎት ማስፋፊያ የተደረገባቸው ናቸው። 

ህዳር 14 ቀን 2015 .

ኢትዮ ቴሌኮም

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives