የጨረ ማስታወቂያ ቁጥር 05/2014

ኢትዮ ቴሌኮም ከኩባንያው አገልግሎት የተመለሱ፤ ንቃይ ጣውላዎች፤ የእንጨት ፓሌቶች ፤ ጉማጅ እና አገልግሎት የማይሰጡ የእንጨት ፖሎች፤ የማገዶ እንጨት፤ የኬብል ድራሞች ፤ የእንጨት ማሸጊያ ሳጥኖች፤ አጣናዎች፤ የፓርቲሽን ጣውላዎች፤ ሞራሌ፤ አገልግሎት የማይሰጡ የእንጨት ፖሎች እና ፋይበር ዲሾች፣ ሂት ሽሪንክ፤ ያለቁ የቶነር ካርትሪጆች ፤ የተለያዬ ቁርጥራጭ የኤች ዲ ፒ ደክቶች ኘላስቲኮች እና የተሸከርካሪ ጎማዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ከሰኔ   10 እስከ ሰኔ 27 ቀን 2014 ዓ.ም ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ በሥራ ሰዓት የማይመለስ አንድ መቶ ብር በመክፈል አቃቂ ከሚገኘው የኢትዮ ቴሌኮም ዕቃ ግምጃ ቤት መግዛት የሚችሉ ሲሆን በተጨማሪም በኩባንያችን ድህረገጽ www.ethiotelecom.et/tender እንዲሁም በ www.extratenders.com እና www.afrotender.com ዌብሳይቶች በመከታተልና በቴሌ ብር ክፍያችሁን በመፈጸም በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ ንብረቶቹን ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች መታወቂያ በመያዝ አቃቂ በሚገኘው የኩባንያው ዕቃ ግ/ቤት እንዲሁም አየር ጤና በሚገኘው የኩባንያው ግቢ ውስጥ ማየት ይችላሉ ፡፡

ጨረታው ሰኔ 27 ቀን በ11፡00 ሰዓት ይዘጋል፡፡

ጨረታው ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮ ቴሌኮም አቃቂ ዕ/ግ/ቤት ሰኔ 28 ቀን 2014 ዓ.ም ከረፋዱ 4:30 ላይ ይከፈታል፡፡  

ለተጨማሪ መረጃ አቃቂ ከሚገኘው የኢትዮ ቴሌኮም ዕቃ ግምጃ ቤት ሥራ አስኪያጅ ቢሮ በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይቻላል ፡፡

ኩባንያው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives