ኩባንያችን የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን እውን ለማድረግ የሚያስችሉ ዘርፈ-ብዙ የመሠረተልማት ማስፋፊያ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ይህንን ስትራቴጂ እውን  ለማድረግ ከሚያስፈልጉ አስቻይ ሲስተሞች ውስጥ አንዱ የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ሲሆን፣ ለአካታች የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ከፍተኛ ቁልፍ ሚና ያለው መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት በሀገር አቀፍ ደረጃ እስከ 2018 ዓ.ም ድረስ 90 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች ለማዳረስ በመደረግ ላይ ያለውን መጠነ ሰፊ ጥረት በመደገፍ የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ ለማድረግ የመመዝገቢያ መሳሪያዎችን በመግዛት፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ የአገልግሎት ማዕከላቱን  በመጠቀም እና የሰው ኃይል በማሰልጠን የምዝገባ ስራ በስፋት በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

ኩባንያችን የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ምዝገባ ከማከናወን ባሻገር ደንበኞች የህትመት ጥያቄ/ትእዛዝ በቴሌብር ሱፐርአፕ በኦንላይን በማከናወን እና ክፍያ በመፈጸም እንደምርጫቸው ከዚህ በታች በሰንጠረዥ በተዘረዘሩት በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ 63 የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት/ የካርድ መቀበያ ቦታዎች መታወቂያ ካርዳቸውን መረከብ የሚችሉበትን አሰራር በይፋ አስጀምሯል፡፡  

ይህም አገልግሎት ደህንነቱ አስተማማኝ፣ ደረጃውን የጠበቀ እና ጥራት ያለው ካርድ በቀላሉ ለማቅረብ የሚያስችል ሲሆን ደንበኞች በቴሌብር ሱፐርአፕ ብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ የካርድ ህትመት መተግበሪያ ወይም በድረገጽ https://teleprint.fayda.et/ በመግባት፣ የፋይዳ ተለዋጭ ቁጥር (FAN) በማስገባት፣ በአጭር ጽሑፍ የሚላከውን የማረጋገጫ መለያ ኮድ በማስገባት፣ የአገልግሎት ፍጥነት፣ ካርድ የመረከቢያ ቀን እና ቦታ እንደፍላጎታቸው መምረጥ ይችላሉ፡፡

የአገልግሎት ክፍያን በተመለከተ ደንበኞች በተለያየ የህትመት ማድረሻ ፍጥነት አማራጮች (delivery time) ማለትም ለመደበኛ በ7 የሥራ ቀናት (345 ብር)፣ ለፕሪሚየም በ2 የስራ ቀናት (600 ብር) እና ለኤክስፕረስ አስቸኳይ (800 ብር) በቀላሉ በቴሌብር በመፈጸም አገልግሎቱን ማግኘት የሚችሉ ይሆናል፡፡

የመታወቂያ ህትመቱ አገልግሎቱ ዘመናችን በደረሰበት የመጨረሻ የህትመት ቴክኖሎጂ በላቀ የህትመት ጥራት ደረጃ የሚከናወን ሲሆን፣ በቀላሉ የማይጫጫር፣ ቀለሙ የማይለቅ እና ሳይበላሽ እስከ 10 አመታት የሚደርስ የአገልግሎት እድሜ ያለው ነው፡፡  

የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ አገልግሎቶችን ለዜጎች ለማቅረብ፣ የላቀ የደንበኞች አገልግሎት ተሞክሮን እውን ለማድረግ፣ የሥራ ፈጠራን ለማበረታታት፣ የኢ-ኮሜርስን ግብይት ለማሳለጥ፣ የፋይናንስ አካታችነትን የሚጨምሩ የአነስተኛ ብድር አገልግሎቶችን ያለዋስትና ለማቅረብ፣ የክሬዲት ግብይት ለማስፋፋት፣ የብድር ምጣኔ (credit score) ለማሻሻል እንዲሁም የዜጎችን የአኗኗር ዘይቤ የሚያዘምኑ እና ቢዝነስን የሚያቀላጥፉ የዲጂታል አገልግሎቶችን ለማቅረብ ያስችላል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የዲጂታል መታወቂያ ህትመት አገልግሎት የሚሰጥባቸው ማእከሎቻችን ዝርዝር የሚከተሉት ናቸው፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የዲጂታል መታወቂያ ህትመት አገልግሎት የሚሰጥባቸው ማእከሎቻችን ዝርዝር የሚከተሉት ናቸው፡፡

ተ.ቁየአገልግሎት ማዕከል
1ባምቢስ አገልግሎት ማዕከል
2ጌጃ ሰፈር የአገልግሎት ማዕከል
3ካዛንቺስ አገልግሎት ማዕከል
4ልደታ አገልግሎት ማዕከል
5መስቀል ፈላወር አገልግሎት ማዕከል
6ስታዲየም የሃ ህንፃ አገልግሎት ማዕከል
7ተክለሃይማኖት አገልግሎት ማዕከል
8ቴሌ ጋራጅ
9ውሃልማት አገልግሎት ማዕከል
10አያት አደባባይ አገልግሎት ማዕከል
11አያት ሲኤምሲ-ፀሃይ ሪል እስቴት አገልግሎት ማዕከል
12ቦሌ አራብሳ አገልግሎት ማዕከል
13ቦሌ መድኃኒአለም አገልግሎት ማዕከል
14ቦሌ ሚካኤል አገልግሎት ማዕከል
15ቦሌ ሚሊንየም አገልግሎት ማዕከል
16ቦሌ ኖቪስ ካዝ ሆቴል
17ቦሌ ቴሌ/ ሸገር ህንፃ ፊትለፊት
18ፊጋ የአገልግሎት ማዕከል
19ገርጂ የአገልግሎት ማዕከል
20ሀያሁለት ጐላጉል አገልግሎት ማዕከል
21(መገናኛ አደባባይ) - ደራርቱ ሕንፃ
22ሳሚት 72 የአገልግሎት ማዕከል
234 ኪሎ-ቱሪስት አገልግሎት ማዕከል
246 ኪሎ አገልግሎት ማዕከል
25ፈረንሳይ አገልግሎት ማዕከል
26ጉርድሾላ አገልግሎት ማዕከል
27ኮተቤ መሳለሚያ አገልግሎት ማዕከል
28መገናኛ- አማር ደስታ ህንፃ አገልግሎት ማዕከል
29ሽሮሜዳ አገልግሎት ማዕከል
30ወሰን አገልግሎት ማዕከል
31የካ አባዶ አገልግሎት ማዕከል
32አቃቂ አለም ባንክ አገልግሎት ማዕከል
33አቃቂ በሰቃ አገልግሎት ማዕከል
34አልማዝዬ ሜዳ አገልግሎት ማዕከል
35ቦሌ ቡልቡላ አገልግሎት ማዕከል
36ጎፋ ሶፊያ የገበያ ማዕከል አገልግሎት ማዕከል
37ሃና ማሪያም አገልግሎት ማዕከል
38ቃሊቲ (አቢሲኒያ ባንክ ፊት ለፊት)አገልግሎት ማዕከል
39ቂርቆስ አገልግሎት ማዕከል
40ንፋስ ስልክ አገልግሎት ማዕከል
41ሳሪስ አገልግሎት ማዕከል
42ቱሉ ዲምቱ አገልግሎት ማዕከል
43አለምገና አገልግሎት ማዕከል
44አየርጤና አገልግሎት ማዕከል
45ቤቴል አገልግሎት ማዕከል
46ጀሞ 1 አገልግሎት ማዕከል
47ለቡ ቫርኔሮ አገልግሎት ማዕከል
48ሳርቤት አገልግሎት ማዕከል
49ጦርሃይሎች ቀጠና 2 የአገልግሎት ማዕከል
50ወለቴ አገልግሎት ማዕከል
51አዲሱ ገብያ አገልግሎት ማዕከል
52አራዳ ጊዮርጊስ አገልግሎት ማዕከል
53አሸዋ ሜዳ አገልግሎት ማዕከል
54አስኮ አገልግሎት ማዕከል
55አውቶብስ ተራ አገልግሎት ማዕከል
56ቡራዩ አገልግሎት ማዕከል
57እንቁላል ፋብሪካ - ታደሰ ቸኮል አገልግሎት ማዕከል
58ፋይናንስ ሸጎሌ አገልግሎት ማዕከል
59ቀጨኔ አገልግሎት ማዕከል
60ኮልፌ አገልግሎት ማዕከል
61መርካቶ ምዕራብ አገልግሎት ማዕከል
62መርካቶ ሰባተኛ አገልግሎት ማዕከል
63መሳለሚያ ሸዋ ፀጋ አገልግሎት ማዕከል

                                                          ህዳር 10 ቀን 2017 ዓ.ም

                                                              ኢትዮ ቴሌኮም

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives