ኩባንያችን፣ በራዕዩና በተልዕኮው እንዲሁም በሦስት ዓመት ሊድ (LEAD) የዕድገት ስትራቴጂው ላይ እንደተመለከተው ከኮኔክቲቪቲ አገልግሎት ባሻገር (Beyond Connectivity) መሪ የዲጂታል አገልግሎት አቅራቢ በመሆን የደንበኞቹን የዕለት ተዕለት የቢዝነስ እንቅስቃሴ ለማዘመን እና ለማሳለጥ በሰፊው እየሰራ ሲሆን ከነዚህም ማሳያዎች አንዱ የሆነውን የአዳማ ከተማን ስማርት ሲቲ ፕሮጀክት ተግባራዊ ለማድረግ  የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ በዛሬው ዕለት ከአዳማ ከተማ አስተዳደር ጋር የመግባቢያ ስምምነት ፈጽሟል፡፡

በፕሮጀክቱ የአዳማ አስተዳደር የአይ.ሲ.ቲ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም እና የአገልግሎት ክፍያዎችን በቴሌብር የዲጂታል ክፍያ ስርዓት አማካኝነት በመፈጸም የአፈጻጻም ብቃትን ለመጨመር፣ የመንግስት አገልግሎቶችንም ሆነ የከተማዋ ነዋሪዎችን ህይወት የሚያሻሽል እና የአስተዳደሩን የማስፈጸም አቅም የሚያሳድግ እንዲሁም ከማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ከባቢያዊ ሁኔታዎች አኳያ የነዋሪዎቹን እና የወደፊቱን ትውልድ አጠቃላይ አኗኗር የሚያዘምን እና ከተማዋን ለአልሚ ባለሃብቶች እና ጎብኚ ቱሪስቶች ሳቢ የመዳረሻ ከተማ የሚያደርግ ነው፡፡

በዚህ ስምምነት መሰረት ኢትዮ ቴሌኮም እንደ ሜትሮ ዳርክ ፋይበር (Metro Dark Fiber)፣ ክላውድ አገልግሎት፣ ዳታ ማዕከላት፣ ባለ ከፍተኛ አቅም ባንድዊድዝና ገመድ-አልባ መገናኛ (high bandwidth low latency wireless connectivity)፣ የዲጂታል ክፍያ ስርዓት እና ሌሎች ከመገናኛ ባሻገር /beyond connectivity/ ያሉ የዲጂታል ሶሉሽንስ አገልግሎቶች የኢንፎርሜሽን እና ኮሙንኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT) መሰረተ-ልማቶችን በመዘርጋት የአዳማ ስማርት ሲቲ መርሃግብርን ዕውን የሚያደርግ ይሆናል፡፡

በተጨማሪም ኢትዮ ቴሌኮም የተቀናጀ የቴሌኮም እና የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን መሠረተ ልማትን ከአዳማ ስማርት ከተማ ፕሮግራም ስፋት ጋር በማቀናጀት እና በ4ጂ፣ 5ጂ፣ ኢንተርኔት ኦፍ ቲንግስ NB-IOT /Internet of things/ አማካኝነትና ሌሎችም የመገናኛ መንገዶችን በመጠቀም አስተማማኝ እና ከፍተኛ ጥራት ያለው የገመድ አልባ የመገናኛና ማስተላለፊያ አገልግሎት የሚያቀርብ ይሆናል። ለዚህም ፋይበር ኦፕቲክስ የስማርት ሲቲ የመሠረት ድንጋይ እንደመሆኑ መጠን ኢትዮ ቴሌኮም መሰረተ ልማቱን ወደ መኖሪያ ቤት፣ ሕንጻዎች እና ወደ ተለያዩ አስፈላጊ ቦታዎች በመዘርጋት የኦኘሬሽን ሥራዎችን የሚያከናውን ይሆናል።

እንዲሁም ኢትዮ ቴሌኮም የክላውድና ዳታ ሴንተር አገልግሎቶችን በስማርት ሲቲ ፕሮግራም በማቅረብ እና የከተማ አገልግሎቶችን በክላውድ ሲስተም ተደራሽ በማድረግ በቀላሉ ለማግኘት እንዲቻል እና የማዘጋጃ ቤት አገልግሎቶችን እና ሌሎች የግል አገልግሎቶችን ከቴሌብር ጋር በማቀናጀት የዲጂታል ክፍያ የስማርት ከተማዋ አካል እንዲሆን ተግባራዊ ያደርጋል።

                                               ኢትዮ ቴሌኮም

                                    ጥቅምት 24 ቀን 2015 ዓ.ም

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives