Empowering Enterprises with Smart Solutions!
ኩባንያችን ከኮኔክቲቪቲ አገልግሎት ባሻገር ለህብረተሰባችን ሁለንተናዊ ለውጥና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ትልቅ ትርጉም የሚያመጡ እና የኢትዮጵያን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ለማፋጠን እና የፋይናንሺያል አካታችነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ መጠነ ሰፊ የዲጂታል ሶሉሽኖችን በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡ በተለይም የኢትዮጵያን ዲጂታል ኢኮኖሚ በማሳለጥ የደንበኞቹን የቴክኖሎጂ እና የዲጂታል ፍላጎቶቻቸውን በማሟላት የላቀ ተሞክሮ እንዲኖራቸው ከማስቻል እና አሠራራቸውን ከማዘመን ባሻገር የዲጂታል ኢትዮጵያን ጉዞ በማፋጠን ረገድ ቁልፍ ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡
ኩባንያችን በዛሬው ዕለትም የተቋማት አሰራሮችን ለማዘመን እና ቢዝነሶች ለደንበኞቻቸው የላቀ አገልግሎት በማቅረብ ቀጣይነት ያለው እድገት ለማስመዝገብ የሚያስችሉ በክላውድ ሶሉሽን የታገዙ ሰባት የኢንተርፕራይዝ ሶሉሽኖችን ተግባራዊ ማድረጉን ስናበስር ታላቅ ደስታ ይሰማናል፡፡
የኢንተርፕራይዝ ሶሉሽኖቹ፡–
- ዲጂታል ላይቭስቶክ ትራኪንግ፡ የእንስሳት ምርታማነትን እና የመከታተያ ዘዴዎችን ማሳደግ
- ቴሌ ፑሽ-ቱ-ቶክ/ቪዲዮ፡ እንከን የለሽ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ግንኙነት
- ኮር ባንኪንግ ሶሉሽን፡ የፋይናንሺያል አገልግሎቶችን በክላውድ ላይ ወደ ተመሰረተ ኮር ባንኪንግ ሶሉሽን ማሸጋገር
- የትምህርት አመራር ስርዓት ሶሉሽን፡ የመማሪያ አካባቢዎችን እና አስተዳደርን ማመቻቸት
- የአንድ ቢሮ ትብብር እና ምርታማነት ሶሉሽን- የቡድን ውጤታማነት እና ግንኙነት ማሻሻል
- ቴሌ ኮንታክት ሴንተር፡ የደንበኞችን ተሳትፎ እና የድጋፍ አገልግሎቶችን ማሻሻል
- ኢ.አር.ፒ ሶሉሽኖች- በተቀናጀ የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ ቢዝነሶችን ማጎልበት
እነዚህ በክላውድ የታገዙ የዲጂታል ሶሉሽኖች ድርጅቶች የራሳቸው መሰረተ ልማት መገንባትም ሆነ ቁሳዊ የመረጃ ማዕከል (Physical Data Center) ሳያስፈልጋቸው የኩባንያችንን አስተማማኝ የኢንተርኔት አገልግሎት በመጠቀም ሰርቨሮችን፣ የመረጃ ቋቶችን፣ ሶፍትዌሮችን እንዲሁም ኔትወርኮችንና የዳታ ማከማቻዎችን ማግኘት የሚችሉ ሲሆን፣ ይህም ድርጅቶች ዋንኛ የኦፕሬሽን ስራቸውን በማስተዳደር ላይ ብቻ እንዲያተኩሩ እና ተቋማዊ አቅማቸውን እንዲያጎለብቱ በማድረግ የስራ ፈጠራቸው፣ ተወዳዳሪነታቸው እና ምርታማነታቸው እንዲጨምር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡
ዛሬ በይፋ የተጀመሩት አዳዲስ የኢንተርፕራይዝ ሶሉሽኖች ከዚህ በታች በዝርዝር ቀርበዋል፡-
1. ኢትዮ ቴሌኮም የእንስሳት አያያዝን የሚያዘምን እና የሚገኙበት ቦታ በቀላሉ ለማወቅ የሚያስችል ዲጂታል ላይቭስቶክ ትራኪንግ ሶሉሽን ተግባራዊ አደረገ
Bringing Livestock Management into the Digital Age! Know Where They Are, Know How They Are – Anytime, Anywhere!
በኢትዮጵያ ግንባር ቀደም የቴሌኮም እና ዲጂታል ሶሉሽኖች አቅራቢ የሆነው ኢትዮ ቴሌኮም በላቀ አይ.ኦቲ (IoT) የተደገፈ እና የሀገራችን የእንሰሳት አስተዳደርን ለማዘመን የሚያስችል ዲጂታል የእንሰሳት መከታተያ ሶሉሽን (Digital Cattle Tracking Solution) ተግባራዊ ሲያደርግ ታላቅ ኩራት ይሰማዋል። ይህ ዘመናዊ ሶሉሽን ምርታማነትን ለማሳደግ፣ የእንስሳትን ደህንነት ለማሻሻል በተለይም የእንስሳት ባለቤቶች የፋይናንስ አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ የፋይናንስ ተደራሽነት ክፍተት ለማጥበብ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡
የኢንተርኔት ቁስ (IoT)፣ ክላውድ ቴክኖሎጂን እና የሞባይል ኮኔክቲቪቲን በመጠቀም ይህ አበረታች ኢንሼቲቭ በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ የከፈተ ሲሆን፣ አርሶ አደሮች እና እንሰሳት አርቢዎች በቀላሉ እንስሳቶቻቸውን መከታተል፣ ያሉበትን ቦታ መለየት እና የጤና ሁኔታቸውን መገምገም እንዲችሉ እንዲሁም ውጤታማነትን፣ ደህንነትን እና ኢኮኖሚያዊ እድገትን እንዲያረጋግጡ ከፍተኛ ፋይዳ አለው፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም ባስተዋወቀው የዲጂታል ላይቭስቶክ ትራኪንግ ሶሉሽን አማካኝነት ኢትዮጵያ ወደ ዘመናዊ እና ይበልጥ የቴክኖሎጂ ትስስር ወዳለው ግብርና በመግባት የዲጂታል ኢትዮጵያ ራዕይን እውን በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡በዘርፉ ሲያጋጠሙ የነበሩ ተግዳሮቶችኢትዮጵያ በእንስሳት ብዛት በአፍሪካ ቀዳሚ- 70.3 ሚሊዮን የሚገመቱ የቀንድ ከብቶች፣ 95.4 ሚሊዮን በግና ፍየሎች እንዲሁም 8.1 ሚሊዮን ግመሎች መገኛ ብትሆንም ዘርፉ ለረጅም ጊዜ ከፍተኛ ፈተናዎች/ችግሮች ሲገጥሙት ቆይቷል። እነዚህም ተግዳሮቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ:-
- ቀንድ ከብቶች የት እንዳሉና ለመከታተል ያለው ውስንነት፡– ዘልማዳዊ የእንስሳት መለያ ዘዴ ብዙውን ጊዜ አስተማማኝ ካለመሆኑም በላይ የእንስሳትን ጤናን፣ እንቅስቃሴን እና ባለቤትነትን ለመከታተል አስቸጋሪ ነው፤ ይህም ሁኔታ ለውጤታማ የእንስሳት ሀብት አያያዝ ማነቆ ከመሆኑም ባሻገር እንስሳትን ለበሽታ እና ለስርቆት አደጋ እንዲጋለጡ ያደርጋል፡፡
- የፋይናንስ አቅርቦት እጥረት፡ አርብቶ አደሮችና አርሶ አደሮች የብድርና የኢንሹራንስ አገልግሎት ለማግኘት ለዘመናት ሲቸገሩ እና ሲፍጨረጨሩ ይታያል፡፡ የፋይናንስ ተቋማትም በበኩላቸው የባለቤትነት መብትን ለማረጋገጥ እና የእንስሳትን ዋጋ እና ጤንነትን ለመገምገም አስቸጋሪ ስለሚሆንባቸው የእንስሳትን ሀብት እንደ መያዣ ለመቀበል ያመነታሉ፡፡
· ቀልጣፋ ያልሆነ የመድን ይገባኛል ጥያቄዎች፡– ትክክለኛ የመከታተያ መረጃ አለመኖር ረጅም እና ብዙ ጊዜ አከራካሪ የሆኑ የኢንሹራንስ ይገባኛል ጥያቄዎች ሂደትን ወደ ከፍተኛ የማጭበርበር ይገባኛል ጥያቄዎች ሊያመራ ይችላል።· ዝቅተኛ ምርታማነት፡– የመረጃ ተደራሽነት ውስንነት እና ዘመናዊ የአመራር ዘዴዎች አለመኖር የእንስሳትን ምርታማነት ዝቅተኛ በማድረግ የዘርፉን ዘመናዊ የግብይት ስርዓት እያደናቀፈ ቆይቷል።· ደካማ የኑሮ ደረጃ፡– ከላይ በተጠቀሱት ችግሮች የተነሳ ብዙ አርብቶ አደር ማህበረሰቦች የኑሮ ደረጃቸውን ለማሻሻል ሲቸገሩና ሲጣጣሩ ቆይተዋል። የኢትዮ ቴሌኮም ዲጂታል የእንስሳት መከታተያ ዲጂታል ላይቭስቶክ ትራኪንግ ሶሉሽን (digital cattle tracking solution) በቀጥታ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የእንስሳትን አያያዝ ዘዴን በማቅረብ ከላይ የተዘረዘሩትን ተግዳሮቶች የሚቀርፍ ሲሆን፣ የሚከተሉትን ዲጂታል እንስሳት መከታተያ መሳሪያዎችን ያካተተ ነው።
- የሬዲዮ ፍሪኩዌንሲ መለያዎች/ታግ (RFID Tags): በእንስሳት በጆሮ ላይ የሚገጠሙ መለያዎች አማካኝነት ወሳኝ መረጃዎችን የሚመዘግቡ አነስተኛ የኤሌክትሪክ መሳሪያዎች ልዩ የእንስሳት ዝርዝር መለያዎችን፣ ቀለማቸውን፣ ጾታቸውን፣ የተወለዱበትን ቀንና ዕድሜያቸውን ይመዘግባሉ።
- በጂፒኤስ የታገዙ የራዲዮ ፍሪኩዌንሲ መለያዎች/ታግ (GPS-integrated RFID Tags): የእያንዳንዱን እንስሳት መገኛ ቦታን በቀላሉ ለመከታተል ወይም ለመለየት ያስችላሉ።
- የጂፒኤስ ቺፕሴት (GPS Chipsets)፡ ስለእንስሳቱ ሁለንተናዊ መረጃን መስጠት የሚያስችል ራቅ ባሉ አካባቢዎች ቢጓዙ ወይም ቢጠፉ የት እንደሚገኙ ለማወቅ በቀላሉ ተከታትሎ መረጃ የማቅረብ አቅም ያለው እና ሁለንተናዊ የመረጃ ስብስብ ማለትም RFID፣ GPS እና chipset ቴክኖሎጂን በማጣመር እንደላቀ አማራጭ የሚያገለግል ነው።
ይህ መረጃ ለአጠቃቀም ምቹ በሆነ ፕላትፎርም ከሲስተም ጋር ተቀናጅቶ የተዘጋጀ ሲሆን፣ በድረገጽ በታገዘ የመድን ስርዓት (web-based insurance system) እና ለመስክ ሰራተኞች ወይም የድርጅት ወኪሎች በተዘጋጀ የሞባይል መተግበሪያ ተደራሽ የሚሆን ነው።ቁልፍ ባህሪያት እና ጥቅሞች:· የቁም እንስሳት ቅጽበታዊና የሙሉጊዜ ክትትል፡ አርሶ አደሮችና የሚመለከታቸው አካላት የእንስሳት ሀብታቸው ያሉበት ቦታና ደረጃን በመከታተል የእንስሳት አያያዝን ለማሻሻል እና የሚደርስባቸውን ኪሳራ ለመቀነስ ይችላሉ።· ቀላል/ምቹ ለሆነ የፋይናንሺያል አካታችነት፡– በሶልሽኑ በተረጋገጠ መረጃ በመታገዝ ባንኮች እና የኢንሹራንስ ኩባንያዎች እንስሳቱን እንደ መያዣ በመቀበል የብድር እና የመድን ዋስትና አገልግሎትን ለመስጠት አመኔታ እንዲኖራቸው ያስችላቸዋል።· የተሳለጠ የኢንሹራንስ ይገባኛል ጥያቄ፡– ሶሉሽኑ የኢንሹራንስ ይገባኛል ጥያቄ ሂደቱን ስለሚያቃልል እና ስለሚያፋጥን በካሳ አከፋፈል ረገድ የሚከሰት አለመግባባትን እና ማጭበርበርን ይቀንሳል።· በመረጃ/ዳታ የታገዘ ውሳኔ ለመስጠት፡ የተሰበሰበው መረጃ/ዳታ ለፖሊሲ ቀረጻ እና ሀብት ድልድል ጠቃሚ ዕይታዎችን በመስጠት በእንስሳት ዘርፍ ለዘላቂ ልማት ዕገዛ ያደርጋል።· ከቴሌብር የክፍያ ስርዓት ጋር ትስስር ያለው፡– ከኢትዮ-ቴሌኮም የቴሌብር የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት ጋር ሙሉ ትስስር ስላለው ቀላል፣ምቹና ፈጣን ግብይት እንዲኖር ያስችላል። · በቴሌክላውድ የታገዘ እና በየጊዜው ሊሻሻል የሚችል፡– ኢትዮ ቴሌኮም ይህ ሶሉሽን በቀጣይነት ለወደፊት በየጊዜው ሊሻሻል በሚችል መልኩ በማዘጋጀት ቴክኖሎጂውን ለማቅረብ ችሏል።ይህ ሶሉሽን ለእንስሳት ሀብት ዘርፍ ከፍተኛ እድገት ግስጋሴ ላይ መሆኑን የሚያመላክት ሲሆን፣ የዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም ገበሬዎችን እና ሌሎች እንስሳት አርቢዎችን የሚያበረታታ፣ የእንስሳት እርባታ አያያዝን የሚያዘምን እና የፋይናንስ አካታችነትን የሚያረጋግጥ ነው። ይህ ኢንሼቲቭ የግብርና ዘርፉን ከማዘመን ባሻገር የዲጂታል ትራንስፎርሜሽኑን ጉዞ በማፋጠን በማደግ ላይ ያለውን የሀገራችንን የገጠር ኢኮኖሚ ይበልጥ እንዲጠናከር ያደርጋል።2. ኢትዮ ቴሌኮም ቴሌ ፑሽ-ቱ-ቶክ/ቪዲዮ ሶሉሽን ለድርጅት/ኢንተርፕራይዝ ደንበኞች ይፋ አደረገ!
Empowering Businesses & Operations: Connect, Collaborate, Command!
ኢትዮ ቴሌኮም የተቋማትና ድርጅቶችን ፍላጎት ለማሟላት፣ ፈጣን፣ አስተማማኝ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የቡድን ኮሙኒኬሽን እንዲኖር የሚስችል ቴሌ ፑሽ-ቱ-ቶክ /ቪዲዮ (PTT/PTV) የተሰኘ የቀጣዩ ትውልድ አዲስ የኮሙኒኬሽን ሶሉሽን ሲያቀርብ በታላቅ ኩራት ነው፡፡ ይህ በክላውድ ላይ የተመሰረተ አገልግሎት ነባሩ የሬድዮ ሲስተሞችን በዘመናዊ መንገድ በመተካት በማንኛውም ስማርት ስልክ በኢንተርኔት አማካኝነት የሚሰራ ሲሆን፣ የቡድን ቅልጥፍናን፣ ደህንነትን እና ትብብርን ለማሳደግ በተለይም እንደ ሎጅስቲክስ፣ ደህንነት፣ ትራንስፖርት እና የአደጋ ጊዜ ምላሽ ላሉ ቅጽበታዊ ቅንጅት ለሚሹ ኢንዱስትሪዎች ምቹ የኮሙኒኬሽን አማራጭ ነው፡፡
በቴሌ ፑሽ-ቱ-ቶክ /ቪዲዮ (PTT/PTV) አማካኝነት ኢንተርፕራይዞች ኮሙኒኬሽናቸውን ማቀላጠፍ፣ ስራን ማሳለጥ እንዲሁም ግንኙነቶቻቸውን በማንኛውም ጊዜ እና በማንኛውም ቦታ ቀጣይነት እንዲኖረው ማድረግ ይችላሉ፡፡
ከዚህ ቀደም የነበሩ የሲስተም ተግዳሮቶች፡–
ብዙ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዞች በተለይም በደህንነት፣ በግንባታ፣ በትራንስፖርት እና በእንግዳ ተቀባይነት/ሆስፒታሊቲ ላይ ያሉት ለሀሳብ ልውውጥ በኋላቀር የሬድዮ መገናኛ (two-way radio systems) ላይ ጥገኛ ሆነው የቆዩ ናቸው፡፡ ሆኖም እነዚህ ዘዴዎች ብዙውን ጊዜ ጉልህ ውስንነቶች አላቸው፡፡ ለአብነትም፡-
- የተገደበ አቅም እና ሽፋን፡ የሬድዮ ፊሪኩዌንሲ/ስርጭት ተደራሽነት ውስን ሲሆን፣ የግንኙነት/የኮሙንኬሽን አድማሱ በተወሰኑ አካባቢዎች ብቻ እንዲገደብ ያደርጋል።
- የድምጽ–ብቻ ግንኙነት፡– የቀድሞ የሬድዮ መገናኛዎች በድምፅ ግንኙነት ብቻ የተገደቡ ስለሆነ የጽሑፍ፣ የምስል እና የቪዲዮ ሁለገብ መገናኛዎች ይጎድሉታል።
- የመሣሪያ/ዲቫይስ ጥገኝነት፡ ተጠቃሚዎች ብዙ ጊዜ ግዙፍ፣ አልፎ አልፎ በእጅ የሚያዙ የሬዲዮ መሳሪያዎችን ተሸክመው መንቀሳቀስ ይጠበቅባቸዋል።
- ከፍተኛ ወጪ፡ የሬዲዮ መሳሪያዎችን ለመግዛት፣ ለመጠገን እና ለመተካት ዋጋቸው ከፍተኛ ነው።
- ውስብስብ አቅርቦት፡– ልማዳዊ የሬዲዮ መገናኛዎችን ማዘጋጀት እና ማስተዳደር ጊዜ የሚወስድ እና ልዩ ዕውቀትን የሚጠይቅ ነው።
- የተገደበ የቡድን ግንኙነት/ኮሙንኬሽን (Limited Group Communication)፡ ቡድኖችን ማቋቋም ወይም መቀየር ፈታኝ ነው።
የቴሌ ፑሽ-ቱ-ቶክ ሶሉሽን የሞባይል ኔትወርክን እና የክላውድ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ከላይ የተጠቀሱትን ችግሮችን የሚፈታ ሲሆን፣ በማንኛውም ስማርትፎን ላይ በሚጫን መተግበሪያ አማካኝነት ተደራሽ የሚሆን፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ የተቀናጀ የኮሙንኬሽን ፕላትፎርም አለው፡፡
ቁልፍ ባህሪያት እና ጥቅሞች:
- ፈጣን ቴሌ ፑሽ–ቱ-ቶክ (PTT) እና ፑሽ–ቱ–ቪዲዮ(PTV)፡ አንድን ቁልፍ ብቻ በመንካት/በመጫን ከግለሰቦች ወይም ቡድኖች ጋር ቅጽበታዊ የድምጽ እና የቪዲዮ ግንኙነት ማድረግ ያስችላል።
- የመልቲሚዲያ መልዕክት (Multimedia Messaging)፡ የጽሑፍ መልዕክቶችን፣ ምስሎችን፣ ቪዲዮዎችን እና ፋይሎችን መለዋወጥ ያስችላል።
- በአካባቢ ላይ የተመሰረቱ አገልግሎቶች፡ አስተናባሪዎች እና ተቆጣጣሪዎች ከተጠቃሚዎች እና ቡድኖች ጋር በካርታዎች በመመስረት፣ የማስተባበር ስራን እና የምላሽ ጊዜን ማሻሻል ይችላሉ።
· ጂኦፊንሲንግ እና የፍላጎት ትኩረቶች (Geofencing እና POI)፡ በተጠቃሚዎች አካባቢ ላይ በመመስረት የቡድኖችን፣ ማንቂያዎችንና ማስጠንቀቂያዎችን እንዲፈጥሩ ያስችላቸዋል።· ያሉበትን ሁኔታ ጠቋሚ ማዕከል፡ ተጠቃሚዎች በጉዳዮች እና ክስተቶች ላይ ለአስተናባሪዎች መረጃ እና ወቅታዊ ግንዛቤን በቅጽበት ለመስጠት ያስችላል።· ብልጭ ጥፍት የሚሉ መልእክቶች (Splash Messages)፡ አስፈላጊ ማስታወቂያዎች በመተግበሪያው ላይ እንደ ብልጭ ድርግም የሚሉ መልዕክቶች ሊታዩ እንዲችሉ ስለሚያደርጉ ወሳኝ መረጃ እንዳያመልጥ ይረዳል፡፡· ፑሽ ቱ ቶክ ማእከል (PTT Center)፡ ከብዙ ኮንታክቶች፣ ቡድኖች እና ተጠቃሚዎች ጋር ከማእከል ቋት ጋር ግንኙነቶች እንዲፈጠሩ ያስችላል።· የተማከለ አመራር፡ በዌብ የታገዘ አሠራር ምቹ/ቀላል የሆነ የአገልግሎት አቅርቦትን በመስጠት፣ የመዳረሻ ቁጥጥርን እና የአቅም ድልድል እንዲኖር ያስችላል።· ደህንነቱ የተጠበቀ ተግባቦት/ኮሙንኬሽን፡ ፕላትፎርሙ በቴሌ ክላውድ የሚሰራ ሲሆን አካባቢያዊ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ከጫፍ እስከ ጫፍ የተጠናከረ ኮሙንኬሽን እንዲኖር ያስችላል።· ሊሻሻል የሚችል (Scalability)፡– “እንደ ዕድገት ደረጃ መክፈል” /”pay-as-you-grow” ሞዴል ኢንተርፕራይዞች/ድርጅቶች እንደ አስፈላጊነቱ አጠቃቀማቸውን በቀላሉ እንዲያሳድጉ ያስችላቸዋል።· የኤፒአይ ትስስር፡ ከሌሎች የቢዝነስ መተግበሪያዎች ጋር በቀላሉ ለማስተሳሰር ያስችላል።· የስማርትፎን ተስማሚነት፡– ለራዲዮ መገናኛ የሚስፈልጉ መሣሪያዎችን አስፈላጊነት በማስቀረት ያሉትን ስማርትፎኖች ለመጠቀም ያገለግላል።· በርካታ ፓኬጆች፡– ከተለያየ ወርሃዊ የደንበኝነት ክፍያ ጋር አማራጮችን ለማቅረብ ያስችላል።
ሶሉሽኑ ኋላቀር የመገናኛ ዘዴዎች በከፍተኛ ሁኔታ እንዲሻሻሉ፣ ለኢንተርፕራይዞች የተሻሻለ የቡድን ትብብር፣ ደህንነት እና የተሳለጠ የአሠራር ኃይል፣ ወጪ ቆጣቢ ስርዓት እንዲኖር የሚያስችል ሲሆን የዚህ ቴክኖሎጂ መተግበር እንደ ደህንነት፣ ኮንስትራክሽን፣ ትራንስፖርት፣ ጤና አጠባበቅ እና መስተንግዶ ባሉ ዘርፎች የተሰማሩ ድርጅቶች ቅልጥፍናቸው እና ምላሽ ሰጪነታቸው ፈጣን እንዲሆን ያስችላል።
3. ኢትዮ ቴሌኮም በክላውድ የታገዘ የኮር ባንኪንግ ሶሉሽን ይፋ አደረገ!
Transform your business, ensure compliance, deliver outstanding customer service!
ኢትዮ ቴሌኮም በክላውድ ላይ የተመሰረተ ኮር ባንኪንግ ሶሉሽን የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማትን እና የቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበራትን በዘመናዊ የዲጂታል ፋይናንሺያል መሳሪያዎች ለማስታጠቅ የሚያስችል ሶሉሽን ይፋ ሲያደርግ በታላቅ ኩራት ነው፡፡ይህ ፕላትፎርም ቀልጣፋ፣ አስተማማኝ እና ሊስፋፋ የሚችል የፋይናንሺያል አስተዳደር ሶሉሽኖች ፍላጎትን የሚያሟላ ሲሆን፣ ተቋማቱ አሠራሮቻቸውን ለማቀላጠፍ፣ የደንበኞችን ተሞክሮን ለማሳደግ እንዲሁም የፋይናንስ አካታችነትን ለማረጋገጥ ያስችላል። ውድ የሆኑ መሠረተ ልማቶችን መገንባት ሳያስፈልግ፣ የፋይናንሺያል አገልግሎቶች ተደራሽ ላልሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች እንዲደርሱ በማድረግ አስተማማኝ አገልግሎት ለማቅረብ ያስችላል፡፡ በኢትዮ ቴሌኮም ክላውድ ፓወር ኮር ባንኪንግ ሶሉሽን አማካኝነት፣ የፋይናንስ ተቋማት ስራቸውን ማዘመን፣ ተደራሽነታቸውን ማስፋት እና የባንክ አገልግሎትን በብቃት እና በከፍተኛ በመተማመን ማቅረብ የሚያስችላቸው ይሆናል፡፡በዘርፉ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች፡በርካታ ጥቃቅን እና አነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት እና የቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት በቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት ውስንነት ባለበት ሁኔታ ስለሚንቀሳቀሱ ከፍተኛ ተግዳሮቶች ይስተዋልባቸዋል። እነርሱም፡-§ የአሠራር ቅልጥፍናዎች ማነስ፡ ለደንበኛ ምዝገባ፣ አካውንት አስተዳደር፣ የብድር ሂደት እና ሪፖርት የማውጣት ሂደቶች ጊዜ የሚወስዱ እና በማኑዋል አሰራር ላይ የተመሰረቱ በመሆናቸው ለስህተቶች የተጋለጡ ናቸው።§ ቅጽበታዊ የሆነ መረጃ እጥረት፣ ብዙ ተቋማት የቅጽበታዊ ግብይት ዕድል ልየታ፣ ክትትል እና ሪፖርት አደራረግ ዘዴ ስለሌላቸው በውጤታማ ውሳኔ አሰጣጥ ላይ እንቅፋት እየፈጠረባቸው ይገኛል። § የዳታ አያያዝ ችግሮች፡– ከፍተኛ መጠን ያለው የደንበኛ መረጃን/ዳታን በእጅ በመያዝ ወይም ጊዜ ያለፈባቸውን ዘዴ መጠቀም ፈታኝ እና ለስህተቶች የማጋለጥ እድሉ እና የዳታ መጥፋት አደጋን ይጨምራል§ ወጥ ያልሆነ የደንበኛ ተሞክሮ፡ በተለያዩ ቅርንጫፎች ወይም የአገልግሎት ማእከላት የአገልግሎት ደረጃዎች መለዋወጥ የደንበኞችን እርካታ ማጣት ያስከትላል።§ የማጭበርበር እና የሕግ ተገዢነት አለመኖር ስጋቶች፡– በእጅ የሚሰሩ ሥርዓቶች ለማጭበርበር የበለጠ ተጋላጭ ከመሆናቸውም በተጨማሪ የቁጥጥር/ሬጉላቶሪ መስፈርቶችን ለማክበር አስቸጋሪ ያደርጉታል። § ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ወጪዎች፡ የኮር ባንክ አሰራርን በባለቤትነት ማዘጋጀት እና ዘላቂ ማድረግ ውድ ከመሆኑም ባሻገር ልዩ የአይቲ እውቀትን ይጠይቃል።§ በእጅ የሚፈጸም ክፍያ፡– በጥሬ ገንዘብ፣ በቼኮች ወይም በባንክ የሚደረግ የገንዘብ ማስተላለፍ ስራ አስተማማኝ ያልሆነ፣ አዝጋሚ እና የማይመች ነው።በመሆኑም በክላውድ የታገዘ ባንኪንግ ሶሉሽን የተጠቀሱትን ተግዳሮቶች በቀጥታ ለመቅረፍ እና ለጥቃቅን እና አነስተኛ ፋይናንስ ተቋማት እና ቁጠባ እና ብድር ህብረት ስራ ማህበራት ደህንነቱ የተጠበቀ አሠራር በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።ቁልፍ ባህሪያት እና ጥቅሞች፡§ የተሳለጡ አሰራሮች፡ የደንበኛ ምዝገባን፣ የሂሳብ አያያዝን፣ የብድር አሰጣጥ ሂደትን እና ሪፖርት አደራረግን ጨምሮ ቁልፍ የአሠራር ሂደቶችን አውቶሜት በማድረግ ወይም በማዘመን ስህተቶችን ይቀንሳል።§ የአሁናዊ/ቅጽበታዊ ግብይት መከታተያ፡– ወቅታዊና ፈጣን የግብይት ዳታ ተደራሽነትን በማረጋገጥ የተሻለ ክትትል እና ቁጥጥር ለማድረግ እና ውሳኔ ለመስጠት ያስችላል።§ የተሻለ የደንበኛ ተሞክሮ፡ ለአባላት የሞባይል መተግበሪያን ጨምሮ በሁሉም የአገልግሎት ቻናሎች ላይ ተከታታይ እና ለተጠቃሚ ምቹ የሆነ ተሞክሮ ለማቅረብ ያስችላል።§ ለተሻለ የዳታ አስተዳደር፡ ከፍተኛ መጠን ያለው የደንበኛ ዳታን በአስተማማኝ ሁኔታ በማከማቸትና በማስተዳደር ረገድ የዳታ ተዓማኒነትን እና ተደራሽነትን ያረጋግጣል።§ ማጭበርበርን ለመከላከል እና የሕግ ተገዢነትን ለማስፈን፡– የማጭበርበር ድርጊቶችን ለመለየት እና ለመከላከል የሚያስችሉ ገጽታን በማካተት ተቋማት የቁጥጥር መስፈርቶችን እንዲያሟሉ ይረዳቸዋል።§ ወጪ ቆጣቢነት፡– በክላውድ የታገዘ ሞዴል በሃርድዌር እና በሶፍትዌር ላይ የሚወጣውን ከፍተኛ የሆነ የመዋዕለ ንዋይ ፍሰትን በግልጽ የሚያስቀር በመሆኑ አጠቃላይ የባለቤትነት ወጪ እንዲቀንሰ ያደርጋል።
- የሚጎለብት/ሊሻሻል የሚችል (Scalability)፡ ከዕድገት ደረጃቸው ጋር የሚፈጸም የክፍያ ሞዴል ተቋማት ፍላጎታቸው እያደገ ሲመጣ የአጠቃቀም ፍጆታቸውንም በቀላሉ እንዲያሳድጉ ያስችላቸዋል።
§ የቴሌብር ትስስር፡– ያለምንም እንከን ከቴሌብር ጋር በማስተሳሰር ለብድር አሰጣጥ ፣ለክፍያ አገልግሎት እና ለቁጠባ ምቹ እና አስተማማኝ የሞባይል ክፍያ ዘዴን መጠቀም ያስችላል።§ ሁለንተናዊ ሞጁሎች፡ የምዝገባ፣ የምርት ዝግጅት፣ የብድር አስተዳደር፣ የሒሣብ ሠንጠረዥ (Chart of Accounts) የአሁናዊ/ቅጽበታዊ የዳሽቦርድ ሪፖርት እና ክፍያዎችን ጨምሮ የተለያዩ ኮር/አብይ ሞጁሎችን ለማቅረብ ያስችላል።§ የሞባይል መተግበሪያ፡– አባላት ሂሳባቸውን እንዲመለከቱ፣ ገንዘባቸውን እንዲያስተላልፉ፣ ብድር እንዲጠይቁ እና ክፍያ እንዲፈጽሙ የሚያስችል ምቹ አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላቸዋል።የኢትዮ ቴሌኮም የኮር ባንኪንግ ሶሉሽን በኢትዮጵያ ለፋይናንሱ ዘርፍ በተለይም በጥቃቅን እና አነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት እና ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበራት ዘመናዊ አሰራር ሂደት ውስጥ ትልቅ እድገት ላይ መድረሱን ያመላክታል። ይህ ኮር ባንኪንግ ሶሉሽን አስተማማኝ፣ ቀልጣፋ እና ተደራሽ በማቅረብ ተቋማት አባላቶቻቸውን ወይም ደንበኞቻቸውን በተሻለ መንገድ እንዲያገለግሉ፣ የፋይናንሺያል አካታችነትን እንዲያረጋግጡ እና ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ እድገት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ በማድረጉ ረገድ ከፍተኛ ጥቅም ይሰጣል።
- ኢትዮ ቴሌኮም ትምህርት ቤቶችን የሚያዘምን የትምህርት አስተዳደር ሥርዓትን ይፋ አደረገ
Empowering Education: From Enrollment to Excellence—One System for Every Need!
ኢትዮ ቴሌኮም ሁሉን አቀፍ፣ በክላውድ የተደገፈ፣ የትምህርት ቤት ስራዎችን ለማቀላጠፍ፣ ኮሙኒኬሽኖችን ለማጎልበት እና የትምህርት ማኔጅመንት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችል የቀጣይ ትውልድ የትምህርት ማኔጅመንት ሲስተምን ሲያቀርብ በኩራት ነው፡፡
ይህ ዘመናዊ ሲስተም በየደረጃው ከሚገኙ የትምህርት ተቋማት ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀምሮ እስከ ዩኒቨርሲቲ ድረስ የሚያጋጥሙ የረዥም ጊዜ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የተማከለ፣ ምዝገባ ለማከናወን ምቹ የሆነ፣ የአካዳሚክ፣ የአስተዳደር እና የተማሪዎችን ተሳትፎ በቀላሉ ለማስተዳደር የሚያስችል ነው፡፡
የት/ቤት አስተዳደርን፣ አስተማሪዎችን፣ ተማሪዎችን እና ወላጆችን በዲጂታል ስነ-ምህዳር ማስተሳሰር፣ ቅልጥፍናን ለማምጣት፣ ግልጽነትን ለማረጋገጥ እና ትብብርን ለማጎልበት እንዲሁም ተቋማት አስፈላጊ በሆኑት ጉዳዮች ላይ እንዲያተኩሩ በማድረግ ጥራት ያለው ትምህርት እንዲያቀርቡ እና የተማሪዎቻቸውን ስኬት ይበልጥ እንዲያሳድጉ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡
ቁልፍ ባህሪያት እና ጥቅሞች
- ለት/ቤት አስተዳደር እና መምህራን፡–
- የአስተዳደር ቅልጥፍናን ለማሻሻል፡ እንደ ምዝገባ፣ መዝገብ መያዝ እና ሪፖርት ማድረግ፣ ጊዜን መቆጠብ እና ስህተቶችን መቀነስ ያሉ ተግባራትን ለማዘመን/አውቶሜት ለማድረግ፣
- የላቀ የዳታ አስተዳደር፡ ሁሉንም የትምህርት ቤት ዳታ/መረጃዎች በአንድ ማዕከል በማድረግ አጠቃላይ የተሻለ የሥራ ግንዛቤ ወይም እይታን ለመስጠት፣
- የተሻሻለ ኮሙኒኬሽን፡ ከተማሪዎች እና ከወላጆች ጋር የተሻለ ተግባቦት/ኮሙኒኬሽን ለመፍጠር፣
- የተሳለጠ የፋይናንስ አስተዳደር፡ ክፍያ መሰብሰብን፣ በጀት ማውጣትን እና የሂሳብ አያያዝን ለማቅለል፣
- ወጪ ቆጣቢ እና ሊስፋፋ የሚችል፡ በክላውድ ላይ የተመሰረተ ሞዴል የአይ.ቲ ወጪን ይቀንሳል እንዲሁም በቀላሉ ለማስፋፋት/ለማሳደግ ያስችላል፣
- የጊዜ ሰሌዳን ለማስተዳደር፡ የክፍል የትምህርት መርሐ ግብርን በቀላሉ ለመንደፍ፣
- ሀብትን ለማስተዳደር፡ ይህም የሰው ኃይል፣ ቤተ መፃህፍት እና የእቃ ግምጃ ቤት መሳሪያዎችን ያካትታል፣
- ለተማሪዎች፡-
- እንከን የለሽ የመረጃ ተደራሽነት፡ የፈተና ውጤት፣ አሳይመንት፣ የትምህርት የጊዜ ሰሌዳ እና የትምህርት ቤት ማስታወቂያዎችን በቀላሉ ለማግኘት፣
- ተግባቦትን ለማሻሻል፡ በአስተማሪዎችና ተማሪዎች መካከል የተሻለ ተግባቦት እንዲኖር፣
- ግላዊ ትምህርት፡ ለግል የተዘጋጀ ትምህርትን በዳታ/በመረጃ ላይ በመመስረት እይታዎችን ይደግፋል፣
- ተሳትፎን ለመጨመር፡ የበለጠ አሳታፊ እና መስተጋብር ያለው የመማሪያ አካባቢን ይፈጥራል፣
- ለወላጆች፡-
- የተሻሻለ እይታ፡ የልጆቻቸውን የትምህርት ለውጥ፣ ት/ቤት መገኘት እና የት/ቤት ኮሙኒኬሽኖችን በተፈለገው ቅጽበት ለማግኘት፣
- እንከን የለሽ ኮሙኒኬሽን፡ ከመምህራን እና ከትምህርት ቤት አስተዳዳሪዎች ጋር ቀላልና መልካም ተግባቦት እንዲኖር ለማስቻል፣
- ለክፍያ ያለው ምቹነት፡ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ምቹ የሆነውን ቴሌብርን በመጠቀም የት/ቤት ክፍያዎችን በየትኛውም ቦታ ሆነው ለመክፈል ያስችላል፣
- ተሳትፎን መጨመር፡ ወላጆች በልጆቻቸው ትምህርት ላይ የላቀ ተሳትፎን እንዲኖራቸው ያሳድጋል።
- አጠቃላይ ሞጁሎች፡ የትምህርት አስተዳደር ሲስተሙ (EMS) ለተማሪ ማኔጅመንት፣ ለሰው ኃይል አስተዳደር፣ ለፋይናንስ አስተዳደር፣ ለቤተ መፃህፍት አስተዳደር፣ እቃ ግምጃ ቤት አስተዳደር፣ ለኮሙኒኬሽን እና ማስታወቂያ፣ ለአካዳሚክ አስተዳደር፣ ለጊዜ ሰሌዳ አስተዳደር፣ ሪፖርት ለማድረግ፣ ለተጠቃሚ መለያ አስተዳደር እና ለተማሪ እና ወላጅ የተዘጋጀ ፖርታል ሞጁሎችን ያካትታል።
- ከቴሌብር ጋር ያለው ትስስር፡ ሲስተሙ ከቴሌብር ጋር ያለው የተሳሰረ በመሆኑ ለትምህርት ቤት ክፍያ ምቹ እና አስተማማኝ ሲሆን፣ በኢትዮ ቴሌኮም ቴሌክላውድ የተደገፈ ነው፡፡
የትምህርት አስተዳደር ሲስተሙ የትምህርት ዘርፍ ለማዘመን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያለው ሲሆን፣ በተለይም ሁሉን አቀፍ፣ ለተጠቃሚ ምቹ እና ተመጣጣኝ መፍትሄ በማቅረብ፣ የትምህርት አስተዳደር ሲስተሙ ትምህርት ቤቶች ቅልጥፍና ያለው አገልግሎት እንዲያቀርቡ፣ ኮሙኒኬሽናቸውን እንዲያሳድጉ እንዲሁም ለተማሪዎች የተሻለ የትምህርት አሰጣጥ እንዲጎለብቱ ያስችላቸዋል። ከዚህም ባሻገር የወላጆችን ተሳትፎ በማጎልበት እና መረጃን በቀላሉ ለማግኘት እንዲሁም የክፍያ አማራጮችን ምቹ ለማድረግ ከፍተኛ ፋይዳ አለው፡፡
በተጨማሪም ኩባንያችን በዛሬው እለት አሰራርን የሚያዘምኑ፣ የቡድን ስራን የሚያጠናክሩ እንዲሁም የቢዝነሶችን ምርታማነት የሚጨምሩ በክላውድ ላይ የተመሰረቱ ሦስት ሶሉሽኖችን ይፋ አድርጓል።
- የአንድ-ቢሮ ትብብር እና ምርታማነት ሶሉሽን
Work Smarter, Collaborate Better, Achieve More!
ኩባንያችን የቢዝነስ ሥራዎችን ለማቀላጠፍ፣ የቡድን ስራን ለማጎልበትና ለማዘመን እንዲሁም የሥራ ጥራትን እና ቅልጥፍናን ለማምጣት የሚያስችል ሁለገብ የሆነ የዲጂታል ፕላትፎርም – የአንድ ቢሮ ትብብር እና ምርታማነት ሶሉሽን ተግባራዊ ማድረጉን ስንገልጽ ታላቅ ኩራት ይሰማናል፡፡
ይህ ቁልፍ ሶሉሽን በርካታ የስራ ፍሰቶችን ወደ አንድ በማምጣት ደህንነቱ የተጠበቀ ክላውድን መሰረት ካደረገ ስነ-ምህዳር ጋር የተሳሰረ ሲሆን፣ ይህም በማንኛውም ጊዜ፣ ቦታ እና በመሳሪያዎች ላይ እንከን የለሽ ትብብርን ለማድረግ ያስችላል። በተጨማሪም በማንኛውም ጊዜ የጋራ ሀብቶችን፣ አውቶሜት የሆኑ ፕሮሰሶችን እንዲሁም ሊታወቁ የሚችሉ የኮሙኒኬሽን መሳሪያዎችን በማግኘት ቡድኖች ስራዎቻቸውን በተደራጀ መንገድ እንዲከውኑ እንዲሁም የውሳኔ አሰጣጥን ለማፋጠን ትልቅ ሚና ይጫወታል፡፡
የአንድ ቢሮ ትብብር ሶሉሽን ለኢንተርፕራይዞች ወሳኝ ሚና የሚጫወት ሲሆን፣ በተለይም፡-
- የቡድን ትብብር እና ቅልጥፍናን ለማሳደግ፣
- የቢዝነስ ፕሮሰሶችን አንድ እና አውቶሜት ለማድረግ፣
- ተግባቦትን እና የቡድን ስራን ለማላቅ፣
- የስራ ሂደቶችን ለማዘመን እና ውሳኔ አሰጣጥን ለማፋጠን፣
- ምርታማነትን እና የሰራተኞችን ተሳትፎ ለማሳደግ፣
- ደህንነቱ የተጠበቀ እና እንከን የለሽ የዳታ አስተዳደርን ለማረጋገጥ የሚሉት ናቸው፡፡
የቢዝነስ ሥራዎችን የሚያከናውኑበትን መንገድ በመለወጥ ረገድ፣ ይህ ሶሉሽን ድርጅቶች በአነስተኛ ጥረት የበለጠ ስኬታማ እንዲሆኑ፣ እድገታቸው እንዲጨምር እንዲሁም ፈጠራ እንዲጎለብትና እና ይህን የዲጂታል ዘመን በመጠቀም ስኬታማ እንዲሆኑ የላቀ አስተዋጽኦ አለው፡፡
- በክላውድ ላይ የተመሰረተ የጥሪ ማዕከል (Cloud-based Contact Center)
Deliver Exceptional Customer Service with our All-in-One, Cloud-Powered Contact Center
ኢትዮ ቴሌኮም የቢዝነሶችን የደንበኞች ግንኙነት የሚቀይር፣ በክላውድ ላይ የተመሰረተ እና እጅግ ዘመናዊ ቴሌ የጥሪ ማዕከልን ፕላትፎርም ይፋ ሲያደርግ ደስታ ይሰማዋል። ይህ ዘመናዊ ሶሉሽን የተለያዩ ቻናሎችን ማለትም የድምጽ ጥሪዎችን፣ የጽሑፍ መልዕክቶችን እና ማህበራዊ ሚዲያዎችን በአንድ ወጥ ሲስተም ማቀናጀት ያስችላል። ሶሉሽኑ የድርጅት ደንበኞችን በዘመናዊ መሳሪያዎች እና በተቀላጠፉ የስራ ሂደቶች በመታገዝ የላቀ የደንበኞች አገልግሎት እንዲሰጡ፣ የስራ ቅልጥፍናን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያሻሽሉ እና አስተዳደራዊ ወጪዎችን እንዲቀንሱ ያስችላል።
የቀድሞ ሲስተሞች ተግዳሮቶች፡
- ዝቅተኛ የደንበኛ ተሳትፎ፡ ወጥነት የሌለው አገልግሎት ወደ ቅሬታ ያመራል።
- ውጤታማ ያልሆነ የቅሬታ አያያዝ፡ በእጅ የሚሰሩ ሂደቶች የመፍትሄ አሰጣጥ ፍጥነትን መገደባቸው።
- ውስን የሁሉን-ዓቀፍ ቻናል፡ የቀድሞ ሲስተሞች ወጥነት እና የባለብዙ ቻናል መስተንግዶ ማቅረብ አለመቻል።
- ዘገምተኛ ውሳኔ አሰጣጥ፡ የፈጣን/ቀጥታ መረጃ እጦት ፈጣን ውሳኔዎችን ለመወሰን አለማስቻል።
- ከፍተኛ ኢንቨስትመንት፡ በሃርድዌር እና በጥገና ላይ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ የሚጠይቅ መሆኑ።
- ረጅም የማበልጸጊያ ጊዜ፡ የቀድሞ ሲሰተሞችን ለማበልጸግ ረጅም ጊዜ የሚፈልጉ መሆናቸው።
- ከፍተኛ የኦፕሬሽን ወጪ፡ ከፍተኛ የጥገና እና የሰው ኃይል ወጪዎችን የሚፈልጉ መሆናቸው፡፡
- በፕሮፌሽናሎች ላይ ጥገኛ መሆን፡ ስርዓቶችን ለማስተዳደር ብዙ ጊዜ የአይቲ ፕሮፌሽን ክህሎቶች አስፈላጊ መሆናቸው ይገኙበታል።
የቴሌ የጥሪ ማዕከል ቁልፍ ጥቅሞች እና ባህሪያት:
አዲሱ የኢትዮ ቴሌኮም የጥሪ ማዕከል የተዘረዘሩትን ተግዳሮቶች በሚከተሉት ገጽታዎች ይፈታል፡
- የሁሉን–አቀፍ ቻናል፡ሁሉንም ግንኙነቶች (ድምጽ፣ ጽሑፍ፣ ማህበራዊ ሚዲያ) ከአንድ መድረክ ላይ ያለምንም እንከን ለማስተዳደር ያስችላል።
- የአሰራር ቅልጥፍና፡የስራ ሂደቶችን ለማቀላጠፍ እና ለተሻለ የደንበኞች ጥያቄ አያያዝ በአውቶሜሽን ለማከናወን ያስችላል።
- የላቀ የደንበኛ ተሞክሮ፡ፈጣን፣ ወጥነት ያለው እና ፍላጎትን መሰረት ያደረገ አገልግሎት በመስጠት እርካታን ለማሳደግ ያስችላል።
- አቅሙን ለማስተካከል መቻሉ/Scalable ፡ለወጪ ቁጠባ ፍላጎትን መሰረት ባደረገ መልክ አቅሙን እና ገጽታዎችን በማለዋወጥ መጠቀም ያስችላል።
- የኦፕሬሽን አስተዳደር አለመኖር፡ኢትዮ ቴሌኮም የቴክኒክ ጉዳዮችን የሚያስተዳድር በመሆኑ ቢዝነሶች በዋና ስራቸው ላይ ማተኮር ይችላሉ፡፡
- በቴሌክላውድ የተመሰረተ:በኢትዮ ቴሌኮም አስተማማኝ ክላውድ መሠረተ ልማት ላይ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ እንደፍላጎት ሊስተካከል የሚችል መፍትሄ ያቀርባል።
- የባለሙያ ድጋፍ፡ከኢትዮ ቴሌኮም ባለሙያዎች ቀጣይነት ያለው ስልጠና እና ሙያዊ እገዛ ማግኘት ይችላሉ።
- ፈጣን ትግበራ ፡በፈጣን የሲስተም ትግበራ በቀላሉ ወደ ሥራ ለመግባት ያስችላል።
ቴሌ የጥሪ ማዕከል አገልግሎታቸውን ለማሳደግ ለሚፈልጉ ቢዝነሶች የላቀ፣ ወጪ ቆጣቢ እና ተመጣጣኝ ሶሉሽን የሚያቀርብ በመሆኑ ድርጅቶች ሶሉሽኑን በመጠቀም የደንበኞቻቸውን ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ በማሳደግ ዘላቂ የቢዝነስ እድገት ማስመዝገብ ይችላሉ።
- በክላውድ ላይ የተመሰረተ የኢ.አር.ፒ ሶሉሽን
Empower your Business with Smart ERP: Streamline Operations, Boost Productivity, Drive growth
ኢትዮ ቴሌኮም በክላውድ ላይ የተመሰረተ የኢ.አር.ፒ (ኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ) ሶሉሽን ይፋ ማድረጉን በደስታ ይገልጻል፡፡ ይህም የድርጅት ደንበኞች አሰራራቸውን እንዲያቀላጥፉ፣ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደታቸውን እንዲያሻሽሉ እና ዘላቂ ዕድገት እንዲያስመዘግቡ የሚያስችል ነው። ይህ የተቀናጀ ፕላትፎርም ቁልፍ የሆኑ ተግባራትን – ከፋይናንስ እና ከሰው ኃይል አስተዳደር እስከ አቅርቦት ሰንሰለት እና ከደንበኛ ግንኙነት አስተዳደር – በአንድ ወጥ ስርዓት በማቀናጀት ደህንነቱ አስተማማኝ በሆነው የቴሌክላውድ ላይ ለማግኘት ያስችላል። ይህም የቢዝነስን ተደራሽነት ከመጨመር ባሻገር እንደአስፈላጊነቱ አቅሙን ለማሳደግ እና ወጪ ለመቆጠብ ያስችላል።
ቢዝነሶች የሚያጋጥሟቸው ተግዳሮቶች፡
- ያልተቀናጁ መተግበሪያዎች: የተበታተነ መረጃ ስለ ቢዝነሱ አጠቃላይ እይታ እንዳይኖር ያደርጋል።
- ኋላቀር የሥራ ሂደቶች፡ በማኑዋል መስራት ለስህተት እና ለምርታማነት መቀነስ ይዳርጋል።
- ውስን መስተጋብር/ Limited Interoperability: በሲስተሞች መካከል ያለው የመቀናጀት እጥረት ትብብርን ያደናቅፋል።
- ዘገምተኛ ውሳኔ አሰጣጥ: ፈጣን መረጃ ማግኘት ስለማይቻል የውሳኔ አሰጣጥን ያወሳስባል።
- ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ወጪዎች፡ ኋላቀር ሲስተሞች በሃርድዌር እና በአይቲ ባለሙያዎች ላይ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ይፈልጋሉ።
- የተገደበ የመጠን ማስተካከል ችሎታ፡ ከሚለዋወጡ የቢዝነስ ፍላጎቶች ጋር የሚጣጣም አቅምን ለማስተካከል አያስችሉም።
- የተራዘመ የማበልጸጊያ ጊዜ: የሲስተሞች አተገባበር ሂደቶች ረጅም እና ውስብስብ ሊሆኑ ይችላሉ።
- ከፍተኛ የጥገና ወጪዎች: ቀጣይነት ያለው የሶፍትዌር እና የኦፕሬሽን ወጪዎች ከፍተኛ መሆን
- በፕሮፌሽናሎች ላይ ጥገኛ መሆን፡ የኢ.አር.ፒ ሲስተሞችን ማስተዳደር ብዙ ጊዜ ልዩ የአይቲ ክህሎቶችን ይጠይቃል።
የኢትዮ ቴሌኮም ኢ.አር.ፒ ቁልፍ ባህሪያት እና ጥቅሞች፡
- የተቀናጁ የሥራ ሂደቶች፡ በሁሉም የሥራ ክፍሎች ውስጥ ቁልፍ ሂደቶችን ማቀላጠፍ እና አውቶሜት ማድረግ ያስችላሉ።
- የላቀ የደንበኞች አገልግሎት፡ አገልግሎቶችን ለደንበኞች እንደፍላጎታቸው በማዘጋጀት በማቅረብ ተሞክሮን ያሳድጋል።
- ለትግበራ ፈጣን መሆን፡ ፈጣን ትግበራን በማመቻቸት የአሰራር ቅልጥፍናን ያሻሽላል።
- ምርታማነትን መጨመር፡ ለፈጣን የውሳኔ አሰጣጥ ትክክለኛ ዳታ ለማግኘት ያስችላል።
- የወጪ ቆጣቢነት፡ እጅግ ውድ ከሆነ (on-premises) የአይቲ መሠረተ ልማት ግንባታ ወጭ ያድናል።
- ሊያድግ የሚችል ሞዴል፡ እንደ ቢዝነስ ዕድገት ፍላጎት ተጨማሪ አቅምን በማግኘት ለሚጠቀሙት አገልግሎት ብቻ ክፍያ መፈጸም ያስችላል።
- በቴሌክላውድ የሚስተናገድ፡ ደንበኞች በኢትዮ ቴሌኮም አስተማማኝ ክላውድ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ መፍትሄ ማግኘት ይችላሉ።
- የባለሙያ ድጋፍ፡ ከኢትዮ ቴሌኮም የባለሙያዎች ቡድን ቀጣይነት ያለው ስልጠና እና ሙያዊ እገዛ ማግኘት ያስችላል።
በአጠቃላይ፣ የኢትዮ ቴሌኮም ቢዝነሶች ያለግዙፍ ኢንቨስትመንት በቀላሉ በኢ.አር.ፒ ሶሉሽን አሰራራቸውን እንዲያሻሽሉ እና እድገት እንዲያስመዘግቡ የሚያስችል ወጭ ቆጣቢ ዘመናዊ አማራጭ አቅርቧል።
ኩባንያችን እስካሁን ከ456 በላይ የድርጅት ደንበኞችንና አጋሮችን በቴሌ ክላውድና በዳታ ማዕከል አገልግሎቶቻችን ውጤታማ እንዲሆኑ ያደረገ ሲሆን ባንኮችና አነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት የተቀናጀ ፕላትፎርም ያለው እና በሰውሰራሽ አስተውሎት (AI) የተደገፈ የማርኬት ፕሌስ ሶሉሽን አቅርበንላቸዋል። ይህም የድርጅት ደንበኞቻችን በዋና ሥራቸው ላይ በማተኮር አገልግሎታቸውን በትኩረት ለበርካታ ደንበኞች ተደራሽ እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል።
በመጨረሻም ኩባንያችን ዘርፈ ብዙ ቴክኖሎጂዎችን እና የዲጂታል ሶሉሽኖችን ለድርጅት ደንበኞች በስፋት ተደራሽ በማድረግ የአገልግሎት አሰጣጣቸውን በማዘመን ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ለማህበረሰባችን የዕለት ከዕለት የኑሮ እንቅስቃሴ መሻሻል እና የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ እንዲሁም የተቋማትን አሰራር በማላቅ ምርታማነትን እንዲያሳድጉ አስቻይ ሶሉሽኖችን በማቅረብ የሀገራችን ዘላቂ ልማትን እና ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማፋጠን እያከናወናቸው የሚገኙ ስራዎችን በቁርጠኝነት አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
የካቲት 19 ቀን 2017 ዓ.ም
ኢትዮ ቴሌኮም