ያገለገሉ ፈርኒቸሮች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምሥራቅ ሪጅን በሞጆ ከተማ ቴሌ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ያገለገሉ ፈርኒቸሮችን ግዢ ፍላጎቱ ላላቸው ድርጅቶች ግለሰቦች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ግለሰብ/ድርጅት የጨረታ ሰነድ ለመግዛት በሚመጡበት ወቅት ድርጅት ከሆነ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ ግለሰብ ከሆነ የታደሰ መታወቂያ ወይም ማንነታቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ዋናውን እና ኮፒ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
1. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ከጥር 27 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ከሰኞ እስከ ዓርብ በሥራ ሰዓት አዳማ ከተማ ኦሮሚያ ልማት ማህበር ሕንፃ 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመሥሪያ ቤቱ ሶርሲንግ ክፍል በመቅረብ ስለጨረታው መረጃ ማግኘትና የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡
2. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ውጤቱ እንደታወቀ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ከታወቀ ባንክ ተረጋግጦ በሚቀርብ ዋስትና (CPO) ለተጠቀሱት ላገለገሉ ዕቃዎች የሚያቀርቡትን ጠቅለላ ዋጋ የሚጫረቱበትን ዋጋ/ 5% /አምስት ከመቶ/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
3. የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከገዙበት አድራሻ የበር መግቢያ ፍቃድ በመውሰድ እና የታደሰ መታወቂያ በመያዝ ጨረታው አየር ላይ እስከሚቆይበት ዕለት ድረስ ዕቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ ማየት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የተጠቀሱት ያገለገሉ ዕቃዎች የሚገዙበትን ዋጋ ተ.እታ (VAT) ጨምረው በዋጋ ማስገቢያ ቅጽ ላይ በማካተት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውን እና የጨረታውን ቁጥር በመጥቀስ በኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምሥራቅ ሪጅን ጽ/ቤት፣ አዳማ ከተማ ኦሮሚያ ልማት ማህበር ሕንፃ 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመሥሪያ ቤቱ ሶርሲንግ ክፍል እስከ የካቲት 13 ቀን 2016 ዓ.ም 5፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሰነዱን ባስገቡበት አድራሻ 7ኛ ፎቅ በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ በዕለቱ የካቲት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
6. ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ያለው ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡ መሥሪያ ቤተ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 022-111-0994/022-111-3550 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ኤትዮ ቴሌኮም
ደቡብ ምሥራቅ ሪጅን