ጨረታው የሚጀምርበት ቀን: መጋቢት 08 2013 ዓ.ም
የጨረታ ቁጥር ሰ/ም/ሪ/ዘ/ሰ/ማ/0005/2013
በሰ/ም/ሪጅን ኢትዮ ቴሌኮም ደሴ የሚገኘውን የሠራተኞች ክበብ ከዚህ በታች የወጣውን መስፈርት መሰረት በማድረግ በዘርፉ ለተሰማራ አገልግሎት ሰጪ አካል በማዕቀፍ ግዥ ኮንትራት ውል በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የወጣውን መስፈርት የምታሟሉና በዘርፉ የተሰማራቹና የዘመኑ ግብር የከፈላቸሁ፤ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፤ የታደሰ መታወቂያ ወይም ማንነታቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ዋናውንና ኮፒ ያላችሁ ተጫራቾች ማስረጃዎችን ይዞ በመቅረብ በድርጅቱ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ስነድ ለመግዛት
1. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ከመጋቢት 08, 2013 ዓ.ም እስከ መጋቢት 22, 2013 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰሜን ምስራቅ ሪጅን ኢትዮ ቴሌኮም በተከራየው ህንፃ ሀጂ ሙሀመድ ያሲን ታወር ወይም ሁዳ ሪል እስቴት ቢሮ ቁጥር 201 የማይመለስ ብር 50.00 (ሀምሳ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
2. ተጨራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ውጤቱ እንደታወቀ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሠራተኞች ክበብ አገልግሎት ለመግዛት ጠቅላላ ዋጋ 10,000.00 (አስር ሺህ ብር ብቻ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
3. የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ወይም በታወቀ ባንክ ተረጋግጦ የሚቀርብ ሲ.ፒ.ኦ /ቼክ/ መሆን አለበት፡፡
4. የጨረታ ማስከበሪያውን በጥሬ ገንዘብ ለሚያስይዙ ተጫራቾች ከጨረታዉ መክፈቻ ቀን በፊት በሰሜን ምስራቅ ሪጅን ኢትዮ ቴሌኮም በተከራየው ህንፃ ሀጂ ሙሀመድ ያሲን ታወር ወይም ሁዳ ሪል እስቴት ቢሮ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ ደረሰኙን ከጨረታው መክፈቻ ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
5. ተጨራቾች ለአገልግሎት የቀረበውን የሠራተኞች ክበብ ጨረታ ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ እና ማንነታቸዉን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ በመያዝ ከመጋቢት 08, 2013 ዓ.ም እስከ መጋቢት 23, 2013 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት ደሴ ፒያሳ በሚገኘው ሰሜን ምስራቅ ሪጅን ኢትዮ ቴሌኮም ቴክኒክ ህንፃ በመገኝት የሠራተኞች ክበብ በአካል ወይም በግንባር በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላትና በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማሸግ በሰሜን ምስራቅ ሪጅን ኢትዮ ቴሌኮም በተከራየው ህንፃ ሀጂ ሙሀመድ ያሲን ታወር ወይም ሁዳ ሪል እስቴት ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 በሚገኘው የጨረታ ሳጥን መጋቢት 22, 2013 ዓ.ም እስከ 11፡00 ስዓት ድረስ የሠራተኞች ክበብ የተዘጋጀውን ሰነድ ዋጋ መሙላትና ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ባለው ጊዜ ብቻ የጨረታ ሰነዱን ዋጋ በመሙላት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
7. የሠራተኞች ክበብ የወጣው ጨረታ ከመጋቢት 23, 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 በሰሜን ምስራቅ ሪጅን ኢትዮ ቴሌኮም በተከራየው ህንፃ ሀጂ ሙሀመድ ያሲን ታወር ወይም ሁዳ ሪል እስቴት ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ጨረታ የሚከፈቱባቸው ቀናት የህዝብ በዓላት ቀናቶች ላይ ከዋለ በሚቀጥለው ስራ ቀናት ላይ በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታው ይከፈታል ፡፡
8. ተጫራቾች በጨረታው በከፊል መሳተፍ አይችሉም፡፡
9. ኢትዮ ቴሌኮም የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
10. ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በሰሜን ምስራቅ ሪጅን ኢትዮ ቴሌኮም በተከራየው ህንፃ ሀጂ ሙሀመድ ያሲን ታወር ወይም ሁዳ ሪል እስቴት ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 በስራ ሰዓት በግንባር በመቅረብ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እናሳስባለን፡፡