የሾፖች ቢሮዎች፣ የቢሮ አካባቢ፣ የግቢ እና የመኪና ማቆሚያ ቦታ የፅዳት አገልግሎት የሚያቀርቡ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን በሪጅኑ ስር በሚገኙ ሾፖች ቢሮዎች፣ የቢሮ አካባቢ፣ የግቢ እና የመኪና ማቆሚያ ቦታ የፅዳት አገልግሎት የሚያቀርብ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ድርጅት ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሸነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላል፡፡

  1. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ከመስከረም 07 ቀን 2013 እስከ መስከረም 27 ቀን 2013 ዓ.ም ከሰኞ እስከ ዓርብ በስራ ሰዓት አዳማ ከተማ አዋሽ ባንክ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመስሪያ ቤቱ ሶርስንግ ክፍል በመቅረብ ስለጨረታው መረጃ ማግኘትና የማመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) ብር በመክፈል የጨረታውን ሠንድ በመግዛት መወዳደር ይቻላል፡፡
  2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት በሚመጡበት ወቅት የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ዋናውን እና ኮፒ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል ::
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ውጤቱ እንደተወቀ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ከታወቀ ባንክ ተረጋግጦ በሚቀርብ ዋስትና (CPO) 20,000 (ሃያ ሺ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ሰነዶቻቸው ላይ የጨረታውን ስም፤ የተጫራቹን ሙሉ ስም እና አድራሻ በትክክል መጻፍ አለባቸው፡፡
  5. የድርጅቱን የባንክ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ባንክ ስቴትመንት ማቀርረብ የሚችል፡፡
  6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መስከረም 27 ቀን 2013 . ከቀኑ 500 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 830 ሰዓት ይከፈታል::
  7. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱንና ሲፒኦ በታሸገ ኢንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ በተዘገጀ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 022-111-0994 / 022-112-1660 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives