የትምህርት አስተዳደር ሥርዐት

Update soon
ለላቀ ትምህርት አስተዳደር፡ ከምዝገባ እስክ ምርቃት፤ ሁሉንም አገልግሎቶች በአንድ መድረክ!
የትምህርት ተቋማትን አሠራር ለማዘመንና ሁሉንም አገልግሎት በአንድ ማዕቀፍ ሥር ለመስጠት የተነደፈ ሁሉን አቀፍ ሶሉሽን ነው። ይህ ዘመናዊ ሲስተም፤ ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ጀምሮ እስከ ዩኒቨርሲቲ፤ ከሞያ ማሠልጠኛ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ድረስ፤ የሚያጋጥሙ የረዥም ጊዜ ተግዳሮቶችን በመፍታት ምዝገባ ለማከናወን ምቹ የሆነ፣ የአካዳሚክ፣ የአስተዳደር እና የተማሪዎችን ተሳትፎ በማቅለል፤ ተቋማቱ ጥራት ያለው ትምህርት ለመስጠት በሚያስችላቸው ተገባራት ላይ እንዲያተኩሩ ያስችላቸዋል።

ለምን የእኛን የትምህርት አስተዳደር ሥርዐትን ይመርጣሉ?
የትምህርት አስተዳደር ሶሉሽናችን፤ የትምህርት ተቋማትን ፍላጎቶች ለማሟላት የተነደፈ ሁሉን አቀፍ መፍትሔ ነው። ስለሆነም፡-
ሁሉም በአንድ ሥርዐት ማስተዳደሩ፤
ሊለካ የሚችልና ወጪ ቆጣቢ፤ እንዲሁም እየተገለገሉበት የሚከፍሉት መሆኑ፤
በክላውድ ላይ የተመሠረተ፣ በማንኛውም መሳሪያዎች ላይ እንከን የለሽ ትሥሥር መፍጠር መቻሉ፤
ኢትዮጵያ ላይ ያተኮረና አካባቢያዊ ፍላጎቶችን ማሟላት የሚያስችል መለያዎች መኖሩ፤
 በTelecloud የጎለበተ፣ ደኅንነቱ የተጠበቀና አስተማማኝ መሆኑ፤
በየጊዜው ሒደቱን የሚከታተሉ የባለሞያዎች ድጋፍ መኖሩ ተመራጭ ያደርገዋል።
ቁልፍ ባሕርያትና ጥቅሞች
ለት/ቤት አስተዳደርና መምህራን፡–
የአስተዳደር ቅልጥፍናን ያሻሽላል፡ ምዝገባ፣ መዝገብ መያዝና ሪፖርት አውቶሜት ለማድረግ፤
የላቀ የዳታ አስተዳደር፡ መረጃዎች በአንድ ማዕከል በማድረግ የተሻለ የሥራ ግንዛቤን ለመስጠት፤
የተሻሻለ ኮሙኒኬሽን፡ ከተማሪዎችና ከወላጆች ጋር ተግባቦት/ኮሙኒኬሽን ለመፍጠር፤
የተሳለጠ የፋይናንስ አስተዳደር፡ ክፍያ መሰብሰብን፣ በጀት ማውጣትንና የሒሳብ አያያዝን ለማቅለል፤
ወጪ ቆጣቢና ሊስፋፋ የሚችል፡ በክላውድ ላይ የተመሠረተ፣ የአይ.ቲ ወጪን በመቀነስ በቀላሉ ለማስፋፋት/ለማሳደግ ያስችላል፤
የጊዜ ሰሌዳን ለማስተዳደር፡ የትምህርት ክፍለ ጊዜ መርሐ ግብርን በቀላሉ ለመንደፍ፤
ሀብትን ለማስተዳደር፡ የሰው ኃይልን፣ ቤተ መጻሕፍትንና የእቃ ግምጃ ቤት መሳሪያዎችን ይቆጣጠራል፡፡
ለተማሪዎች፡-
እንከን የለሽ የመረጃ ተደራሽነት፡ የፈተና ውጤት፣ አሳይመንት፣ ክፍለ ጊዜንና ማስታወቂያዎችን በቀላሉ ለማግኘት፤
ተግባቦትን ለማሻሻል፡ በአስተማሪዎችና ተማሪዎች መካከል የተሻለ ተግባቦት እንዲኖር፤
ግላዊ ትምህርት፡ ለግል የተዘጋጀ ትምህርትን በዳታ/በመረጃ ላይ በመመሥረት እይታዎችን ይደግፋል፤
ተሳትፎን ለመጨመር፡ የበለጠ አሳታፊና መስተጋብር ያለው የመማሪያ አካባቢን ይፈጥራል።
ለወላጆች፡-
የተሻሻለ እይታ፡ የልጆቻቸውን የትምህርት ለውጥ፣ ት/ቤት መገኘትና የት/ቤት መስተጋብሮችን በቅጽበት ለማግኘት፤
እንከን የለሽ ትሥሥር፡ ከመምህራንና ትቤት አስተዳዳሪዎች ጋር ቀላልና መልካም ተግባቦት እንዲኖር ለማስቻል፣
ለክፍያ ያለው ምቹነት፡ ደኅንነቱ የተጠበቀና ምቹ በሆነውን ቴሌብርን በመጠቀም የት/ቤት ክፍያዎችን በየትኛውም ቦታ ለመክፈል ያስችላል፤
ተሳትፎን መጨመር፡ ወላጆች በልጆቻቸው ትምህርት ላይ የላቀ ተሳትፎን እንዲኖራቸው ያሳድጋል።
ከቴሌብር ጋር ያለው ትስስር፡ ሲስተሙ ከቴሌብር ጋር ያለው የተሳሰረ በመሆኑ ለትምህርት ቤት ክፍያ ምቹ እና አስተማማኝ ሲሆን፣ በኢትዮ ቴሌኮም ቴሌክላውድ የተደገፈ ነው፡፡

የትምህርት አስተዳደር ሥርዐት ዋጋ �ርዝር

የትምህርት አስተዳደር ሥርዐት ዋጋ ዝርዝር

የሕዝብ ት/ቤት ጥቅል

ቋሚ ዓመታዊ ክፍያ: 47,500 ብር

የተማሪዎች ቁጥር: ያልተገደብ

ከቅድመ ደረጃ እስከ 12ኛ ክፍል

150,000 ብር
የግል ት/ቤት ጥቅል

ቋሚ ዓመታዊ ክፍያ: 55,000 ብር

የተማሪዎች ቁጥር: ያልተገደብ

ከቅድመ ደረጃ እስከ 12ኛ ክፍል

350,000 ብር
አዳሪ የሕዝብ ት/ቤት ጥቅል

ቋሚ ዓመታዊ ክፍያ: 50,000 ብር

የተማሪዎች ቁጥር: ያልተገደብ

የዶርም፣ ምግብና ትራንስፖርት አገልግሎት

175,000 ብር
አዳሪ የግል ት/ቤት ጥቅል

ቋሚ ዓመታዊ ክፍያ: 75,000 ብር

የተማሪዎች ቁጥር: ያልተገደብ

የዶርም፣ ምግብና ትራንስፖርት አገልግሎት

550,000 ብር
የግብርና ኮሌጅ

ቋሚ ዓመታዊ ክፍያ: 250,000 ብር

የተማሪዎች ቁጥር: ያልተገደብ

750,000 ብር
ፖሊ ቴክኒክና ሞያ ሥልጠና ኮሌጅ

ቋሚ ዓመታዊ ክፍያ: 50,000 ብር

የተማሪዎች ቁጥር: ያልተገደብ

350,000 ብር
ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ

ቋሚ ዓመታዊ ክፍያ: 87,500 ብር

የተማሪዎች ቁጥር: ያልተገደብ

450,000 ብር
የሕዝብና የግል ዩኒቨርሲቲ

ቋሚ ዓመታዊ ክፍያ: 1,500,000 ብር

የተማሪዎች ቁጥር: ያልተገደብ

8,000,000 ብር
ERP (ለህዝብ ትምህርት ተቋም)

ቋሚ ዓመታዊ ክፍያ: 35,000 ብር

ለመንግስት ትምህርት ተቋማት (ዩኒቨርሲቲዎች በስተቀር)

35,000 ብር
ERP (ለህዝብ አዳሪ ት/ቤት)

ቋሚ ዓመታዊ ክፍያ: 25,000 ብር

ለመንግስት አዳሪ ትምህርት ተቋማት

50,000 ብር
ERP (የግልና ዩኒቨርሲቲዎች)

ቋሚ ዓመታዊ ክፍያ: 55,000 ብር

ለግል ትምህርት ተቋማትና ዩኒቨርሲቲዎች

100,000 ብር

ሁሉም ዋጋዎች ተ.እ.ታን ያካተቱ ናቸው!

ለአገልግሎቱ የድርጅት አገልግሎት መስጫ ማዕከላችንን ይጎብኙ!