የኢትዮ ቴሌኮም የሦስት ዓመታት (2013 – 2015) ስትራቴጂ (Growth Strategy) እና የ2013 ዓመታዊ እቅድ
ይህ ስትራቴጂ የሚሸፍነው ከሐምሌ 2012 እስከ ሰኔ 2015 ያለውን ጊዜ ነው፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም በሀገራችን ለ126 ዓመታት የቴሌኮም አገልግሎት በመስጠት በሀገር ሁለንተናዊ እድገትና በዜጎች ኑሮ መሻሻል ላይ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡ መንግስት የሀገራችንን የቴሌኮም ዘርፍ የገበያ መዋቅር ላይ የፖሊሲ ለውጥ በማምጣት ተወዳዳሪ የቴሌኮም ገበያ ለመፍጠር የሰጠውን አቅጣጫ ተከትሎ በ2012 በጀት ዓመት የኢትዮ ቴሌኮም ማኔጅመንት ለሦስት አመታት የሚያገለግል ስትራቴጂ በመቅረጽ ተቋሙን ተመራጭና ለውድድር ብቁ ለማድረግ፣ በቢዝነስ እይታና በውድድር መንፈስ የተቃኘ አመራርና ሠራተኛ እንዲሁም አሠራር ለመፍጠር የሚያስችለውን ስትራቴጂ በመንደፍ ወደ ትግበራ መግባቱ ይታወሳል፡፡
ኩባንያችን የሦስት ዓመቱን ስትራቴጂ በመከለስና አንድ ዓመት በመጨመር የሦስት ዓመት የእድገት ስትራቴጂ አዘጋጅቷል፡፡ የቴሌኮም ዘርፍ በፍጥነት እያደገና ተለዋዋጭ በመሆኑ ከወቅቱ ጋር በፍጥነት የሚራመድ ተቋም የመሆን ትልም በመንደፍ ይህ ዕቅድ ቋሚ (Static) ሳይሆን በየወቅቱ በኢንዱስትሪው ላይ የሚታዩ እድገትና ለውጦች እንዲሁም ከውድድርና የባለቤትነት ድርሻ ከማስተላለፍ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችንና የሀገራችን ነባራዊ ሁኔታዎችን ታሳቢ በማድረግ ‘deliberate’ እና ‘emergent strategy approach’ በመከተል የተዘጋጀ ሲሆን እቅዱ ሊሻሻል እንደሚችል ታሳቢ ተደርጓል፡፡
ስትራቴጂው ሲዘጋጅ የተቋሙን ተወዳዳሪነት እና አስተማማኝ እድገት ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ ተቋሙ ላይ ፍላጎትና ተጽዕኖ ሊኖራቸው የሚችሉ የመንግስት የፖሊሲ ሰነዶችን፣ የውስጥና የውጭ ባለድርሻ አካላት ፍላጎትና ተጽዕኖ (የደንበኞች፣ የሠራተኞች፣ የቴክኖሎጂ አቅራቢዎችና የተለያዩ የመንግስት አካላት እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት) በተጨማሪም በቴሌኮም ዘርፍ የተሰማሩ ሌሎች ተቋማት ያላቸውን የገበያ እንቅስቃሴና ልምድ፣ የቴሌኮም ኢንዱስትሪ እድገት ዋና ዋና አዝማሚያዎችና የዓለም አቀፍ ምርጥ ተሞክሮችን በመተንተን፣ እንዲሁም ውስጣዊ ጥንካሬና ውስንነቶችን በመለየት፣ ውጫዊ መልካም አጋጣሚዎችና ስጋቶችን በመለየትና በመተንተን የተቋሙን ተጨባጭ አቅምና ለተወዳዳሪነት የሚያበቃውን ተግባራት በመቃኘት የተዘጋጀ እቅድ ነው፡፡
የሦስት ዓመት ስትራቴጂውና የ2013 በጀት ዓመት ቢዝነስ እቅድ በማኔጅመንት የተገመገመና የጸደቀ ሲሆን በተጨማሪም በተቋሙ የሥራ አመራር ቦርድ ሰፊ ውይይት በማካሄድ የጸደቀ ነው፡፡ ይህንንም ተከትሎ ለ2013 በጀት ዓመት እቅድ ማስፈጸሚያ በጀት ጸድቆ ስትራቴጂውን ለትግበራ ዝግጁ ከማድረግ አኳያ በሥራ ክፍሎች መካከል ተገቢውን ትስስርና መንሰላሰል በመፍጠርና ካስኬድ በማድረግ ከበጀት ዓመቱ መጀመሪያ ወር (ሐምሌ 2012) አንስቶ ሥራ ላይ ውሏል፡፡
ስትራቴጂው በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ የመጣውን የደንበኛ ፍላጎትን ለማርካት፣ የቴሌኮም ስርጸትን በማሳደግ የዲጂታል ኢኮኖሚን ለመደገፍና አጠቃላይ የሀገሪቱን ምርታማነትን ለማሳደግ እንዲሁም የተቋሙን የገቢ ምንጭ ከተለመደው መሠረታዊ የቴሌኮም አገልግሎቶች ወደ ዳታና የይዘት አገልግሎቶች (Contents and Value Added Services) ትኩረት በማድረግ እንደ Internet of Things (IoT) እና Application Program Interface (API) የመሳሰሉ አገልግሎቶችን በማስጀመርና በማጠናከር የተቋሙን ቀጣይነትና እድገት አስተማማኝ ለማድረግ ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡
የተቋሙ ዋነኛ ኃብት የሆነውን የሰው ኃይል ከማልማት አንጻር የኢንዱስትሪውን በፈጣን ሁኔታ ማደግና ተለዋዋጭነትን በሚገባ የሚገነዘብ፣ ከእድገቱ የሚገኙ ትሩፋቶችንና መልካም አጋጣሚዎችን በአግባቡ የሚጠቀም እንዲሁም ከኢንዱስትሪው ባህሪ ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ ፈታኝ ሁኔታዎችን በበቂ ዝግጅትና በጥንቃቄ ለመምራት የሚያስችል እውቀትና ክህሎት ያለው የሰው ኃይል መገንባት የስትራቴጂው ዋነኛው የትኩረት አቅጣጫ ነው፡፡
የቴሌኮም አገልግሎት በኢንዱስትሪው ላይ ያሉ ባለድርሻ አካላት የተባበረ ጥረት የሚጠይቅ እንደመሆኑ የተቋሙን ስትራቴጂ ከእነዚህ አካላት ጋር በተለይም የቴክኖሎጂ መሳሪያ አቅራቢዎች ጋር ውይይት የተካሄደበት ሲሆን በቀጣይም ከተቋሙ ምርት አከፋፋይ አጋሮች፣ የይዘት አገልግሎት አቅራቢዎችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት የሚደረግበት ይሆናል፡፡ ይህም ተቋሙ ምርትና አገልግሎቶቹን ወደ ገበያ የሚያቀርብበትን ጊዜ የሚያሳጥርና የደንበኞቹን እርካታ ለማረጋገጥ የሚያደርገውን ጥረት የሚደግፍ ነው፡፡
ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት በተለዩት ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮች ማለትም ምርጥ የደንበኛን ተሞክሮ ማረጋገጥ፣ ጠንካራ የፋይናንስ አቅም መፍጠር፣ የአገልግሎትና የቴክኖሎጂ ልህቀት ማረጋገጥ፣ ሰው ተኮርና የሚማር ተቋም መገንባት፣ የኦፕሬሽን ልህቀት እና ተቋማዊ ገጽታ ግንባታ ሥራዎች ኩባንያው ዕውን ለማድረግ ያለውን የሰው ኃይል፣ እውቀትና ሀብት በአግባቡ በመምራት በደንበኞቹ፣ በአጋሮቹና በባለድርሻ አካላት ተመራጭ ኩባንያ ለመሆን የሚንቀሳቀስ ይሆናል፡፡
በ2013 በጀት ዓመት ለማከናወን የታቀዱ ዋና ዋና ግቦች
የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል የኔትወርክ አቅምና ሽፋንን የሚያሳድግ የኔትወርክ ማስፋፊያ እንዲሁም አማራጭ የኃይል አቅርቦት ሥራዎች በአዲስ አበባና በሁሉም ክልሎች የሚከናወኑ ሲሆን የዳታ ትራፊክ እድገትን መሠረት ያደረገ የ4G/LTE Advanced አገልግሎት በአዲስ አበባ የማስፋፊያ ሥራዎች እና የ4G/LTE ኔትወርክ ማስፋፊያ በክልል ዋና ዋና ከተሞች ይከናወናል፡፡ በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ 5.47 ሚሊዮን ተጨማሪ ደንበኞችን ማስተናገድ የሚችል የሞባይል ኔትወርክ አቅም የሚገነባ ሲሆን በተጨማሪም በፍጥነት እያደገ ያለውን የዳታ አጠቃቀም ለማስተናገድ የሚያስችል የዓለም አቀፍ ጌትዌይ አቅም ለማሳደግም እቅድ ተይዟል፡፡
በ2013 በጀት ዓመት የደንበኛ ብዛትን በ13% በመጨመር 52.12 ሚሊዮን ለማድረስ የታቀደ ሲሆን በሞባይል 11.8% በመጨመር 49.77 ሚሊዮን፣ የዳታና ኢንተርኔት ተጠቃሚ በ16.5% በመጨመር 27.47 ሚሊዮን፣ የፊክስድ ብሮድባንድ ደንበኛ በ215% በመጨመር 669.4 ሺህ በማድረስ አጠቃላይ የቴሌኮም ስርጸት መጠንን 51.3% ለማድረስ ታቅዷል፡፡
ገቢን ከማሳደግ አኳያ ከተለመደው የቴሌኮም የገቢ ምንጮች በተጨማሪ ሌሎች እሴት የሚጨምሩ አገልግሎቶችን በመጨመር፣ 14 አዲስና 21 የተሻሻሉ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ አገልግሎቶችን ለገበያ በማቅረብ የገቢ መጠንን 55.55 ቢሊዮን ብር ለማድረስ ታቅዷል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም ስትራቴጂውን በታቀደው መሠረት በመተግበር የኦፕሬሽን ልህቀትንና የደንበኛ እርካታን ለማረጋገጥ የሠራተኛውን የመፈጸም አቅም በማሳደግና በማሳተፍ፣ የሠራተኛውንና የተቋሙን ዓላማ በማስተሳሰርና በማጣጣም ይሰራል፡፡
አዳዲስና የተሻሻሉ ምርትና አገልግሎቶች
በዛሬው ዕለት በርካታ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ አዳዲስና የተሻሻሉ ምርትና አገልግሎቶች የቀረቡ ሲሆን በሁሉም ነባር የጥቅል አገልግሎቶች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ቅናሽ የተደረገ ተደርጓል፡፡ ኩባንያችን ማህበራዊ ኃላፊነቱን ከመወጣት አኳያ የኮቪድ-19 ተጽዕኖ ለመቋቋም ከዚህ ቀደም በቤትዎ ይቆዩ በሚል ያቀረበው አገልግሎት ላይ እስከ 59% ቅናሽ በማድረግና በማሻሻል በጤና ይቆዩ በሚል ያቀረበ ሲሆን ያለፈውን በጀት ዓመት በስኬት መጠናቀቅን አስመልክቶ ለሦስት ቀናት የሚቆይ የምስጋና ስጦታ ጥቅል አገልግሎት አቅርቧል፡፡ በተጨማሪም የአዲስ ዓመት መቃረብን አስመልክቶ የአደይ አበባ የሞባይል ጥቅል አገልግሎትና በዓለም አቀፍ አየር ሰዓት አገልግሎት ላይ 100% የአየር ሰዓት ስጦታ ለደንበኞቹ አቅርቧል፡፡
ድርጅቶች ከሠራተኞቻቸውና ከሥራ አጋሮቻቸው ከርቀት ሆነው በቪዲዮ የታገዙ ስብሰባዎችን፣ የቡድን ሥራዎችንና የተለያዩ ዎርክሾፖችን ለማከናወን የሚረዳ ኢትዮ አቫያ ስፔስ ኢንተርፕራይዝ ኮላቦሬሽንስ ሶልዩሽን የተሰኘ በርካታ ተዛማጅ አገልግሎቶችን የሚሰጥ አገልግሎት የቀረበ ሲሆን በተጨማሪም መደበኛ የቴሌኮም አውታሮች በማይገኙባቸው አካባቢዎች ወይም እንደ መጠባበቂያ መጠቀም የሚያስችል የሳተላይት አገልግሎት በማሻሻል ለገበያ ቀርቧል፡፡ ኩባንያችን ደንበኞቹ ምርትና አገልግሎቶቻችንን በቀላሉ ማግኘት የሚያስችላቸው My Ethiotel የሚል የሞባይል መተግበሪያ፣ Ethio eCare የተሰኘ ራስ አገዝ መተግበሪያ እንዲሁም አዲስ ድረ ገጽ በማዘጋጀት ለደንበኞቹ ያቀረበ ሲሆን ደንበኞቹም በነጻ መጎብኘትና መገልገል ያስችላቸዋል፡፡ ዝርዘር አገልግሎቶችና የተደረጉ የዋጋ ማሻሻያዎች ከዚህ በታች ቀርበዋል፡፡
የዋጋ ቅናሽ የተደረገባቸው ነባር አገልግሎቶች
- በሞባይል ዳታ ጥቅልአገልግሎት እስከ 35 በመቶ ቅናሽ
- በሞባይል ድምፅ ጥቅልአገልግሎት እስከ 29 በመቶ ቅናሽ
- የሞባይል ድምፅ እና ዳታ ጥምርአገልግሎት እስከ 28 በመቶ ቅናሽ
- በፕሪሚየም ያልተገደበ የድምፅ ጥቅልአገልግሎት እስከ 21 በመቶ ቅናሽ
- በፕሪሚየም ያልተገደበ የዳታ ጥቅልአገልግሎት እስከ 21 በመቶ ቅናሽ
- በፕሪሚየም ያልተገደበ የድምፅ እና ዳታ ጥቅልአገልግሎት እስከ 20 በመቶ ቅናሽ
- በፕሪሚየም ፕላስ ያልተገደበ ጥቅልአገልግሎት እስከ 16 በመቶ ቅናሽ እንዲሁም
- በሳተላይት አገልግሎት (VSAT) ላይ እስከ 61 በመቶ የሚደርስ ቅናሽ ተደርጓል፡፡
አዲስ የቀረቡ አገልግሎቶች
- My Ethiotelየሞባይል መተግብሪያ
- Ethio eCareዌብ ፖርታል
- የሞባይል ጥቅል ክሬዲት አገልግሎት
- የድህረ ክፍያ የሞባይል ኮንትራት ፕላን
- ኢትዮ አቫያ ስፔስ ኢንተርፕራይዝ ኮላቦሬሽን ሶልዩሽን
- በጤና ይቆዩየሞባይል ጥቅል እስከ 59 በመቶ ቅናሽ
- አደይ አበባየሞባይል ጥቅል እስከ 53 በመቶ ቅናሽ
- መልካም ማለዳየሞባይል ጥቅል አገልግሎት እስከ 33 በመቶ ቅናሽ
በዓለም አቀፍ የቴሌኮም አገልግሎት ላይ አዲስ የቀረቡ
- የዓለም አቀፍ የወጪ ጥሪ ጥቅል አገልግሎት
- ዓለም አቀፍ የገቢ ጥሪ ለሚቀበሉ ደንበኞች የቀረበ የሞባይል አገልግሎት ጥቅል ስጦታ
- በዓለም አቀፍ አየር ሰዓት አገልግሎት ላይ የተደረገ 100% የአየር ሰዓት ስጦታ
Ethio telecom 2020 – 2023 Growth Strategy and 2020/21 Business Plan
This strategy covers a time period from 1 July 2020 to 30 June 2021
Ethio telecom, as an enabler for the socio-economic development of the nation, has been serving Ethiopia for the last 126 years. Following the government’s direction to reform the Ethiopian telecom market, to create a competitive space, Ethio telecom management took initiative to develop a three-year strategic plan in the last budget year to get ready for the upcoming competitive market, reshape and lead the company with a business orientation and competitive mindset with ultimate aim of making the company a Preferred Operator. Consequently, strategy execution was put in place.
Ethio telecom follows rolling strategy model applying deliberate and emergent strategy development approaches to accommodate a changing reality, considering the nature of the business and the ongoing market reform. To ensure competitiveness and sustainable growth of the company, this strategy has been developed by considering and reviewing relevant government policies, international best practices, and Industry trends. Various important analyses have been made such as internal and external stakeholders’ interests and expectations (Customers, Employees, Vendors/suppliers and various government organs), previous company performances, internal strengths, organizational resources and capacities, and weaknesses, opportunities and threats in the outer environment (PESTLE) and the upcoming competition.
The strategy has been reviewed at senior and middle management levels, consulted, and validated by Ethio telecom Board of Directors. Following validation, communication, cascading, and alignment of the strategy have been conducted to improve strategy execution among stakeholders.
The strategy addresses ever-changing customer demand, digital inclusion to create better digital economy, enhance productivity, shift the revenue from traditional revenue streams to value added and content driven services by introducing new business streams and solutions like Internet of Things (IOT), Application Programming Interface (API), and other new services. The strategy has also focused on the most important company asset – employees, to equip them with relevant knowledge and skill that will enable them to grasp and catch up with the telecom industry dynamism, to exploit opportunities arising from development of the industry and cope with the challenges.
Telecom business needs collaboration and concerted efforts of all players in the ecosystem, to this end, the strategy has been discussed with partners including vendors and subsequent discussions with distributors, content providers and other stakeholders will be held within a short period of time. This will further enhance the shortening of TTM, meet customer demands by adopting new solutions and insights.
Major Business plan Objectives and Targets in 2013 EFY (July 2020 – June 2021)
To improve the quality of services and service accessibility, network expansion and alternative power solutions will be implemented in Addis Ababa and regions. Based on data traffic growth and demand, 4G/LTE Advanced network capacity expansion will be carried out in Addis Ababa and 4G/LTE roll out will be conducted in regional towns. To improve network coverage and capacity, more than 5.47 Million additional Mobile network capacity will be installed in Addis Ababa and Regions. Furthermore, to accommodate growing data usage, International gateway capacity will be upgraded.
Ethio telecom has also planned to increase total subscribers by 13% to 51.12 M, Mobile Voice subscribers by 11.8% to 49.77M, Data and Internet users by 16.5% to 27.47M, Fixed Broadband subscribers by 215.3% to 669.4K. This is expected to bring telecom penetration to 51.3%.
By engaging in new business streams and shifting revenue source from traditional to value-added services and by offering 14 new and 21 revamped local and international products & services, Ethio telecom aims to generate 55.55B Birr revenue.
With enhanced employee engagement, empowerment, skill development and goal alignment, Ethio telecom aspires and works to become preferred Operators by its Customers, partners and stakeholders.
New and Revamped Products and Services
We have offered several new and revamped services, both local & international, with significant discounts; as part of our Corporate Social Responsibility roles, we have offered Stay Safe package to lessen COVID -19 impacts with up to 59% discount. This offer is revamped from Stay at home package that has been in place since April 16, 2020. As previous budget year ended and Ethiopian new year is approaching, we have offered Three Days Thank You Gift Package and Adey Abeba packages consecutively. Our New year offer also includes a 100% local airtime gift on International Airtime Top-up (IAT).
We have offered Ethio- Avaya a business solution to provide unified communications, real-time video collaboration, networking, and related services to enterprises of all sizes in Ethiopia. We have also offered a discount in our telecommunication Service via Satellite (VSAT) that allows to connect remote locations where terminal network is not available.
In creating more convenience for our customers, we have developed and availed My Ethiotel Mobile App, Ethio e-Care and new website that could be accessed for free by all customers.
The detail offers and discounts is presented below.
Discounts Made on Existing Services
- Up to 35 % discount on Mobile Data Package
- Up to 29 % discount on Mobile Voice Package
- Up to 28 % discount on Mobile Voice Plus Data Package
- Up to 21 % discount on Unlimited Premium Mobile Voice Package
- Up to 21 % discount on Unlimited Premium Mobile Data Package
- Up to 20 % discount on Unlimited Premium Mobile Voice Plus Data Package
- Up to 16 % discount on Premium Plus Mobile Package
- Up to 61 % discount on Telecom Service Via Satellite (VSAT) Service
Newly Introduced Services
- My Ethiotel Mobile App
- Ethio e-Care Web Portal
- Mobile Package Credit Services
- Post-paid Mobile Contract Plan
- Ethio Avaya Enterprise Corporate Solution
- Stay Safe Mobile Packages- with up to 59 % discount
- Adey Abeba Packages- with up to 53% discount
- Good Morning Packages- with up to 33 % discount
New International Telecom Services
- International Outgoing Call Packages
- Receive International Call and Get Voice Package as a Gift
- A 100% Gift on International Airtime Top-up