የቴሌብር ሚስጥር ቁጥር ቢጠፋብዎ በቀላሉ ሌላ አዲስ የሚስጥር ቁጥር ለመቀየር አስቀድመው ለመረጡት ሚስጢራዊ ጥያቄ መልስ በመስጠት ዝግጁ ማድረግ ይችላሉ፡፡
- ለቴሌብር አገልግሎትዎ አስቀድመው ሚስጥራዊ ጥያቄ እና መልስ ለማዘጋጀት
- ወደ ቴሌብር ሱፐርአፕ አገልግሎትዎ ይግቡ፣
- መለያ የሚለዉን በመጫን ሚስጥራዊ ጥያቄ ይምረጡ፣
- ከዚያም ይቀጥሉ የሚለውን ይጫኑ፣
- የፈለጉትን የደህንነት ጥያቄ ይምረጡ፣
- ለመረጡት ጥያቄ መልስ በመስጠት ያረጋግጡ፣
- የጠፋብዎትን የቴሌብር አገልግሎትዎን የሚስጥር ቁጥር በአዲስ ለመቀየር
- ወደ ቴሌብር ሱፐርአፕ አገልግሎትዎ ይግቡ፣
- የሚስጥር ቁጥር ረስተዋል የሚለውን ይምረጡ፣
- ከ127 የሚደርስዎን የማረጋገጫ ቁጥር ያስገቡ፣
- ከዚህ በፊት የሞሉትን የሚስጥራዊ ጥያቄ በመምረጥ መልስ ያስገቡና ያረጋግጡ፤
- በመቀጠል ከ127 የሚደረስዎን ቁጥር ጊዜያዊ የሚስጥር ቁጥር በሚለዉ ቦታ ላይ ያስገቡ፣
- አዲስ ባለ 6 አኃዝ የሚስጥር ቁጥር ያስገቡ፤
- በመጨረሻም በድጋሚ አዲሱን የሚስጥር ቁጥር አስገብተዉ ያረጋግጡ፡፡