የቴሌብር ሚስጥር ቁጥር ቢጠፋብዎ በቀላሉ ሌላ አዲስ የሚስጥር ቁጥር ለመቀየር አስቀድመው ለመረጡት ሚስጢራዊ ጥያቄ መልስ በመስጠት ዝግጁ ማድረግ ይችላሉ፡፡

  1. ለቴሌብር አገልግሎትዎ አስቀድመው ሚስጥራዊ ጥያቄ እና መልስ ለማዘጋጀት
  • ወደ ቴሌብር ሱፐርአፕ አገልግሎትዎ ይግቡ፣
  • መለያ የሚለዉን በመጫን ሚስጥራዊ ጥያቄ ይምረጡ፣
  • ከዚያም ይቀጥሉ የሚለውን ይጫኑ፣
  • የፈለጉትን የደህንነት ጥያቄ ይምረጡ፣
  • ለመረጡት ጥያቄ መልስ በመስጠት ያረጋግጡ፣
  1. የጠፋብዎትን የቴሌብር አገልግሎትዎን የሚስጥር ቁጥር በአዲስ ለመቀየር
  • ወደ ቴሌብር ሱፐርአፕ አገልግሎትዎ ይግቡ፣
  • የሚስጥር ቁጥር ረስተዋል የሚለውን ይምረጡ፣
  • ከ127 የሚደርስዎን የማረጋገጫ ቁጥር ያስገቡ፣
  • ከዚህ በፊት የሞሉትን የሚስጥራዊ ጥያቄ በመምረጥ መልስ ያስገቡና ያረጋግጡ፤
  • በመቀጠል ከ127 የሚደረስዎን ቁጥር ጊዜያዊ የሚስጥር ቁጥር በሚለዉ ቦታ ላይ ያስገቡ፣
  • አዲስ ባለ 6 አኃዝ የሚስጥር ቁጥር ያስገቡ፤
  • በመጨረሻም በድጋሚ አዲሱን የሚስጥር ቁጥር አስገብተዉ ያረጋግጡ፡፡

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives