የጨረታ ቁጥር ደ/አ/አ/ዞን 01/2013 ዓ.ም.

ጨረታው የሚቆይበት ጊዜ ከሰኔ 1 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ሰኔ 29 ቀን 2013 ዓ.ም. ጠዋት 4፡30 ሰዓት ድረስ ይሆናል፡፡

1. ስለ አሻሻጡ ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ከሰኔ 01 ቀን 2013 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 28 ቀን 2013 ዓ.ም. ጠዋት 3፡00 ሰዓት ድረስ ከሙለጌ ህንፃ 5 ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 509 የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይቻላል፡፡

2. የተለያዩ ያገለገሉ ወረቀቶች፣ካርቶን፤ደረሰኞች እና ፎርሞችን ለማየት ለሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የገዙበትን ደረሰኝና መታወቂያ በመያዝ ገላን ቴሌ ጊቢ ውስጥ በሚገኘው መጋዘን በመገኘት ከሰኔ 1 ቀን 2013 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 29 ቀን 2013 ዓ.ም. ዘወትር በስራ ሰዓት መመልከት ይቻላል፡፡

3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ተመላሽ የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የተለያዩ ያገለገሉ ወረቀቶች፣ካርቶን፤ደረሰኞች እና ፎርሞችን ለመግዛት የሚያቀርቡትን ጠቅላላ ዋጋ 5% (አምስት ከመቶ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታ ማስከበሪያው ከታወቀ ባንክ ተረጋግጦ በሚቀርብ ሲፒኦ (CPO) መሆን ይኖርበታል፡፡

4. ተጫራቾች የተለያዩ ያገለገሉ ወረቀቶች፣ካርቶን፤ደረሰኞች እና ፎርሞችን የሚገዙበትን ዋጋ በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ/ፎርም መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን የተለያዩ ያገለገሉ ወረቀቶች፣ካርቶን፤ደረሰኞች እና ፎርሞችን የሚያሳይ የዋጋ ማስገቢያ ቅጽ/ፎርም፣ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ኮፒ፣የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ (CPO) ፣ የተጫራቾች አድራሻ መግለጫን በማካተት በታሸገ ኤንቨሎ ሙሉ አድራሻውንና የጨረታውን ቁጥር በመጥቀሰ ሙለጌ ህንፃ 5 ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 509  ከሰኔ 1 ቀን 2013 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 29 ቀን 2013 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት የሚጠበቅ ሲሆን ከዚህ ቀንና ሰዓት በኋላ የሚቀርብ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም::

5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሙለጌ ህንፃ 5 ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 509 ሰኔ 29 ቀን 2013 ዓ.ም. ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives