ኢትዮ ቴሌኮም ለኩባንያው አገልግሎት የማይሰጡ ልዩ ልዩ የከባድ እና ቀላል መኪና መለዋወጫዎችን፣ የስልክ ቀፎዎችን፣ ከአገልግሎት የተመለሱ ባትሪዎችን፣ ፒ.ቪ.ሲዎችን፣ የኤች.ዲ.ፒ ዳክቶችን፣ የጽሕፈት መሣሪያዎችን፣ የተለያዩ የኢንፎርሜሽን ሲስተም፣ የፋን፣ የፓወር እና የኔትወርክ ዕቃዎችን እንዲሁም ልዩ ልዩ የብረት፣ የእንጨት እንዲሁም የኮንክሪት ፖሎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ከመጋቢት 16 እስከ ሚያዝያ ዐ6 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ በማንኛውም ጊዜ እና ሰዓት በቴሌ ብር አማካኝነት  የማይመለስ አንድ መቶ ብር በመክፈል ከ www.extratenders.com እና www.afrotender.com ዌብ ሳይቶች  መግዛት የሚችሉ ሲሆን ንብረቶቹን ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች የታደሰ መታወቂያቸውን በመያዝ ላንቻ አከባቢ በሚገኘው የኩባንያው ጋራዥ እንዲሁም መስቀል ፍላወር እና አቃቂ በሚገኙት የኩባንያው ዕቃ ግምጃ ቤቶች ማየት ይችላሉ፡፡

ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአቃቂ ዕቃ ግምጃ ቤት ሚያዝያ 7 ቀን 2014 ዓ.ም ከረፋዱ 4:30ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ አቃቂ ከሚገኘው የኢትዮ ቴሌኮም ዕቃ ግምጃ ቤት ሥራ አስኪያጅ ቢሮ በአካል በመቅረብ መረጃ ማግኘት ይቻላል ፡፡

ኩባንያው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ዉድ ደንበኞቻችን የጨረታዉ መዝጊያና መክፈቻ ቀን ወደ

ቁጥር

መግለጫ

ቀን እና ሠዓት

1

የጨረታው መዝጊያ ቀን እና ሠዓት

 17/8/2014 11:00

2

የጨረታው ሠነድ የሚከፈትበት ቀን እና ሠዓት

 18/8/2014 04:30

የተራዘመ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡

 

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives