የጨረታ ቁጥር 01/2014

ኢትዮቴሌኮም ከኩባንያው አገልግሎት የተመለሱ ፤ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች ፤የተለያዩ የመኪና መለዋወጫዎች፤ የተለያዩ የብረት መዝጊያና መስኮቶች ፤አልሙኒየም ፤ ኬብል ራን እና የተለያዩ ፕላስቲኮች ፤ ሜሽዋየር፤ የቶነር ካርትሪጆች ፤ ቀለሞች ፤ የእንጨት እቃ ማሸጊያ ሳጥኖች ፤ የእንጨት ፓሌቶች ፤ ኤም ዲ ኤፍ እንጨቶች፤ የእንጨት መዝጊያ፣ መስኮት እ ና ፓርቲሽን ፤ የማገዶ እንጨቶች ፤ የእንጨት ሞራሌ ፤ የእንጨት ድራም ፤ ካዝናዎች ፤ ቦንዳዎች ፤ የተለያዩ አይነት መጠን ያላቸው ጎማዎች፤ የተለያዩ አይነት በርሜሎች፤ የተለያዩ አይነት መጠን ያላቸው የተበላሹጎማዎች፤ አካፋ እና ዶማ ፤ ምንጣፎች ፤ ከአገልግሎት የተመለሱ ቆርቆሮዎች ፤ የሽንት ቤት መቀመጫዎች፤ የፍሎረስንት መያዣ፤ ኤም ዲ ኤፍ ፍሬም እና ጃምፐር ዋየር ፤ የህዝብ ቴሌፎኖች፤ የተለያዩ መጠን ያላቸው የማይከሮዌቭ የፋይበር ዲሾች፤ ካትሪን አንቴና ፤ ሽቦዎች ፤ የተለያዩ አሮጌ ቴሌ ፕሪንተሮች፤ የተለያዩ የኔት ወርክ ካርዶችና እና የቴሌፎን አፓራተስ ፣ሴቲንግ ቴምፕሌት ፤ አንቴና ታወር ፤ የእንጨት ፖሎች፤ ትራንስፎርመሮች፤ ሶላር ፓናል ፤ የፓወር ኬብሎች፤ የተለያዩ አይነት ራኮች ፤የተለያዩ የኔት ወርክ ማቴርያሎችን፤ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት በሚመጡበት ወቅት የዘመኑ ግብር የከፈሉበትን የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣የታደሰ መታወቂያ ወይም ማንነታቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ዋናውንና ኮፒ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል::

1. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ከነሀሴ 17 ቀን 2013 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2013 ዓ.ም. ከሰኞ እስከ ዓርብ በሥራ ሰዓት ከአቃቂ ዕቃ ግምጃ ቤት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡

2. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ውጤቱ እንደታወቀ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) ለተጠቀሱት ለኩባኒያዉ ዕቃዎች የሚያቀርቡበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% (አምስት ከመቶ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
3. የጨረታ ማስከበሪያው ዋስትና ከታወቀ ባንክ ተረጋግጦ በሚቀርብ ሲፒኦ(CPO) መሆን አለበት፡፡
4. ተጫራቾች ለሽያጭ የቀረቡትን እቃዎች ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ እና የታደሰ መታወቂያ በመያዝ ከነሀሴ 14 ቀን 2013 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2013 ከቀኑ 11:00 ሰዓት ድረስ በአቃቂ እቃ ግ/ቤት በሚገኘው የድርጅቱ ዕቃ ግምጃ ቤት በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች የተጠቀሱትን ከኩባኒያዉ አገልግሎት የተመለሱ ዕቃዎችን የሚገዙበትን ዋጋ ቫትን (VAT) ጨምረው በዋጋ ማቅረቢያ ቦታው ላይ በማካተት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውን እና የጨረታውን ቁጥር በመጥቀስ በኢትዮ ቴሌኮም አቃቂ ዕቃ ግምጃ ቤት ጳጉሜ 5 ቀን 2013 ዓ. ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል::
6. ጨረታው ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአቃቂ እቃ ግ/ቤት መስከረም 3 ቀን 2014 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል ፡፡ሆኖም በመክፈቻው ቀንና ቦታ ተጫራቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ካልተገኙ እንደተገኙ ተቆጥሮ በተገኙት ተጫራቾች ፊት ያቀረቡት ሠነዶች ይከፈታሉ፡፡

7. ተጫራቾች በጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
8. ኢትዮ ቴሌኮም የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
9. ለተጨማሪ መረጃ አቃቂ በሚገኘው በኢትዮ ቴሌኮም ዕቃ ግምጃ ቤት ሥራ አስኪያጅ ቢሮ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር፡ 0911 508813 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል ፡፡

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives