ከውጭ ሀገራት የአየር ሰዓት እና ጥቅል ለሚቀበሉ ደንበኞቻችን ከዚህ በታች የተጠቀሱት ዝርዝር ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
- ከ99 ብር ጀምሮ የአየር ሰዓት እንዲሁም የሞባይል ጥቅል ስጦታ ከውጭ ሃገራት ሲቀበሉ የተቀበሉትን 50% በስጦታ ያገኛሉ
- ስጦታው የሚያገለግለው ለ30 ቀናት ብቻ ነው፡፡
- ስጦታውን ለቴሌኮም ፍጆታ ማለትም ለመደወል፣ መልዕክት ለመላክ እና ዳታ ለመጠቀም ወይም ለራስዎ ጥቅል በመግዛት መጠቀም ያስችላል፡፡
- ስጦታውን ወደ ሌላ ደንበኛ ማስተላለፍ አይችሉም
- በስጦታው ወደ አጭር ቁጥር ለመደወል፣ ዓለም አቀፍ ጥሪ ለማድረግ፣ ለሮሚንግ አገልግሎት ለመጠቀም፣ ለሌላ ደንበኛ ጥቅል በስጦታ ለመላክ እንዲሁም ከኢትዮ ቴሌኮም ኔትወርክ ውጪ ለመደዋወል አያገለግልም፡፡
- ስለተቀበሉት ስጦታ የማሳወቂያ መልዕክት በስልክዎ የሚደርስዎ ይሆናል፡፡
- እስከ ጥር 12/2017 ዓ.ም ድረስ ከውጭ አገራት ጥቅል እና አየር ሰዓት በመቀበል 50% በስጦታ ማግኘት ይችላሉ፡፡