ቪፒኤን አገልግሎት

  • ቪፒኤን የግል እና የመንግስት ተቋማት ከተለያዩ ቅርንጫፎቻቸው ጋር እንዲገናኙ የሚያደርግ ሲሆን ተቋማቱ የራሳቸውን የግል ኔትወርክ እንዲያደራጁ ያስችላቸዋል።
  • አገልግሎቱ መረጃን ለማጋራት እንዲሁም በቅርንጫፎች ውስጥ ያሉትን ሁሉንም የመረጃ ቴክኖሎጂ ስርዓቶችን በመደበኛ ወይም በተንቀሻቃሽ አማራጮች መተግበር ያስችላል።
  • አገልግሎቱ የሞባይል ኔትዎርክ ሽፋን ተደራሽ በሆነባቸው እና የዳታ አገልግሎትን በሚሰጡ በሁሉም ኢትዮጵያ ክፍሎች ይገኛል።
  • የቪፒኤን አገልግሎቶችን በሁለት አማራጭ የምናቀርብ ሲሆን እነዚህም

1.  የሞባይል ብሮድባንድ ቪፒኤን

2.  የፊክስድ ብሮድባንድ ቪፒኤን

ወርሃዊ የሞባይል ቪፒኤን ጥቅል አገልግሎቶች

ጥቅል ዋጋ
1 ጂቢ
60 ብር
2.5 ጂቢ
140 ብር
5 ጂቢ
250 ብር
8 ጂቢ
244 ብር
15 ጂቢ
589 ብር
20 ጂቢ
660ብር
ያልተገደበ
1300 ብር

  • ለአገልግሎቱ ለመመዝገብ የድርጅቶች በአቅራቢያቸው የሚገኝ የቢዝነስ አገልግሎት መስጫ ማዕከላችንን ይጎብኙ፡፡
  • ያልተገደበ ዓመታዊ የረጅም ጊዜ የሞባይል ቪፒኤን ጥቅል ለመግዛት ደንበኞች የአገልግሎት ክፍያውን ቀድመው መክፈል ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጥቅል መጠኑም በየ30 ቀናት በዓመት ለ12 ወራት ከተመዘገቡበት ቀን ጀምሮ የሚቀብላቸው ይሆናል፡፡ በዓመት ውስጥ ለአጠቃላይ 360 ቀናት አገልግሎቱን ያገኛሉ ማለት ነው፡፡
  • የረጅም ጊዜ የሞባይል ቪፒኤን ጥቅል መጠቀም የአሻምቴሌ ነጥብ አያስገኝም፡፡
  • ነባር የሞባይል ቪፒኤን ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚነት አላቸው፡፡

መደበኛ ብሮድባንድ ቪፒኤን

  • መደበኛ ባለገመድ እና ገመድ አልባ የብሮድባንድ የቪፒኤን አገልግሎት በዋናነት በMPLS (Multi-Protocol Labeled Switch) በኩል የሚቀርብ ሲሆን ይህም በተለያዩ ቦታዎች በሚገኙ የአንድ ድርጅት ቅርንጫፎችን ፤ የመረጃ ማዕከልን እና ዋናውን መ/ቤት በማገናኘት ደህንነቱ የተጠበቀ የመረጃ ፍሰት እንዲኖር ለማድረግ የሚያስችል በተመጣጣኝ ዋጋ የቀረበ አገልግሎት ነው፡፡

ጥቅሞች

  • ደህንነቱ የተጠበቀ የዳታ ወይም የመረጃ ፍሰት
  • በተለያየ ቦታ የሚገኙ የአንድ ድርጅት ቅርንጫፎችን ከአንድ ቦታ ላይ ሆኖ ለመቆጣጠር ወይም ለማስተዳደር የሚያስችል ነው
  • ለቢዝነስ ቀጣይነት ጠቀሜታው የጎላ ነው
  • የዕለት ተዕለት ስራ ማስኬጃ ወጪዎችን ለመቀነስ ያገለግላል

የመደበኛ ብሮድባንድ Local MPLS VPN ታሪፍ​

ተቁፍጥነትዋጋ
11 ሜጋ ቢትስ በሰከንድ 530
22 ሜጋ ቢትስ በሰከንድ 660
35 ሜጋ ቢትስ በሰከንድ 1,655
410 ሜጋ ቢትስ በሰከንድ 3,260
520 ሜጋ ቢትስ በሰከንድ 6,420
630 ሜጋ ቢትስ በሰከንድ 9,525
750 ሜጋ ቢትስ በሰከንድ 11,115
8100 ሜጋ ቢትስ በሰከንድ 23,285
9200 ሜጋ ቢትስ በሰከንድ 46,300
10300 ሜጋ ቢትስ በሰከንድ 69,060
11400 ሜጋ ቢትስ በሰከንድ 100,550
12500 ሜጋ ቢትስ በሰከንድ 113,778
13800 ሜጋ ቢትስ በሰከንድ 194,240
141024 ሜጋ ቢትስ በሰከንድ 226,000

ተጨማሪ መረጃዎች​

  • ከ1ጊ.ባ በሴኮንድ በላይ ላለው የአገልግሎት ፍጥነት መጠን ዋጋው፡-
  • Y= የ1 ጊ.ቢ በሴኮንድ ዋጋ + 200*(N-1024)
  • Y የተፈለገው የአገልግት ፍጥነት ዋጋ ጊ.ቢ በሴኮንድ ከተጨማሪ እሴት ጋር ነው
  • N የተጠየቀው የአገልግሎት ፍጥነት ነው፡፡
  • 200 በስሌቱ ውስጥ የማይለወጥ/ቋሚ ቁጥር ሲሆን የሜ.ቢ በሴኮንድ ታሪፍ ነው፡፡
  • የተጠየቀው የአገልግሎት ፍጥነት መጠን ከላይ ባለው ቀመር መሰረት በሜ.ቢ በሴኮንድ የሚሰላ ይሆናል፡፡
  • 1024 በቀመሩ ውስጥ የማይለወጥ/ቋሚ ቁጥር ሲሆን 1 ጊ.ባ በሴኮንድ ወደ ሜ.ቢ በሴኮንድ ሲቀየር ነው፡፡
  • የደንበኝነት ምዝገባ፣ በድጋሚ መስመር ለማገናኘት፣ የስም ለውጥ ለማድረግ፣ የባለቤትነት ለውጥ እንዲሁም የአድራሻ ለውጥ ከክፍያ ነፃ ናቸው፡፡

መደበኛ ገመድ አልባ ብሮድባንድ ቪፒኤን​

የፊክስድ ገመድ አልባ ብሮድባንድ ቪፒኤን ያለገመድ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ነገር ግን  በተመረጡ ቦታዎች ብቻ የተገደበ አገልግሎት ነው፡፡ አገልግሎቱ በAironet ወይም VSAT አማራጮ ይሰጣል።

ጥቅሞች

  • የቢዝነስ ቀጣይነትን ለማረጋገጥ እንደ ተጨማሪ መጠባበቅያ የገመድ አልባ አማራጭ ያገለግላል
  • የዕለት ተዕለት ስራ ማስኬጃ ወጪዎችን ለመቀነስ ያገለግላል
  • ባለገመድ ኔትወርክ በሌለበት አካባቢ ስራዎችን ለማከናወን ይረዳል
  • አገልግሎትን በቀላሉ የማሳደግ አቅም ይፈጥራል – ደንበኞች አዳዲስ ቦታዎችን፣ ተጠቃሚዎችን እና መተግበሪያዎችን በፍጥነት ለማገኛኝት ይረዳቸዋል፡፡
  • በከፍተኛ ደረጃ የማዳረስ አቅም መኖር
  • ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑ እና ደንበኞች አገልግሎቱን በሚፈልጉት መልኩ እንዲቆጣጠሩት ማስቻሉ፡፡ ደንበኞች አገልግሎቱን ለማስተዳደር የራሳቸውን የደህንነት ፓሊሲ በማዘጋጀት የትኞቹ ተጠቃሚዎች የትኛውን የኔትወርክ ክፍል መጠቀም እንዳለባቸው መከታተል እና መቆጣጠር ያስችላቸዋል፡፡

FIXED LOCAL WIRELESS MPLS -VPN via VSAT

የፍጥነት አማራጭ (በሴኮንድ) የበፊቱ ወርሃዊ ታሪፍ አዲሱ ወርሃዊ ታሪፍ
512 ኪሎ ባይት 14,517.19 13,040
1 ሜ.ባ 27,465.21 14,735
2ሜ.ባ 53,361.25 20,629
4 ሜ.ባ አዲስ አገልግሎት 28,880
5 ሜ.ባ አዲስ አገልግሎት 31,768
የድሮው አዲሱ
የምዝገባ ክፍያ 54,942.80 41,923

ተጨማሪ መረጃዎች​

  • ለVSAT ብሮድባንድ ድምጽ + ቪፒኤን አገልግሎት፣ የድምፅ ምዝገባ እና የኪራይ ክፍያ ከቪፒኤን የደንበኝነት ምዝገባ እና የኪራይ ክፍያ ላይ ተጨማሪ ያስከፍላል፡፡
  • የድምፅ አገልግሎት ብቻውን አይቀርብም፡፡
  • የድምጽ አገልግሎት ጥያቄ ለሚያቀርብ አንድ ደንበኛ ስድስት የድምፅ መስመሮች ይሰጡታል፡፡
  • የድምጽ ደንበኝነት ምዝገባ እና የአጠቃቀም ታሪፍ ከመደበኛ የስልክ አገልግሎት ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡
  • ይህ ታሪፍ የወርሀዊ የአገልግሎት ክፍያን አያካትትም፡፡
  • ሁሉም ታሪፎች የተ.እ.ታን ያካትታሉ፡፡
  • የደንበኝነት ምዝገባ ክፍያ የቴምብር ቀረጥ ክፍያን ያካተተ ነው፡፡