ዕሴት ጨማሪ አገልግሎቶች (VAS)

ከተለያዩ ዕሴት ጨማሪ  አገልግሎት አማራጮች መካከል የፈለጉትን መርጠው ይጠቀሙ!

የ VoLTE አገልግሎት

እንኳን ወደ ላቀ የግንኙነት ዓለም በደህና መጡ!

ታይቶ የማይታወቅ የጥሪ ልምድ VoLTE ይጎናፀፉ!

የቮልቲኢ (VoLTE) የሚያስጠቅሙ የሞባይል አይነቶች

S.NSamsung
1Samsung Galaxy Fold 5G
2Samsung Galaxy Z Flip 5
3Samsung Galaxy Z Flip 5 (8GB RAM + 512GB)
4Samsung Galaxy Z Fold 5
5Samsung Galaxy Z Fold 5 (12GB RAM + 1TB)
6Samsung Galaxy Z Fold 5 (12GB RAM + 512GB)
7Samsung Galaxy Z Flip 4 5G
8Samsung Galaxy Z Flip 4 (8GB RAM + 256GB)
9Samsung Galaxy Z Flip 4 (8GB RAM + 512GB)
10Samsung Galaxy Z Fold 4
11Samsung Galaxy Z Fold 4 (12GB RAM + 512GB)
12Samsung Galaxy Z Flip
13Samsung Galaxy A53 5G
14Samsung Galaxy A53 5G (8GB RAM + 128GB)
15Samsung Galaxy Z Flip 3
16Samsung Galaxy Z Fold 3
17Samsung Galaxy A54 5G
18Samsung Galaxy A54 5G (8GB RAM + 256GB)
19Samsung Galaxy A34 5G
20Samsung Galaxy A34 5G (8GB RAM + 128GB)
21Samsung Galaxy A34 5G (8GB RAM + 256GB)
22Samsung Galaxy A73 5G
23Samsung Galaxy A73 5G (8GB RAM + 256GB)
24Samsung Galaxy S21 5G (8GB RAM + 256GB)
25Samsung Galaxy S21 FE 5G
26Samsung Galaxy S21 FE 5G (8GB RAM + 256GB)
27Samsung Galaxy S21 Plus
28Samsung Galaxy S21 Plus 5G (8GB RAM + 256GB)
29Samsung Galaxy S21 Ultra
30Samsung Galaxy S21 Ultra 5G (12GB RAM + 128GB)
31Samsung Galaxy S21 Ultra 5G (16GB RAM + 512GB)
32Samsung Galaxy S22 5G
33Samsung Galaxy S22 5G (8GB RAM + 256GB)
34Samsung Galaxy S22 Plus 5G
35Samsung Galaxy S22 Plus 5G (8GB RAM + 256GB)
36Samsung Galaxy S22 Ultra 5G (12GB RAM + 512GB)
37Samsung Galaxy S22 Ultra 5G (8GB RAM + 128GB)
38Samsung Galaxy S23 5G
39Samsung Galaxy S23 Plus 5G
40Samsung Galaxy S23 Ultra 5G
41Samsung Galaxy S21
42Samsung Galaxy S21 FE (Snapdragon)
43Samsung Galaxy Note 20 5G
44Samsung Galaxy Note 20 Ultra 5G
45Samsung Galaxy-A52s-5G
46Samsung Galaxy-M52-5G AE TSSMMEA_13
47Samsung Galaxy A23 5G
48Samsung Galaxy A32 5G
49Samsung Galaxy A22 5G
50Samsung Galaxy A22e 5G
51Samsung Galaxy A33 5G
52Samsung Galaxy A33 5G (8GB RAM + 128GB)
53Samsung Galaxy A52 5G
54Samsung Galaxy A71 5G
55Samsung Galaxy A72 5G
56Samsung Galaxy S20 5G
57Samsung Galaxy S20 5G UW
58Samsung Galaxy S20 FE 5G
59Samsung Galaxy S20 Plus 5G
60Samsung Galaxy S20 Ultra 5G
61Samsung Galaxy A51 5G
62Samsung Galaxy Note 10 Plus 5G
63Samsung Galaxy S10 5G
64Samsung Galaxy A14 5G
65Samsung Galaxy A14 5G (6GB RAM + 128GB)
66Samsung Galaxy A14 5G (8GB RAM + 128GB)
67Samsung Galaxy A24 5G
68Samsung Galaxy A13 5G
69Samsung Galaxy M23 5G
70Samsung Galaxy M54 5G
71Samsung Galaxy M14 5G
S.NIphone
1Apple A2402/Apple iPhone 12
2Apple A2403/Apple iPhone 12
3Apple A2404/Apple iPhone 12
4Apple A2398/Apple iPhone 12 Mini
5Apple A2399/Apple iPhone 12 Mini
6Apple A2400/Apple iPhone 12 Mini
7Apple A2341/Apple iPhone 12 PRO
8Apple A2406/Apple iPhone 12 PRO
9Apple A2407/Apple iPhone 12 PRO
10Apple A2408/Apple iPhone 12 PRO
11Apple A2342/Apple iPhone 12 PRO MAX
12Apple A2410/Apple iPhone 12 PRO MAX
13Apple A2411/Apple iPhone 12 PRO MAX
14Apple A2412/Apple iPhone 12 PRO MAX
15Apple A2482/Apple iPhone 13
16Apple A2631/Apple iPhone 13
17Apple A2633/Apple iPhone 13
18Apple A2634/Apple iPhone 13
19Apple A2635/Apple iPhone 13
20Apple A2629/Apple iPhone 13 Mini
21Apple A2626/Apple iPhone 13 Mini
22Apple A2628/Apple iPhone 13 Mini
23Apple A2481/Apple iPhone 13 Mini
24Apple A2630/Apple iPhone 13 Mini
25Apple A2483/Apple iPhone 13 PRO
26Apple A2636/Apple iPhone 13 PRO
27Apple A2638/Apple iPhone 13 PRO
28Apple A2639/Apple iPhone 13 PRO
29Apple A2640/Apple iPhone 13 PRO
30Apple A2484/Apple iPhone 13 PRO MAX
31Apple A2641/Apple iPhone 13 PRO MAX
32Apple A2643/Apple iPhone 13 PRO MAX
33Apple A2644/Apple iPhone 13 PRO MAX
34Apple A2645/Apple iPhone 13 PRO MAX
S.NTecno
1Tecno Telecom CK9N/Camon 20 Premier 5G
2Tecno Telecom CK8N/Camon 20 PRO 5G
3Tecno Telecom CI7N/Camon 19 PRO 5G
4Tecno Telecom AD10/Phantom V Fold
5Tecno Telecom AD8/Phantom X2 5G
6Tecno Telecom AD8/Phantom X2 5G
S.NZTE
1ZTE A7040/ZTE Blade A72/ZTE Blade V40 Smart
2ZTE 7540N/ZTE Blade A72 5G/ZTE Blade V40 Smart 5G
3ZTE 8040N/ZTE YH20 5G/ZTE YH20CX 5G
4ZTE 8040N/ZTE YH20 5G/ZTE YH20CX 5G
5ZTE A2022/ZTE A30/ZTE AXON 30
6ZTE 8030N/ZTE S30 SE 5G
7ZTE 7531N/ZTE A71S 5G
8ZTE A2020N3/ZTE Stage 5G
9ZTE A2021G/ZTE Axon 11 5G
10ZTE 8012N/ZTE BLADE 20 5G/ZTE Blade V2021 5G
11ZTE 9030N/ZTE S30 5G
12ZTE 8140N/ZTE Blade V41 Vita 5G
13ZTE A2023/ZTE Axon 40/ZTE Axon 40 PRO 5G
S.NInfinix
1Infinix X6815C/Zero 5G 2023
2Infinix X6820/Zero Ultra
3Infinix X666B/HOT 20 5G
4Infinix X6711/Infinix Note 30 5G
5Infinix X673/Note 12 PRO 5G
6Infinix X6710/Note 30 VIP
7Infinix X666/HOT 20 5G
8Infinix X6832/HOT 30 5G

ጥያቄ1: VoLTE አገልግሎት ምንድነው?

  • የ VoLTE አገልግሎት ለሁሉም ደንበኞቻችን የቀረበ ሲሆን ከፍተኛ ጥራት ያለው የድምፅ ጥሪ የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ ኔትወርክን በመጠቀም ለማድረግ የሚያስችል አገልግሎት ነው፡፡ ከመደበኛው የ2ጂ/3ጂ ኔትወርክ ከሚጠቀም የድምፅ ጥሪ የሚለየው የ VoLTE አገልግሎት የድምፅ ጥሪን ለማስተላለፍ የዳታ አገልግሎት መጠቀሙ ነው፡፡

ጥያቄ2: 4 እና VoLTE መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው?

  • 4ጂ- ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የዳታ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን VoLTE ደግሞ የኤል.ቲ.ኢ ኔትወርክን በመጠቀም የላቀ ጥራት ያለው የድምፅ ጥሪ ለመስጠት በልዩነት የቀረበ አገልግሎት ነው፡፡

ጥያቄ3: VoLTE አገልግሎት ጥቅሞች ምን ምን ናቸው?

  • VoLTE ከመደበኛው የድምፅ ጥሪ የተለየ የሚያደርገው የድምፅ እና የቪዲዮ ጥሪን በላቀ ጥራት ማድረግ ማስቻሉ፣ ጥሪዎችን በፍጥነት ማድረሱ፣ የድምፅ እና የዳታ አገልግሎትን በተመሳሳይ ጊዜ ማስጠቀሙ እንዲሁም የባትሪ የቆይታ ጊዜን የተሻለ እንዲሆን ማስቻሉ ነው፡፡

ጥያቄ4: VoLTE አገልግሎትን ማን መጠቀም ይችላል?

  • የ VoLTE አገልግሎትን መጠቀም የሚያስችል የስልክ ቀፎ ያላቸው የድህረ ክፍያ፣ ቅድመ ክፍያ እና ሀይብሪድ የ4ጂ ኔትወርክ ሞባይል ደንበኞች በሙሉ የሚችሉ ሲሆን ዳታ ብቻ የሚያስጠቅም ሲም ካርድ ያላቸው ደንበኞችን ግን አያካትትም፡፡

ጥያቄ5: VoLTE አገልግሎትን ለማግኘት መስፈርቱ ምንድነው?

  • ደንበኞች VoLTE አገልግሎትን የሚያስጠቅም የሞባይል ቀፎ ከ4ጂ/5ጂ ሲም ካርድ ሊኖራቸው የሚገባ ሲሆን የሚገለገሉበት ቀፎ ከእጅ ስልክ አምራቹ በቅርብ ጊዜ ሶፍትዌር ማዘመን፣ የ4ጂ/5ጂ ኔትወርክ ሽፋን የሚያገኝ አካባቢ መሆን እንዲሁም በሞባይላቸው አገልግሎቱን ለመጠቀም ማስጀመር (Turn On) ማድረግ አለባቸው፡

ጥያቄ6: ሁሉም ስማርት ስልኮች የ VoLTE አገልግሎትን ያስጠቅማሉ?

  • ሁለም ስማርት ስልኮች አገልግሎቱን ስለማያስጠቅሙ በቅድሚያ የሞባይል ቀፎው የ4ጂ/5ጂ ኔትወርክ የሚያስጠቅም መሆኑን ያረጋግጡ፡፡

ጥያቄ7: ቀፎዬ የ VoLTE አገልግሎት እንደሚያስጠቅም/እንደማያስጠቅም በምን ማረጋገጥ እችላለሁ?

  • የስልክዎ መቼት (Settings) ውስጥ በመግባት መመልከት ይችላሉ፡፡ የ VoLTE አገልግሎትን በስልክዎ መቼት ውስጥ ለማግኘት የታች ያሉትን መመሪያ ይመልከቱ!

ለአንድሮይድ ስልክ

  • ከስልክዎ ማውጫ "Settings" ይምረጡ
  • በመቀጠል "Connections" ወይም "Network & Internet" የሚለውን ይምረጡ
  • "Mobile Networks" ወይም "Cellular Networks"የሚለውን አማራጭ ይክፈቱ
  • ቀጥሎ "VoLTE" ወይም "HD Calling" ወይም "Enhanced 4G LTE Services" የሚሉ ምርጫዎች ከተመለከቱ አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ ማለት ነው፡፡

 

በአይኦኤስ (አይፎን)

  • የ "Settings"መተግበሪያውን ይክፈቱ
  • "Cellular" ወይም "Mobile Data" የሚለውን ይጫኑ
  • "Cellular Data Options" የሚለውን ይምረጡ
  • "Voice & Data" የሚለውን ይክፈቱ
  • "LTE" ወይም "Data Only" የሚለውን በመምረጥ አገልግሎቱን ያስጀምሩ

ጥያቄ8: በ VoLTE አገልግሎት ዳታ ስጠቀም ይቆጥራል?

  • አይቆጥርም፤ VoLTE የድምፅ አገልግሎት ሲሆን ምንም አይነት ዳታ አይጠቀምም፡፡ ጥሪዎችም በመደበኛው የጥሪ ታሪፍ መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡

ጥያቄ9: በ VoLTE የቪዲዮ ጥሪ በማደርግበት ወቅት የዳታ ጥቅል ያስፈልገኛል?

  • አያስፈልግዎትም፤ ደንበኞች የቪዲዮ ጥሪውን ያለምንም ዳታ አገልግሎት ማድረግ ይችላሉ፡፡ የቪዲዮ ጥሪው በመደበኛ የጥሪ ታሪፍ መሰረት ተሰልቶ ከአየር ሰዓት ወይም ካሎት የድምፅ ጥቅል ተቆራጭ ይሆናል፡፡

ጥያቄ10: በ VoLTE ጥሪ በሚደረግበት ጊዜ መደበኛው ታሪፍ ስንት ነው?

  • በኢትዮ ቴሌኮም ኔትወርክ የድምፅ/ቪዲዮ ጥሪ ሲያደርጉ
    • በመደበኛ ሰዓት 50 ሣንቲም/በደቂቃ
    • ከመደበኛ ሰዓት ውጪ 0.35 ሣንቲም በደቂቃ
  • ከኢትዮ ቴሌኮም ኔትወርክ ውጪ የድምፅ ጥሪ ሲያደርጉ
    • በመደበኛ ሰዓትም ሆነ ከመደበኛ ሰዓት ውጪ75 ሣንቲም በደቂቃ

ጥያቄ11: የ VoLTE አገልግሎትን ለዓለም አቀፍ ጥሪ መጠቀም እችላለሁ?

  • ይህ አገልግሎት የሚሰራው ለሀገር ውስጥ ጥሪ ብቻ ነው፡፡

ጥያቄ12: የ VoLTE አገልግሎትን ለዓለም አቀፍ ጥሪ መጠቀም እችላለሁ?

  • ይህ አገልግሎት የሚሰራው ለሀገር ውስጥ ጥሪ ብቻ ነው፡፡

ጥያቄ13: የVoLTE ጥሪ በማድረግ ላይ እያለሁ የ4ጂ/5ጂ ኔትወርክ ሽፋን የሌለበት አካባቢ ውስጥ ብገባ ምን ይፈጠራል?

  • እያደረጉት ያለው ጥሪ በ VoLTE ቢሆንም የኔትወርክ ሽፋኑ 4ጂ/5ጂ የሌለበት አካባቢ ከገቡ የ3ጂ/2ጂ ኔትወርክን በመጠቀም ንግግርዎ ሳይቋረጥ ይጠቀማሉ፡፡

ጥያቄ14: የVoLTE አገልግሎት እየተጠቀምኩ መሆኑን በምን ማረጋገጥ እችላለሁ?

  • የአንድሮይድ ተጠቃሚ ከሆኑ “HD/VoLTE” የሚል ምልክት ከላይ የስልክዎ ስክሪን ላይ ይታያል
  • የአይኦኤስ ተጠቃሚ ከሆኑ ምንም የሚታየ ምልክት አይመጣም፤ ነገር ግን የስልክዎ መቼት ውስጥ በመግባት በጥያቄ ቁጥር 7 መሰረት መመልከት ይችላሉ፡፡

 

ጥያቄ15: የVoLTE አገልግሎት በሁሉም ቦታ ይገኛል?

  • አገልግሎቱ የሚሰራው የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ ወይም 5ጂ ኔትወርክ ሽፋን ባላቸው አካባቢዎች ነው፡፡

ጥያቄ16: የVoLTE አገልግሎት በሁሉም ቦታ ይገኛል?

  • አገልግሎቱ የሚሰራው የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ ወይም 5ጂ ኔትወርክ ሽፋን ባላቸው አካባቢዎች ነው፡፡

ጥያቄ17: የ VoLTE አገልግሎት እንዲሰራ ተቀባዩም ደዋዩም አገልግሎቱ ሊኖራቸው ግዴታ ነው?

  • ▪ የድምፅ ጥሪ ለማድረግም ሆነ ለመቀበል VoLTE ያደረገው ደንበኛ ሌላኛው ደንበኛ ቢያደርግም ባያደርግም አገልግሎቱን ያገኛል፡፡ የቪዲዮ ጥሪ ለማድረግ ግን ሁለታችሁም አገልግሎቱ ሊኖራችሁ ይገባል፡፡

መልቲሚዲያ መልዕክት አገልግሎት

ፅሁፍ፣ ምስል፣ የድምፅ ቅጂዎችን፣ ፋይሎችን፣ ኦዲዮና ቪዲዮ ክሊፖችን በመላላክ ከጓደኛ፣ ቤተሰብ፣ ወዳጅ እና ከስራ ባልደረባዎችዎ ጋር አይረሴ ትዝታዎችን የመልዕክት አገልግሎት በመጠቀም ብቻ ለመፍጠር ያስችላል፡፡

Tap *Settings*.
Tap *SIM cards & mobile networks*.
Under *SIM CARD SETTINGS*, Tap the desired SIM card.
Tap *Access Point Names*.
Tap *New APN*.
The *New Access Point* window opens.
Type MMS in *Name* field then tap *OK*.
Type mms.et in *APN* field then tap *OK*.
Do not type anything in field in *Proxy* field
Do not type anything in field in *Port* field
Type ethio in *Username* field then tap *OK*.
Type ethio in *Password* field then tap *OK*.
Type http://ethiomms.et in *MMSC* field then tap *OK*.
Type 10.1725.226.163 in *MMSC Proxy* field then tap *OK*.
Type 7080 in *MMSC Port* field then tap *OK*.
Do not type anything in field *Authentication type*.
Type mms in *APN type* field then tap *OK*.
Choose IPv4 in *APN protocol* field then tap *OK*.
Choose IPv4 in *APN roaming protocol* field then tap *OK*.
Tap *More*.
Tap *Save*.

አገልግሎቱን ማን መጠቀም ይችላል?

  • ለሁሉም የድህረ እና ቅድመ ክፍያ እንዲሁም ሀይብሪድ ደንበኞቻችን የቀረበ አገልግሎት ነው፡፡

አገልግሎቱን እንዴት ማስጀመር ይቻላል?

  • የስልክዎን ‘’setting’’ ማስተካከል ሳይጠበቅብዎ አማራጩን ለሁሉም ደንበኞቻችን አስጀምረናል፡፡ ከእርስዎ የሚጠበቀው የመልዕክት ሳጥንዎን በመክፈት አማራጮቹን መጠቀም ብቻ ነው፡፡

ሌላስ?

  • በአንድ ጊዜ ከአንድ በላይ ለሆኑ ደንበኞች የመልቲሚዲያ መልዕክቶችን መላክ ይችላሉ፡፡

ስልክዎ ዝግ ሆነ መልዕክት ቢላክልዎት እስከ 48 ሰዓታት ባለው ጊዜ ውስጥ ያገኙታል፡፡

ጉግል RCS መልዕክት

ስሜትዎን በኢሞጂ፣ ጥሩ ጊዜን በፎቶ፣ መገኛዎን፣ ቪዲዮ እና የድምፅ ቅጂ አንድ ለአንድ ወይም በቡድን ያለገደብ በመልዕክት ማጋራት ያስችላል፡፡ ከእርስዎ የሚጠበቀው የGoogle Messaging መተግበሪያን አውርደው መጠቀም መጀመር ብቻ ነው፡፡

አገልግሎቱን ለማስጀመር
  1. “Google Messages’’ መተግበሪያን ከጉግል አፕ ስቶር ያውርዱ
  2. የጂሜል አካውንትዎን በማስገባት ዋና የመልዕክት መቀበያ እና መላኪያ እንዲሆን ይፍቀዱ
  3. በመተግበሪያው ከላይ በቀኝ በኩል ‘’Messages settings’’ የሚለውን ይምረጡ
  4. ‘’General’’ የሚለውን በመጫን በመቀጠል ‘’RCS Chats’’ የሚለውን ይምረጡ
  5. ‘’Verify Your Number’’ የሚለውን በመምረጥ የሞባይል ቁጥርዎን በማስገባት ይጨርሱ

መልቲ ነምበር

ደንበኞች እስከ 5 የሚደርሱ የሞባይል ቁጥሮችን በአንድ ሲም ካርድ እንዲገለገሉ የሚያደርግ አገልግሎት ነው፡፡

አገልግሎቱ የደንበኛውን ሙሉ መረጃ የያዘ አንድ ዋና ቁጥር የሚኖረው ሲሆን እስከ 4 የሚደርሱ ሁለተኛ ተጨማሪ ቁጥሮች አብረውት የሚሸጡ ይሆናል፡፡

1 ዋና ቁጥር እስከ 4 ከሚደርሱ ሁለተኛ ተጨማሪ ቁጥሮች ጋር በአንድ ሲም

ዋጋ

  • የዋና ቁጥር ለመመዝገብ– 30 ብር

በድጋሚ ለማውጣት—15 ብር

  • እስከ 5 ለሚደርሱ ተጨማሪ ቁጥሮች ለመመዝገብ—የአንዱ ዋጋ 12 ብር

በድጋሚ ለማውጣት— ነፃ

  • ለድህረ ክፍያ ተጠቃሚዎች የተጨማሪ ቁጥሮች ወርሃዊ ኪራይ–ነፃ

ማስታወሻ

  • ለአገልግሎቱ ለመመዝገብ ነባር ቁጥርዎን መጠቀም ወይም አዲስ ቁጥር እንዲሰጥዎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  • ዋናው ቁጥርዎን ብቻ ተጠቅመው የአየር ሰዓት/ጥቅል መግዛት የሚቻል ሲሆን ሌሎች ተጨማሪ ቁጥሮችዎ የዋናው ቁጥር የገዛውን አገልግሎት መጠቀም እንጂ መግዛት አይችሉም፡፡
  • ተጨማሪ ቁጥሮችዎ በራሳቸው ጥሪ መቀበል/መደወል፣ የፅሁፍ መልዕክት መላክ/መቀበል እንዲሁም ዳታ መጠቀም ይችላሉ፡፡

የመልቲ ነምበር አገልግሎትን ለማስተዳደር የሚረዱ አጭር ቁጥሮች

አገልግሎት የአጭር ቁጥር ትዕዛዝ
የሁለተኛ/ተጨማሪ የአገልግሎት ቁጥሮችዎን ለማስጀመር *136*2# ይደውሉ
     ቀጥሎ መለያ ቁጥር 1/2/3/4/ እንደምርጫዎ ያስገቡ
     ወይም *136#2519XXXXXXXX ይደውሉ
በመረጡት   የአገልግሎት ቁጥር የሚመጣውን ገቢ ጥሪ ለመገደብ *135# ይደውሉ
ያገዱትን   አገልግሎትን ቁጥር እገዳውን ለማንሳት *135* ይደውሉ
ሁሉንም   የአገልግሎት ቁጥሮችዎን በሞባይል ስክሪንዎ ለመመልከት *138# ይደውሉ

  • ሁሉም የግለሰብ እንዲሁም የድርጅት አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ቅድመ ክፍያ፣ ድህረ ክፍያ እና ሀይብሪድ ቁጥሮች መልቲ ነምበር አገልግሎትን ለመጠቀም ብቁ ናቸው፡፡
  • የመልቲ ሲም አገልግሎት የሚጠቀሙ እንዲሁም የቡድን አገልግሎቶችን ማለትም ሲዩጂ፣ የወዳጅ ዘመድ ጥቅል እንዲሁም በቋሚነት አገልግሎት የሚያጋሩ እና በማጋራት የሚጠቀሙ ደንበኞች የመልቲ ነምበር አገልግሎትን መጠቀም አይችሉም፡፡
  • ከዋናው የአገልግሎት ቁጥር በተጨማሪ አንድ ደንበኛ ማውጣት የሚችለው ሁለተኛ/ተጨማሪ ቁጥሮች የተፈቀደው ከፍተኛው ብዛት 4 ሲሆን ከዋናው ቁጥር ጋር አገልግሎቶችን እና አካውንት በመጋራት አገልግሎት የሚሰጡ ይሆናል፡፡
  • ሁለተኛ/ተጨማሪ ቁጥሮች የሚኖራቸው የአገልግሎት ጊዜ እና ሁኔታ ከዋናው ቁጥር ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡

ለምሳሌ፡ ዋናው ቁጥር በቂ የአገልግሎት ዘመን ሳይኖረው ወይም በተለያየ ምክንያት ወጪ ጥሪ እንዳያደርግ ቢታገድ ሁሉተኛ/ተጨማሪ ቁጥሮቹም በሙሉ በተመሳሳይ መልኩ ይታገዳሉ፡፡ ነገር ግን ዋናው ቁጥር የአየር ሰዓት በመሙላት ወደ አገልግሎት ከተመለሰ ሌሎቹም ተጨማሪ ቁጥሮች በተመሳሳይ ወደ አገልግሎት ይመለሳሉ፡፡

  • የሁለተኛ/ተጨማሪ ቁጥሮች የአከፋፈል ሁኔታ በዋናው ቁጥር የአከፋፈል ሁኔታን መሰረት ያደረገ እንጂ የተለያየ የአከፋፈል ሁኔታ ሊኖራቸው አይችልም፡፡ ለምሳሌ፡ ዋናው ቁጥር ድህረ ክፍያ ከሆነ እሱን መሰረት አድርገው የሚወጡት ሁለተኛ/ተጨማሪ ቁጥሮች በሙሉ ድህረ ክፍያ ይሆናሉ ማለት ነው፡፡
  • የተለያዩ አገልግሎቶች ማለትም የአየር ሰዓት፣ የጥቅል ሀብት (ያልተገደበ ጥቅልን ጨምሮ) በሙሉ በዋናው ቁጥር ላይ ብቻ የሚገኙ ሲሆን ሁለተኛ/ተጨማሪ ቁጥሮቹ ከዋናው ቁጥር ላይ የተቀጡትን አገልግሎቶች ተጋርተው ይጠቀማሉ፡፡
  • በጊዜያዊነት የሁለተኛ/ተጨማሪ ቁጥሮችን በመጠቀም ደንበኞች ጥሪ መቀበል/መደወል፣ መልዕክት መላክ/መቀበል እንዲሁም ዳታ መጠቀም ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም ከሶስተኛ ወገን ስጦታ መቀበል፣ የጥሪ ማቆያ እና የጥሪ ማስተላለፍ አገልግሎት ማግኘት ይቻላል፡፡
  • አገልግሎቱን ከገዙ በኋላ የባለቤትነት ለውጥ ማድረግ እና የአከፋፈል ሁኔታ መቀየር አይችሉም፡፡ በተጨማሪም በቡድን የሚገኙ አገልግሎቶችን ማለትም መልቲ ሲም፣ ሲዩጂ እና የወዳጅ ዘመድ ጥቅል አገልግሎት ለመጠቀም አይችሉም፡፡
  • ለጊዜው ቴሌብር እና ጥሪ ማሳመሪያ መመዝገብ፣ ጥቅል መግዛት፣ ጥቅል ማስተላለፍ እና መቀየር፣ አሻምቴሌ፣ ማይ ኢትዮቴል መተግበሪያ መጠቀም ለሁለተኛ ሲም ካርዶች አልተፈቀደም፡፡
  • ዋናውንና ተጨማሪ ቁጥሮችዎን የያዘው ሲም ካርድ ቢጠፋብዎ ዋናውን ቁጥር ብቻ አንዲዘጋልዎ በመጠየቅ ተጨማሪ ቁጥሮቹም አብረው የሚዘጉ ይሆናል፡፡ እንዲሁም በድጋሚ ሲያወጡ ወይም ሲያስከፍቱ ሁሉም ቁጥሮች በተመሳሳይ ጊዜ አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ፡፡

Magic Voice and Background

Music

It is a service enabling customers to change their voice into different voice sounds and add different background music while speaking to their friends or families.

  • Magic voice allows the customer to change their voice over a phone call. They can sound like a baby, an old man/woman, a cartoon character, or the opposite of themselves.
  • Background Music Service (BGM) is a fun-based service that allows a mobile caller to add a background music automatically and lets them speak to their friends or families with the selected background music playing.

Current Available Music Voice and BGM contents

  • Queen Voice
  • King-Voice
  • Carton-Voice
  • Traffic Ambiance
  • Birthday Ambiance
  • Football Ambiance

NB: Additional tone contents will be added on demand basis

እለታዊ የማጂክ ቮይስ ዋጋ

3ብር

ሳምንታዊ የማጂክ ቮይስ ዋጋ

15ብር

ወርሃዊ የማጂክ ቮይስ ዋጋ

18ብር

    • The service is available for all prepaid, postpaid and hybrid mobile users.
    • The service does not apply for calls made to roaming service subscribers.
    • The service works for local calls made from mobile to mobile/Fixed/CDMA services.
    • To use the service customers shall register for the service first. After registration, the caller shall dial “604Receiver Mobile Number”. Eg: 60409********
    • The voice charging shall start after 25 seconds (i.e. there will not be any charging for the 25 seconds within the call). The receivers would not be charged any tariff.
    • Subscription and un-subscription for the service is free.
    • User can select the Voice or Background music from pre-recorded voice or music. There is no charge while user browse and select a magic or background from the catalogue when the caller uses the service by selecting Magic voice or Background music.

Life Cycle of the Services

    • If customer do not have enough balance to pay the daily or weekly or monthly service subscribed after normal service time, subscriber will enter Grace period (7 days) while using the service and system shall wait till, they have the required balance to charge. With this stage they can access the 604 IVR and use the default voice changer.
    • If the customer does not have balance within the 7 days of the grace period, they will enter the suspension period (60 days) where they cannot use the service at all, and service suspended.
    • At last, if the customer did not pay within the suspension period, they will be automatically terminated from the service.
    • If customers fail to pay monthly rental fee, the system will let them use the weekly package to enable user can access the service for 7 days’ and minimize the user experience impact. This shall be applied in case the charging is failed for weekly service as well.

በተለያዩ አካባቢዎች ከሚገኙ እስከ አምስት የሚደርሱ ተጠቃሚዎችን የሚያካትት የስራ ወይም የማህበራዊ ጉዳይ ስብሰባ/ ውይይት የኮንፈረንስ ጥሪ አገልግሎትን በመጠቀም በቀላሉ ያካሂዱ

የኮንፈረንስ ጥሪ አገልግሎት አጠቃቀም

  • ወደ መጀመሪያው ቁጥር ይደውሉ
  • ስልኩ እስኪነሳ ይጠብቁ
  • የደወሉላቸውን ደንበኛ ሆልድ (hold) ላይ በማድረግ ለሁለተኛውን ቁጥር ለመደወል አድ ኮል (add call) የሚለውን ይንኩ
  • ሁለተኛውን ቁጥር በመደወል እስኪነሳ ይጠብቁ
  • “conference” ወይም “Merge call” የሚለውን ሲመርጡ ከደወሉላቸው ሁለቱም ደንበኞች በጋራ ማውራት ይችላሉ
  • ተጨማሪ ሰዎችን ወደ ኮንፈረንስ ጥሪዎ ለማካተት ከቅደም ተከተሉ ከ3ኛ እስከ 5ኛ ያሉትን ትዕዛዛት ይድገሙ

የአገልግሎት ዋጋ

  • የደወሏቸው ጥሪዎች በሙሉ በመደበኛው የድምፅ ጥሪ አገልግሎት ዋጋ ተሰልተው አጠቃላይ ድምሩን ይከፍላሉ

ያሎት ሂሳብ አነስተኛ ቢሆንም ወይም በአገልግሎት ጊዜው በማብቃቱ ወጪ ጥሪ ማድረግ ባይችሉም ለፈለጉት ደንበኛ ሲደውሉ በቀጥታ ወደፈለጉት ደንበኛ ሲደውሉ ምልክት (Missed Call) በ710 ከማሳወቂያ መልዕክት ጋር እናደርስልዎታለን!
ደንብና ሁኔታዎች
• አገልግሎቱ ምንም/አነስተኛ ሂሳብ ላላቸው ቅድመ ክፍያ ደንበኞች እንዲሁም በክፍያ ምክንያት ወጪ ጥሪ ማድረግ ለማይችሉ የድህረ ክፍያ ደንበኞች በነፃ የቀረበ አገልግሎት፡፡
• ሁሉም የቅድመ ክፍያ፣ ድህረ ክፍያ እንዲሁም ሀይብሪድ ደንበኞች ቢፕ ኮል መቀበል ይችላሉ፡፡
• አገልግሎቱ ለሀገር ውስጥ ጥሪዎች ብቻ የሚያገለግል ነው፡፡
• አገልግሎቱን በቀን መጠቀም የሚችሉት ከፍተኛው ብዛት 8 ነው፡፡

በአንድ ጊዜ እስከ አምስት ሰዎችን የሚያካትት የቡድን ጥሪ ያድርጉ፤ መራራቅ ሳይገድብዎ ስራዎን ያቀላጥፉ።

የኮንፈረንስ ጥሪ ለማድረግ

  • የመጀመሪያውን ስልክ ይደውሉ
  • የደወሉላቸው ደንበኛ ስልኩን ሲያነሱ በመስመር ላይ በማቆየት (ጥሪውን Hold በማድረግ) “Add call” የሚለውን ተጭነው ለቀጣዩ የኮንፈረንስ ተሳታፊ ይደውሉ
  • የሁለተኛው ደንበኛ ስልክ ሲነሳ “Conference” ወይም “Merge Call” የሚለውን በመምረጥ የኮንፈረንስ ጥሪዎን ያካሂዱ
  • ሌሎች ተሳታፊዎችን ለመጨመር ከላይ የተዘረዘሩትን ቅደም ተከሎች ይድገሙ

ታሪፍ

መደበኛ የጥሪ ዋጋ በኮንፈረንስ ተሳፊዎች ቁጥር ተባዝቶ የሚከፍሉ ይሆናል

  • የሞባይሎ አየር ሰዓት መጠን ዝቅተኛ ሲሆን ለሚፈላጓቸው ደንበኛ የይደውሉልኝ ጥያቄ ይላኩ
  • አገልግሎቱን ለማግኘት፡ *807*የተቀባዮን ስልክ ቁጥር# በማድረግ ይደውሉ

ካለዎት የሞባይል የአየር ሰዓት ላይ ለወዳጅ ዘመድዎ ወይም ወደ ሁለተኛ ስልክዎ አየር ሰዓት ይላኩ

አገልግሎቱን ለማግኘት፡   *806*የተቀባዮን ስልክ ቁጥር*የሚላከውን የብር መጠን# በማድረግ ይደውሉ

የአገልግሎቱ ዝርዝር አጠቃቀም እና ለደንበኞች የሚያስገኘው ጥቅም

  • የሞባይል አየር ሰዓት ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች በቀላሉ ለማካፈል ይረዳዎታል
  • የአየር ሰዓት ማስተላላፍ የሚቻለው ከቅድመ ክፍያ ው ቅድመ ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ብቻ ነው
  • የአየር ሰዓት ተቀባዩ ደንበኛ የአገልግሎት ጊዜያቸው ያላለፈ መሆን ይኖርባታል
  • አንድ ደንበኛ ከ1 ብር ጀምሮ እስከ 1,000 ብር መላክ ይችላል
  • በተሳካ ሁኔታ የአየር ሰዓት ሲልኩ 20 ሳንቲም ያስከፍሎታል

ደዋዮችዎን በመረጡት የጥሪ ማሳመሪያ ጣዕመ ዜማዎች ያዝናኑ

የአገልግሎት ክፍያ  
ሳምንታዊ 3 ብር
የ 2 ሳምንት4 ብር
ወርሃዊ7 ብር
ዜማዎች 6 ብር

ለአገልግሎቱ ለመመዝገብ ወደ 822 የእንግሊዝኛውን ፊደል ‘A’ ይላኩ ወይም www.crbt.et. ‘ን ይጎብኙ

አገልግሎቱን ለማቋረጥ ‘U’ ይላኩ

ስለ አገልግሎቱ አጠቃቀም ርጋፍ ካስፈለገዎ የእንግሊዝኛውን ፊደል ‘H’ ይላኩ

የአገልግሎቱ ዝርዝር አጠቃቀም እና ለደንበኞች የሚያስገኘው ጥቅም

  • ከሌሎች ደንኞች ለየት ያለ ማንነት ያላብሶታለል
  • የሰልክ ጥሪው እስኪነሳ ያለውን ቆይታ አዝናኝ ያድርጋል
  • ደዋዮችዮን ዘና ያደርጋል
  • ለተለያዩ ደዋዮች የተለያየ የጥሪ ማሳመሪያ ምጠቀም ይችላሉ
  • እንደ ፍላጎትዎ ለተለያየ ጊዜ የተለያየ የጥሪ ማሳመሪያ መጠቀም ይችላሉ ለምሳልይ ለጠዋት፣ ለበዓላት ለቫላንታይንስ ወዘተ

በተለያየ ምክንያት በስልክዎ መገኘት በማይችሉበት ጊዜ ደዋዮችዎ የቮይስ ሜይል መልዕክት እንዲያስቅምጡልዎ ያድርጉ

የአገልግሎቱ አይነት

ዋጋ

ለአገልግሎቱ ለመመዝገብ ወይም ለማቋረጥ

ነጻ

ወርሀዊ ክፍያ

ነጻ

የተቀመጠልዎትን መልዕክት ለማዳመጥ

ነጻ

ከ824 የሚደርሱ ማሳወቂያ መልዕክቶች ክፍያ

ነጻ

የተቀመጠልዎትን መልዕክት ሲያዳምጡ ለሚነገሩ የማሳወቂያ መልዕክቶች ክፍያ

ነጻ

 

አገልግሎቱ ለደንበኞች የሚያስገኘው ጥቅም

  • ከአገልግሎት መስጫ ክልል ውጪ ሲሆኑ፣ ስልክ ለማንሳት ሳይመችዎ ሲቀር፣ ስልክዎ ዝግ ሲሆን ወይም ሌላ የስልክ ጥሪ እያስተናገዱ ቢሆንም ጠቃሚ መልዕክቶችን እንዲያግኙ ይረዳዎታል

ጥሪ በሚደረግበት ወቅት የፅሁፍ መልዕክት በሞባይል ስክሪን ላይ የሚታይበት አገልግሎት ነው፡፡ ተጠቃሚው የራሱን መልዕክት በማዘጋጀት በደዋዮች ስክሪን ላይ ጥሪ ሲቀበሉ ወይም ሲደውሉ ስልኩ ከመነሳቱ በፊት እንዲታይ ለማድረግ የሚያገለግል ነው፡፡

ማንነትን፣ ስሜትን እና ያሉበትን ጊዜያዊ ሁኔታ ለመግለፅ ይጠቅማል፡፡

ለመመዝገብ

በአጭር መልዕክት

ለዕለታዊ ጥቅል 1ን ወደ 623 በመላክ

ለሣምንታዊ ጥቅል 2ን ወደ 623 በመላክ

በአጭር ቁጥር

*623# በመደወል ትዕዛዛቱን መከተል

የአገልግሎት ክፍያ

ለመመዝገብ እና የጥሪ ፊርማን ለመቀየር በነፃ

ዕለታዊ ጥቅል ዋጋ = 2 ብር

ሣምንታዊ ጥቅል ዋጋ = 6 ብር

ደንብና ሁኔታዎች

  • አገልግሎቱ ለሁሉም የድህረ ክፍያ፣ ቅድመ ክፍያ፣ ሀይብሪድ እንዲሁም አገልግሎት በመስጠት ላይ ያሉ ሁሉም የሞባይል ደንበኞች ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡
  • የጥሪ ፊርማ አገልግሎት ጥሪ ሲያደርጉም ሆነ ሲደወልሎት የሞባይሎ ስክሪን ላይ ሊታዮት የሚችል አገልግሎት ነው፡፡
  • የጥሪ ፊርማ ለሀገር ውስጥ ጥሪ እና አገልግሎቶች ብቻ የተገደበ ነው፡፡

ከዚህ በፊት ደውለው ማግኘት ላልቻሏችው ደንበኛ  አሁን መልሰው ቢደውሉ ሊያገኟቸው እንድሚችሉ በአጭር ጽሁፍ መልዕክት የሚያሳውቅ አገልግሎት ነው::

የአገልግሎቱ አጠቃቀም:

  • አገልግሎቱ ለሁሉም ደንበኞች የተለቀቀ ሲሆን እንደፍላጎትዎ አጭር ጽሁፍ መልዕክት እና USSD በመጠቀም ማቋረጥም ሆነ መልሰው ማስጀመር ይችላሉ.

 

አገልግሎቱን ማቋረጥ እና ማስጀመር

  • አገልግሎቱን ለማቋረጥ D1 ብለው ወደ 824 ይላኩ
  • አገልግሎቱን መልሰው ለማስጀመር A1 ብለው ወደ 824 ይላኩ

አገልግሎቱ ለደንበኞች የሚያስገኘው ጥቅም

  • ውጤት አልባ የሆኑ ተደጋጋሚ ጥሪዎችን ከማድረግ ይታድጎታል
  • በተደጋጋሚ የጥሪ ሙከራ የሚያባክኑትን ጊዜ በመቆጠብ ምርታማነትዎን ያሳድጋል

 

አገልግሎት ዋጋ

  • አገልግሎቱ ለሁሉም ደንበኞቻችን ያለምንም የአገልግሎት ምዝገባ እንዲሁም ወርሀዊ ክፍያ በነጻ ይቀርቧል
  • የአጭር ጽሁፍ መልዕክት ማሳወቂያ ያለመንም ክፍያ ይደርስዎታል

ስልክዎ ዝግ በነበረበት ወይም ከአገልግሎት መስጫ ክልል ውጭ በነበሩበት ሰዓት የትኞቹ ደንበኞች ደውለው እንዳጡዎ በአጭር ጽሁፍ መልዕክት የሚያሳውቅ አገልግሎት ነው

 አገልግሎቱ ለደንበኞች የሚያስገኘው ጥቅም

  • ለሁሉም ያልተሳኩ ጥሪዎች ማሳወቂያ ይደርስዎታል
  • ስልክዎ ዝግ በነበረበት ወይም ከአገልግሎት መስጫ ክልል ውጭ በነበሩበት ሰዓት ደውለው ስላጡዎ ደንበኞች የተሟላ መረጃ ያገኛሉ (የስልክ ቁጥራቸውን፣ የደወሉበትን ሰዓት ወዘተ

አገልግሎት ዋጋ

  • አገልግሎቱ ለሁሉም ደንበኞቻችን ያለምንም የአገልግሎት ክፍያ በነጻ ይቀርቧል

የአገልግሎቱ አጠቃቀም:

 አገልግሎቱ ለሁሉም ደንበኞች ተለቋል

አገልግሎቱን ማቋረጥ እና ማስጀመር

  • አገልግሎቱን ለማቋረጥ D2 ብለው ወደ 824 ይላኩ
  • አገልግሎቱን መልሰው ለማስጀመር A2 ብለው ወደ 824 ይላኩ

  • ስልክ እያነጋገሩ ሌላ አስፈላጊ ጥሪ ቢመጣ ምልክት የሚሰጥዎ እና እንዳያመልጥዎት የሚያስችል አገልግሎት ነዉ
  • አገልግሎቱ በነፃ የሚሰጥ ሲሆን በአብዛኛው ስልኮች ላይ ይገኛል፡፡

  • ገቢ ጥሪዎችን ወደሌላ ቁጥር ማስተላለፍ የሚያስችልዎ አገልግሎት ነው
  • አገልግሎቱን ስልክዎን በመጠቀም ማስጀመርም ሆነ ማቋረጥ ይችላሉ
  • ከታች በተዘረዘሩት ሁኔታዎች ውስጥ ሲሆኑ ጥሪዎችዎ ወደ ሌላ ስልክ እንዲተላለፍ ማድረግ ይችላሉ
  • ሌላ ጥሪ እያስተናገዱ ሲሆን
  • ከአገልግሎት መስጫ ክልል ውጭ ሲሆኑ
  • ስልኩን ሳያነሱት ሲቀር
  • ሁሉንም ገቢ ጥሪዎች እንደፍላጎትዎ ማስተላለፍ ይችላሉ

አገልግሎቱ ለደንበኞች የሚያስገኘው ጥቅም

  • መገኘት ባልቻሉበት ሰዐት ጠቃሚ ስለኮች እንዳያመልጡዎ ይረዳል

የጥሪ ማስተላለፍ አገልግሎት

  1. የጥሪ ማስተላለፊያ አገልግሎትን በስልኬ እንዴት ላስጀምር?
  • *21*ጥሪዎ የሚተላለፍበትን ስልክ ቁጥር# በመፃፍ መደወል
  • ሁሉንም ጥሪዎች ያለቅድመ ሁኔታ ለማስተላለፍ፤ **21*ጥሪዎ የሚተላለፍበትን ስልክ ቁጥር# በመፃፍ መደወል
  • ስልክዎ ሳይነሳ ሲቀር ለማስተላለፍ፤ **61*ጥሪዎ የሚተላለፍበትን ስልክ ቁጥር# በመፃፍ መደወል
  • ከአገልግሎት መስጫ ክልል ውጭ ሲሆኑ ለማስተላለፍ **62*ጥሪዎ የሚተላለፍበትን ስልክ ቁጥር# በመፃፍ መደወል
  • ሌላ ጥሪ እያስተናገዱ ከሆነ፤ **67*ጥሪዎ የሚተላለፍበትን ስልክ ቁጥር# በመፃፍ መደወል
  1. የጥሪ ማስተላለፍ በመጠቀሜ የምከፍለው የአገልግሎት ክፍያ አለ?

አዎ: ጥሪው ወደ ሶስተኛ ወገን እንዲተላለፍ ያደረገው ደንበኛ የጥሪ ማስተላለፍ አገልግሎት ክፍያን ይከፍላል፡፡ ሁሉም ዋጋዎእ ተ.እ.ታን ያካተቱ ናቸው፡፡

ለመመዝገብ ክፍያ: ነፃ

    የአገልግሎት ክፍያ: ከመደበኛ ስልክ ወደ ሞባይል ቁጥር ጥሪ ከተላለፈ

  • በመደበኛ ሰዓት 50 ሣንቲም በደቂቃ
  • ከመደበኛ ሰዓት ውጪ 35 ሣንቲም በደቂቃ

    የአገልግሎት ክፍያ: ከመደበኛ ስልክ ወደ መደበኛ ስልክ

  • ከተማ ውስጥ 23 ሣንቲም በ6 ደቂቃ
  • ከከተማ ወደ ከተማ
    • በመደበኛ ሰዓት 46 ሣንቲም በደቂቃ
    • ከመደበኛ ሰዓት ውጪ 29 ሣንቲም በደቂቃ
  1. የጥሪ ማስተላለፍ አገልግሎትን እንዴት ማቋረጥ እችላለው?
  • #21# በመፃፍ መደወል
  • ##21# በመፃፍ መደወል
  • ##61# በመፃፍ መደወል
  • ##62# በመፃፍ መደወል
  • ##67# በመፃፍ መደወል
  • ሁሉንም የተላለፉ ጥሪዎችን ለማቋረጥ ##002# በመፃፍ መደወል
  1. የጥሪ ማስተላለፍ አገልግሎትን ተጠቃሚ ሁኜ ወጪ ጥሪ ማድረግ እችላለሁ?
  • አዎ፤ የጥሪ ማስተላለፍ አገልግሎት ተጠቃሚ ቢሆኑም ወጪ ጥሪ ማድረግ ይችላሉ
  1. ስልኬ ዝግ ሲሆን ጥሪ ማስተላለፍ እችላለሁ?

አዎ, **62*ጥሪዎ የሚተላለፍበትን ስልክ ቁጥር# በመፃፍ መደወል

  1. ወደ ሌላ ቁጥር ጥሪ እንዲተላለፍ ሲደረግ የማሳወቂያ መልዕክት ይደርሰኛል?
  • ለአገልግሎቱ ሲመዘገቡ ወይም ሲያቋርጡ ለአመለከቱት አዲሱ አገልግሎት በተሳካ ሁኔታ ተመዝገበዋል/ተቋርጧልየሚል የድምፅ መልዕክት ይደርስዎታል፡፡ ወይም
  • አገልግሎቱን ማስጀመርዎትን የሚገልፅ መልዕክት የስልክዎ ስክሪን ላይ የሚታይዎት ይሆናል፡፡
  1. የጥሪ ማስተላለፍ አገልግሎት ከተመዘገቡ በኋላ አገልግሎቱን ለማስጀመር ምን ያህል ጊዜ ይቆያል?
  • ምንም ያህል ጊዜ ሳይፈጅ አገልግሎቱ እንደተመዘገቡ ወዲያው ይጀምራል፡፡
  1. ጥሪ ያስተላለፍኩበት የሞባይል ቁጥር ሌላ ጥሪ በማስተናገድ ላይ ከሆነ ወይም ከአገልግሎት መስጫ ክልል ውጪ ቢሆን ምን ይሆናል?
  • ያስተላለፉበት ስልክ አሁናዊ መረጃ ለደዋይ ደንበኞችዎ እንዲያውቁት ይሆናል፡፡

 

 

 

 

 

  1. ጥሪዎችን ወደ ተለያዩ የሞባይል ቁጥሮች ማስተላለፍ እችላለሁ?
  • ሁሉንም ጥሪዎች ያለቅድመ ሁኔታ ለማስተላለፍ፤ **21*ጥሪዎ የሚተላለፍበትን ስልክ ቁጥር# በመፃፍ መደወል
  • ስልክዎ ሳይነሳ ሲቀር ለማስተላለፍ፤ **61*ጥሪዎ የሚተላለፍበትን ስልክ ቁጥር# በመፃፍ መደወል
  • ከአገልግሎት መስጫ ክልል ውጭ ሲሆኑ ለማስተላለፍ **62*ጥሪዎ የሚተላለፍበትን ስልክ ቁጥር# በመፃፍ መደወል

ሌላ ጥሪ እያስተናገዱ ከሆነ፤ **67*ጥሪዎ የሚተላለፍበትን ስልክ ቁጥር# በመፃፍ መደወል

  • ለማስታወስ እና ለመደወል ቀላል የሆኑ በአራት ምድቦች የተመደቡ (ፕላቲኒየም ፣ ወርቅ ፣ ብር እና ነሐስ) የሞባይል ስልክ ቁጥሮችን በአቅራቢያዎ ባለ የኢትዮ ቴሌኮም ሽያጭ ማዕከል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ለሥራ፣ ለትምህርት ወይም ለሌላ ጉዳይ ወደ ውጪ አገር ሲሄዱ አልያም ሀገር ውስጥ ሆነው ረዘም ላለ ጊዜ የመደበኛ ወይንም የሞባይል ስልክዎን ሳይጠቀሙበት ለማቆየት ቢፈልጉ ቁጥሬን ያቆዩልኝ አገልግሎትን በመጠቀም ቁጥርዎን በአደራ እንዲቀመጥልዎት በማድረግ መልሰው መጠቀም ይችላሉ፡፡

ቁጥርዎን እስከ 5 ዓመታት ድረስ ማቆየት ይችላሉ፡፡

የአገልግሎት ዋጋ በዓመት 109 ብር

አገልግሎቱን ለማግኘት የኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከል ይጎብኙ፡፡