ኢትዮ ቴሌኮም እና ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በተቀናጀ ደራሽ የክፍያ ስርዓት አማካኝነት የውሃ አገልግሎት ሰጪ መስሪያ ቤቶች የወርሃዊ አገልግሎት ክፍያን በቴሌብር ለመፈጸም የሚያስችል ስትራቴጂያዊ የአጋርነት ስምምነት ተደርጓል፡፡

በዛሬው ዕለት በሐረሪ፣ ባሕርዳር፣ ፍኖተ ሰላም፣ እንጅባራ፣ አርባምንጭ፣ ደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች የሚገኙ የቴሌብር ደንበኞች የውኃ አገልግሎት ክፍያቸውን በተቀናጀ ደራሽ የክፍያ ስርዓት አማካኝነት በቴሌብር ለመፈጸም ይችሉ ዘንድ ኢትዮ ቴሌኮም እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ስምምነት በመፈጸም አገልግሎቱን ተግባራዊ አድርገዋል፡፡

በዚህ ስምምነት መሰረት የውኃ አገልግሎት ሰጪ መስሪያ ቤቶች በተቀናጀ ደራሽ የክፍያ ስርዓት አማካኝነት የደንበኞቻቸውን ወርሃዊ ሂሳብ በቴሌብር ለመሰብሰብ የሚያስችላቸው ይሆናል፡፡ ይህ አሠራር የማህበረሰባችንን የዲጂታል ክፍያ ተጠቃሚነት ፍላጎት ለማሳደግ፣ በጥሬ ገንዘብ የሚደረገውን ግብይት ለመቀነስ እና የቢዝነስ መረጃዎችን ፍሰት በቀላሉ ለማወቅና ለማሻሻል ትልቅ ፍይዳ የሚኖረው ይሆናል፡፡

በተጨማሪም ይህ የክፍያ ሥርዓት ለውኃ እና የፍሳሽ አገልግሎት ቢሮዎች የአገልግሎት ክፍያን በአነስተኛ ወጪና በወቅቱ ለመሰብሰብ፣ ደንበኞቻቸው ሂሳባቸውን ከየትኛውም ቦታ ሆነው በቀላሉ እንዲከፍሉ ለማስቻል፣ የተሻለ የደንበኛ ግንኙነት እንዲጎለብት፣ በመረጃ ላይ የተመሰረተ ሪፖርት ለማዘጋጀት እና ደንበኞችን በቀላሉ ለመለየት እንዲሁም እንደ አገልግሎት አጠቃቀማቸው ደረጃ ለመመደብ ወይም ለመከፋፈል ያስችላቸዋል፡፡

የቴሌብር አገልግሎትን ተግባራዊ ማድረጉ ለበርካታ ኢትዮጵያውያን አዲስ የኑሮ ዘይቤ መፈጠር እና የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት መስፋፋት ቁልፍ ሚና እየተጫወተ የሚገኝ ሲሆን በተለይም በአጭር ጊዜ ውስጥ ከ19 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች፣ ከ82 በላይ ዋና ወኪሎች፣ 67 ሺ በላይ ወኪሎች እና ከ17 ሺ በላይ ነጋዴዎች ማፍራት መቻሉ እና ከ16.2 ቢሊዮን ብር በላይ የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ ዝውውር መደረጉ እንዲሁም 12 ባንኮች ጋር ከባንክ ወደ ቴሌብር እና ከ10 ባንኮች ጋር ደግሞ ከቴሌብር ወደ ባንክ ገንዘብ ለማስተላለፍ ትስስር መፍጠሩ ለዲጂታል የክፍያ ስርዓት ያለውን ከፍተኛ ተመራጭነት ያሳያል፡፡

ኩባንያችን ከዚህ በፊት ከበርካታ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር የአገልግሎት ክፍያዎችን በቴሌብር ለመፈጸም የሚያስችል አሰራርን ተግባራዊ ያደረገ ሲሆን፤ በቀጣይም በሌሎች ክልሎች ከሚገኙ የውኃ እና ፍሳሽ ተቋማት ጋር በመተባበር በተቀናጀ ደራሽ የክፍያ ስርዓት እና በቴሌብር አማካኝነት ክፍያ መፈጸም የሚያስችል አሰራር ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም

ግንቦት 10 ቀን 2014 ዓ.ም

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives