ያገለገሉ ጄኔሬተሮች እና አሳንሰር(ሊፍት) ፣ አሮጌ የኮንክሪት ሞልድ እና የብረት ፎርም ወርክ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር FD/AM/04/2015
ኢትዮ ቴሌኮም ያገለገሉ ጄኔሬተሮችን እና አሳንሰር(ሊፍት) ፣ አሮጌ የኮንክሪት ሞልድ እና የብረት ፎርም ወርክ ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከመጋቢት 4 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መጋቢት 19 ቀን 2015 ዓ.ም tender.2merkato.com . www.extratender.com & afrotender.com የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በቴሌብር በመክፈል መግዛት አለባቸው።
- ንብረቶቹን ለማየት ተጫራቾች መታወቂያቸውን በመያዝ ጄኔሬተሮቹን አቃቂ በሚገኘው ኢትዮ ቴሌኮም ዕቃ ግምጃ ቤት እና አሳንሰር (ሊፍት) ፣ አሮጌ የኮንክሪት ሞልድ እና የብረት ፎርም ወርክ በወሎ ሰፈር በሚገኘው ኢትዮ ቴሌኮም ማዕከላዊ ዕቃ ግምጃ ቤት በመገኘት ከመጋቢት 4 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ መጋቢት 19 ቀን 2015 ዓ.ም. ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ-አርብ) ማየት ይችላሉ።
- ጨረታ የሚዘጋው መጋቢት 20 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ነው።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው መጋቢት 20 ቀን 2015 ዓ.ም. ከሰዓት 9፡00 ሰዓት ይከፈታል።
- ኢትዮ ቴሌኮም ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ዝርዝር መረጃውን ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ።