ኩባንያችን በራዕዩና በተልዕኮው እንዲሁም በሦስት ዓመት ሊድ (LEAD) የዕድገት ስትራቴጂው ላይ እንደተለጸው ከኮኔክቲቪቲ አገልግሎት ባሻገር (Beyond Connectivity) መሪ የዲጂታል አገልግሎት አቅራቢ በመሆን የተቋማትን የቢዝነስ እንቅስቃሴ ለማዘመን እና ለማሳለጥ በሰፊው እየሰራ የሚገኝ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለትም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር የአዲስ አበባ ስማርት ሲቲ ፕሮጀክትን እውን ለማድረግ የሚያስችል የመሠረተ ልማት ግንባታ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

በስምምነቱ መሠረት ኢትዮ ቴሌኮም የከተማዋን የተለያዩ ቢሮዎች እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ከዋናው የዳታ ማዕከል ጋር በቀላሉ ለማስተሳሰር የሚያስችል የዋይድ ኤሪያ ኔትዎርክ (SD-WAN Network) የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎችን በማከናወን 11 ክፍለ ከተሞችን፣ 120 ወረዳዎችን፣ በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ 44 ቢሮዎችን እንዲሁም የዋና ዳታ ማዕከሉን አሁን ከሚገኝበት በሜጋ ባይት በሚለካ የግንኙነት ፍጥነት በማሻሻል ከ1 ጊ.ባ እስከ 100 ጊ.ባ በሚደርስ እጅግ ከፍተኛ ፍጥነት እና ጥራት ባለው የኦፕቲካል ፋይበር ግንኙነት (Lamda Connectivity) በማስተሳሰር ለከተማ አስተዳደሩ የሚያስረክብ ይሆናል፡፡

ይህም የከተማ አስተዳደሩ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር የአፍሪካ መዲና እና የበርካታ ዓለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫ የሆነችውን አዲስ አበባን የሚመጥን እና ዘመኑ ያፈራቸውን የአይ.ሲ.ቲ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የአዲስ አበባ ስማርት ሲቲ መርሃግብርን ዕውን ለማድረግ እያከናወናቸው ከሚገኙ ሜጋ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ ነው፡፡

በፕሮጀክቱ የከተማ አስተዳደሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣውን የቴክኖሎጂ ፍላጎትንና የዳታ ደህንነት ስጋቶችን ለመቅረፍ፣ ክፍለ ከተሞችን እና ወረዳዎችን በቴክኖሎጂ በማስተሳሰር ወሳኝ ተልዕኮ ላላቸው (Mission Critical) እና በተመሳሳይ ወቅት መከናወን የሚፈልጉ አገልግሎቶችን (real time) ለመከወን፣ የአሰራር ሥርዓትን በማዘመን አስተማማኝ፣ ቀልጣፋ እና ጥራት ያለው አገልግሎት ለከተማዋ ነዋሪዎች ለማቅረብ፣ የአፈጻጻም ብቃትንና የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናን በመጨመር እና የነዋሪዎችን አኗኗር በማዘመን ከተማዋን የቴክኖሎጂ መናሃሪያ (technology Hub) ለማድረግ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።

ኩባንያችን ከጥቂት ወራት በፊት የአዳማ ከተማን ስማርት ሲቲ ፕሮጀክት ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ከአዳማ ከተማ አስተዳደር ጋር በመፈጸም የተለያዩ ተግባራትን በትጋት እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን፣ የአዲስ አበባ ስማርት ሲቲ ፕሮጀክትን ጨምሮ በበርካታ መስኮች ለመሰል ተቋማት የቴክኖሎጂ እና ዲጂታል ሶሉሽኖችን በማቅረብ እና የአገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን የማሕበረሰባችንን የኑሮ ሁኔታ የሚያቀሉ በርካታ ተግባራትን በማከናወን ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረጉን ይቀጥላል።

ኢትዮ ቴሌኮም

ግንቦት 29 ቀን 2015 .

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives