ኢትዮ ቴሌኮም ያገለገሉ አሳንሰር ሊፍቶች (Elevetors) ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

  1. ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ተጫራቾች ህዳር 24 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 10 ቀን 2016 ዓ.ም ከኤክስትራ ቴንደር (www.extratender.com) ፣ከአፍሮ ቴንደር (www.afrotender.com) እና ከቱ መርካቶ (www.2Merkato.com) ድህረገፅ የማይመለስ ብር 100.00(አንድ መቶ) በቴሌ ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. አሳንሰሮአቹን ለማየት ተጫራቾች ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ ወሎ ሰፈር እና አቃቂ በሚገኙት የኢትዮ ቴሌኮም ዕቃ ግምጃ ቤቶች  ከህዳር 24 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 10 ቀን 2016 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት (ከሰኞ-አርብ) በመገኘት ማየት የሚችሉ ሲሆን ነገር ግን በመዝጊያው ቀን ታህሳስ 10 እስከ ጠዋት 6፡30 ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የግዤውን ዋጋ አሥር በመቶ 10% (አስር ፐርሰንት) የሚመለስ በቴሌ ብር ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  1. የጨረታው ሰነድ ገቢ የሚደረገው ትራኮን ታወር በሚገኘው ኢትዮ ቴሌኮም 10ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 10 ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ታህሳስ 10 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ትራኮን ህንጻ 12ኛ ፎቅ ይከፈታል፡፡
  2. ዝርዝር መረጃውን ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives