ኩባንያችን ከኮኔክቲቪቲ አገልግሎት ባሻገር (Beyond Connectivity) መሪ የዲጂታል አገልግሎት አቅራቢ በመሆን የደንበኞቹን የዕለት ተዕለት የቢዝነስ እንቅስቃሴ ለማዘመን፣ የዲጂታል አገልግሎት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እና ተሞክሮአቸውን ለማሳደግ እንዲሁም አጠቃላይ የህብረተሰባችን የዲጂታል የአኗኗር ዘይቤን ለማሻሻልና የሀገራችን የዲጂታል አገልግሎት ተጠቃሚነት ለማሳደግ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል፡፡ በዛሬው ዕለትም የዚህ ጥረት አካል የሆነ እና ዜድቲኢ ብሌድ V50 ዲዛይንን ጨምሮ ዜድቲኢ ብሌድ A40 እና A54 ስማርት የሞባይል ስልኮችን ለደንበኞቻችን ለማቅረብ የሚያስችል ስምምነት ከዜድቲኢ ኩባንያ ጋር በአጋርነት ፈጽሟል፡፡

ኩባንያችን የስማርት ስልኮችን ተደራሽነት ለማሳደግ እና አጠቃላይ የዜጎችን የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም የደንበኞቹን ፍላጎት ለመሟላት እና ለማሻሻል ከፍተኛ ደረጃ ያላቸውን የስማርት ቀፎዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ በተለያዩ የመክፈያ ዘዴዎች/አማራጮች ከተለያዩ የሞባይል ቀፎ አቅራቢ አጋሮቹ ጋር በጋራ በየዓመቱ ከ1 ሚሊዮን በላይ የተለያዩ ዓይነት ዲቫይሶችን ለተጠቃሚዎች ተደራሽ እንዲሆኑ ሲሰራ ቆይቷል። በተጨማሪም የደንበኞችን ፍላጎት ለማርካት እና የላቀ ተሞክሮ እንዲኖራቸው የሚያስችሉ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የፕሪሚየም ብራንድ ሞዴሎችን ወይም ስማርት ስልኮችን በማቅረብ ላይ ይገኛል።

በዛሬው ዕለት በተደረገው ስምምነት መሰረት ኩባንያችን እና ዜድቲኢ አዲስ ይፋ የሆነውን ዜድቲኢ ብሌድ V50 ዲዛይን ከዜድቲኢ ብሌድ A40 እና A54 ዜድቲኢ ብሌድ ጋር ወደ ኢትዮጵያ ገበያ በጋራ ለማቅረብ ችለዋል።

በዚህም መሰረት ኩባንያችን ለግለሰብ እና ለኢንተርፕራይዝ ደንበኞቹ፡

  • የዜድቲኢብሌድቪ50 ዲዛይን (ZTE Blade V50 design, 6/256GB) በ14,999.00 ብር ከተከታታይሶስትወራት 5ጂ.ቢ+200 ደቂቃ ወርሃዊጥቅል እና ከ12 ተከታታይ ወራት 2ጂቢወርሃዊየዩቲዩብጥቅል ጋር፣
  • ዜድቲኢብሌድ A54 (ZTE Blade A54 Core, 4/128GB) በ9,990.00 ብር ከተከታታይሶስትወራት 3ጂ.ቢ+200 ደቂቃ ወርሃዊጥቅል እና ከ12 ተከታታይ ወራት +2ጂ.ቢወርሃዊዩቲዩብጥቅል ጋር፣
  • A40 ፕሮ (A40 pro, 6/128GB) በ18,500.00 ብር ከተከታታይሶስትወራት 5ጂ.ቢ+200 ደቂቃ ወርሃዊጥቅል፣ ከ12 ተከታታይ ወራት 2ጂቢወርሃዊዩቲዩብጥቅልእና ነፃየZTE የጆሮማዳመጫዎች ጋር አቅርቧል፡፡

ኩባንያችን የደንበኞቻችንን ፍላጎት እና ተሞክሮ ለማሳደግ እንዲሁም የዲጂታል አገልግሎቶችን በቀላሉ እንዲያገኙ ለማስቻል የተያዘውን እቅድ ለማሳካት ከዜድቲኢ ኩባንያ ጋር በትብብር የስማርት ስልኮችን ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ለማቅረብ በመቻሉ ከፍተኛ ደስታ ይሰማናል፡፡: ይህ አጋርነት ለደንበኞቻችን ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ስልኮችን በተመጣጣኝ ዋጋ ተደራሽ ከማድረግ ባሻገር በሁለቱ ኩባንያዎች መካከል ጠንካራ እና ዘላቂ ግንኙነትን ለመገንባት ትልቅ ሚና ይኖረዋል፡፡በዚህ አጋጣሚ ክቡራን ደንበኞቻችን በየአቅራቢያቸው ወደሚገኙ የአገልግሎት መስጫ ማዕከሎቻችን በአካል በመሄድ ወይም በቴሌገበያ ድረ ገጽ https://telegebeya.ethiotelecom.et/ አማካኝነት ለገበያ የቀረቡ ስማርት ስልኮችን መግዛት የሚችሉ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።

ጥር 9 ቀን 2016 ዓ.ም.

ኢትዮ ቴሌኮም

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives