ፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ

ዲጂታል መታወቂያ ለአካታች ዲጂታል ኢኮኖሚ!


ፋይዳ ምንድነው?

የዲጂታል መታወቂያ ዓይነት ሲሆን የነዋሪዎችን የባዮሜትሪክ (የጣት አሻራ፣ የአይን አይሪስ እና የፊት ምስል) እንዲሁም የግል መረጃዎችን በመሰብሰብ አንድን ግለሰብ ልዩ በሆነ መልኩ እንዲታወቅ የሚያስችል ነው፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም መሪ የዲጂታል ሶሉሽን አቅራቢ ድርጅት በመሆኑ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን ራዕይ በአጋርነት ለማሳካት እና ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን የማድረግ ራዕይ ለማፋጠን በዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ፣ በመታወቂያ ህትመትና ስርጭት፡ ማንነትን በማረጋገጥ (Authentication) ስራዎች ላይ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡

የፋይዳ (ብሔራዊ መታወቂያ) ጠቀሜታ

ፋይዳ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን የግለሰቦች፣ የንግዱን ዘርፍ እና የዜጎችን ችግሮች በቋሚነት ይቀርፋል፡፡

ለግለሰቦች

  • ማንነታቸውን በህጋዊ መንገድ ያላረጋገጡ ግለሰቦች መሰረታዊ የዜግነት መብቶቻቸውን አለማግኘት
  • የዜጎችን ፍላጎት ያላገናዘበ አገልግሎት አሰጣጥ
  • የተገልጋዮች ግላዊ መረጃዎች በአግባቡ ስለማያዙ ዜጎች ለዝርፍያና ለሌሎች አደጋዎች ተጋላጭ መሆን
  • ማንነትን ለማረጋገጥ ሰነዶችን ማገላበጥ የሚጠይቅ በመሆኑ የተጓተተ የአገልግሎት አሰጣጥ መኖር

ለነጋዴዎች

  • የተቋማት በተንዛዛ ሂደት ቅልጥፍና የጎደለው አገልግሎት አሰጣጥ መኖር
  • የተለያዩ የንግድ ጥናቶች በመረጃ እጥረት ምክንያት ትክክለኛውን የወደፊት አደጋ በመተንበይ የቅድመ መከላከል ስራ ለመስራት መቸገር
  • አገልግሎት ተጠቃሚዎች የተሳሳተ የማንነት መረጃ ይዘው ሲመጡ ለማጣራት መቸገር እና በዚህም ምክንያት የተቋማት መጭበርበር መበርከት
  • የማንነት ማረጋገጫዎች የመገልገያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው መሆን አለመሆኑን ለማጣራት ሰነድ ማገላበጥ የሚጠይቅ መሆን የሰው ሀይል እና የጊዜ ብክነት መኖር

ለዜጎች

  • ማንነትን ማረጋገጥ አስቸጋሪ በመሆኑ ዜጎች ከማህበራዊ ተቋማት ማግኘት የሚገባቸውን አገልግሎቶች ለማግኘት መቸገር
  • በመረጃ እጥረት ምክንያት ያልተገባ የአገልግሎት አሰጣጥ መኖር
  • አጭበርባሪዎች ሀሰተኛ የማንነት መረጃዎችን በማዘጋጀት ለትክክለኛ ዜጎች መሰጠት የነበረበትን አገልግሎት ለራስ ጥቅም ማዋል
  • አብዛኛው የወቀረት ሂደትን የሚከተሉ አሰራሮች ከፍተኛ የሆነ የሰው ሀይል እንዲሁም ማስተካከያዎችን መፈለግ

እነዚህንና መሰል ችግሮች በፋይዳ ይቀረፋሉ!

ማን ይመዝገብ?

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ህጋዊ ነዋሪ በሙሉ ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ብቁ ነው። በመተዳደሪያ አዋጁ መሰረት በህጋዊ መልኩ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር፣ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለው ወይም የሌለው የተፈጥሮ ሰው እንዲሁም በሀገሪቱ ህግ መሰረት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር ወይም የሚሰራ የውጭ ሀገር ዜጋ ይካተታሉ፡፡

  • ዕድሜያቸው ከ 5 ዓመት በላይ የሆኑ ልጆች መመዝገብ ይችላሉ
  • ከ 5 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት, በቅርቡ ልዩ የምዝገባ ፕሮግራም የሚጀመር ይሆናል
  • ኢትዮጵያዊ እና ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ የነዋሪነት ማረጋገጫ ያላቸው
  • የመኖሪያ አድራሻ ማረጋገጫ ሰነድ ያላቸውም ሆነ የሌላቸው
  • ኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪነታቸው “በአዋጁ መሰረት” የተሰጠ
  • የት እንደሚኖሩ ምንም ዓይነት ሰነድ የሌላቸው ሰዎች የዲጂታል መታወቂያ ያለው ሰው እንደ ምስክር ይዞ በመቅረብ መመዝገብ ይችላሉ።

ለምዝገባ ተቀባይነት ያላቸው ሰነዶች ዝርዝር

 

·       የቀበሌ መታወቂያ

·       ፓስፖርት

·       የልደት ሰርተፊኬት

·       የትምህርት ማስረጃ

·       የንግድ ምዝገባ ወይም የንግድ ፈቃድ ሰርተፊኬት

·       የጋብቻ ሰርተፊኬት

·       መንጃ ፈቃድ

·       የባንክ አካውንት ደብተር

·       የመኪና ሊብሬ

·       የቤት ካርታ

·       የሙያ ፈቃድ ማስረጃ

·       የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር/ መታወቂያ (ፎቶ ያለው)

·       የምርጫ ካርድ/መታወቂያ (የተመራጭነት/የመራጭነት ማስረጃ/መታወቂያ)

·       የጤና መድህን መታወቂያ

·       የጡረታ መታወቂያ

·       የሥራ ፈላጊ መታወቂያ

·       የተማሪነት መታወቂያ

·       ዕድር ደብተር

·       የእቁብ ደብተር

·       የህፃናት ማሳደጊያ ተቋማት የሚሰጡ በፎቶ የተደገፈ ደብዳቤ

·       የዲፕሎማት መታወቂያ(ኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪ መሆኑን የሚያመለክት)

·       የዲያስፖራ ነዋሪነት ማረጋገጫ /Yellow card/ ( ኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪ የሆነ)

·       የስደተኛ ካርድ ወይም ከስደትና ስደት ተመላሽ አገልግሎት የሚሰጠው ማስረጃ

·       የሥራ ፈቃድ መታወቂያ ( ለውጭ ሃገር ዜጎች)

·       የአለም አቀፍ ተቋማት የሰራተኛ መታወቂያ

·       በማንኛውም የመንግሥት አካል የሚሰጥ መታወቂያ

·       የቀበሌ ስራ አስኪያጅ የሚሰጠው ማረጋገጫ

·       ፈቃድ ያላቸው ማንኛውም የፋይናንስ ተቋማት የሚሰጥ የማንነት ማስረጃ

·       የነዋሪነት ፍቃድ (ለውጭ ሀገር ዜጎች)

ማስታወሻ

·       ሁሉም ዓይነት ተቀባይነት ያላቸው ሰነዶች የግለሰቡን ፎቶ ማካተት አለባቸው

·       የሰነድ ማስረጃ ከሌለዎ የፋይዳ መታወቂያ ስርዓት ውስጥ የተመዘገበ የሰው ምስክር ማቅረብ ይችላሉ፡፡

የፋይዳ ምዝገባዎን

በመላ ሀገሪቱ የኢትዮ ቴሌኮም    
የተመረጡ አገልግሎት መስጫ ማዕከሎች   
በነፃ ይችላሉ!
   
አጋር ድርጅቶች   
   
ተንቀሳቃሽ የምዝገባ ጣቢያዎች   

በምዝገባ ወቅት የምዝገባ ባለሞያዎች የባዮሜትሪክ መረጃን (10 የጣት አሻራ፣ የ2 አይን አይሪስ እና የፊት ምስል) እና በቅድመ-ምዝገባ ወቅት የተሞሉ ተቀባይነት ያላቸውን ሰነዶችን ይሰበስባሉ።

መታወቂያዎን በቴሌብር ሱፐርአፕ ያግኙ!

ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባዎን ካጠናቀቁ በኋላ በምዝገባ ወቅት በሰጡት ሞባይል ቁጥርዎ National ID በሚል ባለ 12 አሃዝ የፋይዳ ልዩ ቁጥር በፅሁፍ መልዕክት የሚላክልዎ ሲሆን ቁጥሩን ቴሌብር ሱፐርአፕን ላይ ከገቡ በኋላ “መተግበሪያዎች’’ የሚለውን በመጫን የብሔራዊ መታወቂያ ሚኒ አፕን በመምረጥ ቁጥሩን በማስገባት ለህትመት ዝግጁ የሆነ (softcopy) መታወቂያዎን ማግኘት ይችላሉ፡፡

ጠቃሚ መረጃ

  • If you did not receive your Fayda ID via SMS
  • If you lost your Fayda number
  • If you did not get your Fayda digital ID on telebirr superApp fayda mini app

Click Here https://id.et/help

Or dial 9779


በተጨማሪም የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ አዋጅ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

0
ሀገራዊ የምዝገባ ዕቅድ
0
የ 2018 ዓ.ም ተቋማዊ ዕቅድ
0
አማካይ ወርኃዊ ተቋማዊ ዕቅድ
በተደጋጋሚ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ

  1. ፋይዳዲጂታል መታወቂያ ምንነው? ጠቀሜታውስ?

ፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ግለሰቦች ማንነታቸውን እንዲያረጋግጡ የሚያስችል እና ለአገልግሎት አቅራቢዎች ታማኝ የዲጂታል ማረጋገጫ በዚያው ቅጽበት የሚሰጥ መታወቂያ ስርዓት ነው ።

ጠቀሚታውም;

  • መሰረታዊ “የመታወቅ መብትን” የሚሰጥ ትክክለኛ እና ህጋዊ የማንነት ማረጋገጫ ነው።
  • በሁሉም አካባቢዎች የተለያዩ የገቢ ደረጃ ላይ ላሉ እና የከተማ መስፋፋት ውስጥ ለሚካተቱ ማህበረሰቦች፣ ፍትሃዊ ተደራሽነት እንዲኖር የሚያስችል የመታወቂያ ስርአት ነው።
  • በባዮሜትሪክ ላይ የተመሰረተ መለያ ሲኖር የአንድ ሰው ካርድ ወይም የምስክር ወረቀት መጥፋት ማለት የማንነት ማጣት ማለት አይደለም
  • በአገልግሎት ሰጪ እና በተጠቃሚው መካከል ለሚደረጉ ግብይቶች ተአማኒነትን ይጨምራል ፣ ይህም ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል
  • በሁሉም የሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖሊሲዎች ተጠያቂነትን እና ግልፅነትን ያበረታታል።
  1. ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ብቁ የሆነው ማነው?

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ህጋዊ ነዋሪ በሙሉ ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ብቁ ነው። በ “ረቂቅ አዋጁ” ነዋሪ የሚገለፀው “በህጋዊ መልኩ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር ፣ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለው ወይም የሌለው የተፈጥሮ ሰው እንዲሁም በሀገሪቱ ህግ መሰረት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር ወይም የሚሰራ የውጭ ሀገር ዜጋ ነው።” ይህም የሚያካትተው ፡-

  1. ዕድሜያቸው ከ 5 ዓመት በላይ የሆኑ ልጆች መመዝገብ ይችላሉ። ከ 5 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት, በቅርቡ ልዩ የምዝገባ ፕሮግራም የምንጀምር ይሆናል።
  2. ኢትዮጵያዊ እና ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ የነዋሪነት ማረጋገጫ ያላቸው
  3. የመኖሪያ አድራሻ ማረጋገጫ ሰነድ ያላቸውም ሆነ የሌላቸው ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪነታቸው “በአዋጁ መሰረት” የተሰጠ።
  4. የት እንደሚኖሩ ምንም ዓይነት ሰነድ የሌላቸው ሰዎች ፣ የዲጂታል መታወቂያ ያለው ሰው እንደ ምስክር ይዞ በመቅረብ መመዝገብ ይችላሉ።
  5. ማንኛውም ለምዝገባ ብቁ የሆነ ሰው id.et/proof ላይ በተጠቀሰው መሰረት ተቀባይነት ያለው የማንነት ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርበታል።
  6. ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የት መመዝገብ እችላለሁ?

ለአገልግሎቱ ብቁ የሆኑ ዜጎች የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት መስጫ ማዕከሎችን እንዲሁም ምዝገባ እንዲያደርጉ ፈቃድ ያላቸው አጋሮች ጋር መመዝገብ ይችላሉ፡፡ የባዮሜትሪክ መረጃ መስጠት ስለሚጠበቅብዎ ለአገልግሎቱ በአካል መቅረብ ይጠበቅብዎታል፡፡

  1. የፋይዳ መታወቂያን ለማግኘት ምን ያክል መክፈል ይኖርብኛል?

ለዲጂታል መታወቂያ በነፃ መመዝገብ ይችላሉ፡፡ የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ አዋጅ መሰረት በስኬት መመዝገብዎን የሚገልፅ “የፋይዳ መለያ ቁጥር” በፅሁፍ መልዕክት የሚደርስዎ ይሆናል፡፡ ይህም ማለት የተረጋገጠ “የፋይዳ መለያ“ አለዎት ማለት ነው፡፡ ነገር ግን የታተመ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ከፈለጉ የህትመት የሚከፍሉ ይሆናል፡፡

  1. ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ለመመዝገብ ምን ያክል ጊዜ ይፈጅብኛል?

ሁሉም መረጃዎች በተሟሉበት ሁኔታ ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ለመመዝገብ በአማካኝ ከ5 እስከ 10 ደቂቃ ይፈጃል።

  1. የፋይዳ መለያ ቁጥር ለማግኘት ምን ያክል ጊዜ ይፈጃል?

በተሳካ ሁኔታ ምዝገባዎን ከአጠናቀቁ በኋላ መረጃዎን የማረጋገጡ ሂደት ጥቂት ደቂቃዎች አልያም የተወሰኑ ቀናት ሊወስድ ይችላል፡፡ ልዩ የፋይዳ መለያ ቁጥርዎ በምዝገባ ወቅት ባስመዘገቡት የሞባይል ቁጥር ቁጥር የሚላክልዎ ይሆናል፡፡ ያስመዘገቡት ቁጥር ሊቀየር የማይችል ብቸኛ እርስዎ የሚገኙበት አድራሻ በመሆኑ ሲያስመዘግቡ ጥንቃቄ ያድርጉ፡፡

መረጃዎን ሲስተም ውስጥ ለማስገባት እና ለማረጋገጥ በእጅ (manually) ከሆነ ጥቂት ቀናት የሚወስድ ሲሆን መዘግየት ቢኖርም ነገር ግን ማረጋገጫ ቁጥርዎን በ9779 ወይም National ID Ethiopia በሚል የፅሁፍ መልዕክት የሚላክልዎ ይሆናል፡፡

  1. ከምዝገባ በኋላ መረጃዬን ማስተካከል እችላለሁ?

ደንበኞች የግል መረጃቸውን በማንኛውም ጊዜ ያረጋግጡልኛል ያሏቸውን ሰነዶች በኦንላይን ወይም በአካል በማስገባት ማስተካከል ይችላሉ፡፡ ይህ አገልግሎት ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የሚጀምር ሲሆን በአሁኑ ጊዜ መረጃ ማደስ አይቻልም።

 

  1. ለምዝገባ የሚያስፈልጉ የሰነድ ማስረጃዎች ምን ምን ናቸው?

አሁን ላይ የሚኖሩበት ትክክለኛ አድራሻ እና የማንነት ማረጋገጫ ያስፈልጋል። እንደ፦

  • የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፈቃድ እንዲሁም ሌሎች ህጋዊ ተቀባይነት ያላቸው የግለሰቡ መለያዎች በማስረጃነት መቅረብ ይችላሉ፡፡ ለተጨማሪ ዝርዝር gov.et/proof ይሄን ይጫኑ
  • አንድ ግለሰብ ለመመዝገብ ትክክለኛ ሰነድ ማቅረብ ካልቻለ ዲጂታል መታወቂያ ያለው ሰው ምስክር አምጥቶ መመዝገብ ይችላል።
  1. የፋይዳ መለያ ቁጥር ከጠፋብኝ/ከረሳሁት እንዴት መልሼ ማግኘት እችላለሁ?

የፋይዳ መለያ ቁጥርዎን መልሶ ለማግኘት በምዝገባ ወቅት የሞሉትን ግላዊ ወይም የባዮሜትሪክ መረጃዎን በማቅረብ እንዲሁም አቅራቢያዎ የሚገኝ የምዝገባ ጣቢያ በመጎብኘ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ይህን በማድረግ የፋይዳ መለያ ቁጥርዎን በቀላሉ በፅሁፍ መልዕክት ወይም ከምዝገባ ጣቢያዎች ማግኘት ይችላሉ፡፡

ይህ አገልግሎት በቅርቡ የሚጀምር ሲሆን የምናሳውቅዎ ይሆናል፡፡

  1. ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ መመዝገብ ግዴታ ነው?

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ መብት እንጂ ግዴታ አይደለም። ሆኖም የዲጂታል መታወቂያ አዋጁ እንደሚለው፡- “ማንኛውም አካል አገልግሎትን ለማቅረብ ዲጂታል መታወቂያን የግዴታ መስፈርት አድርጎ የማቅረብ ህጋዊ መብቱ የተጠበቀ ነው።

  1. የውጭ ሀገር ዜጎች ዲጂታል መታወቂያ ማግኘት ይችላሉ?

አዎ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ በህጋዊ መንገድ የሚኖሩ የውጭ ሀገር ዜጎች የነዋሪነት መታወቂያቸውን፣ ፓስፖርት ወይም ሌሎች ተዛማጅ ሰነዶችን በመጠቀም ዲጂታል መታወቂያ ማግኘት ይችላሉ።

  1. የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያዬ የመጠቀሚያ ጊዜው ሊያልፍ ይችላል?

የዲጂታል መታወቂያ ለአንድ ግለሰብ ልዩ የሆነ የህይወት ዘመን ቁጥር ነው። ሆኖም ግን የካርዱ እና የባዮሜትሪክ መረጃ በተወሰነ ጊዜ መታደስ አለበት። አሁን ላይ የካርድ እና የባዮሜትሪክ መረጃ በየ10 አመቱ የሚታደስ ይሆናል።

 

 

 

  1. በክልል ደረጃ ምዝገባ የምትጀምሩት መቼ ነው?

በቀጣይ አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በሁሉም የክልል ዋና እና በተመረጡ ከተሞች የሚጀመር ይሆናል፡፡ የፈረንጆቹ 2025 ከመጠናቀቁ በፊት 90 ሚሊዮን የተለያዩ የገቢ ደረጃ ላይ ላሉ እና የከተማ መስፋፋት ውስጥ ለሚካተቱ ማህበረሰቦች ለመመዝገብ ታቅዷል፡፡

  1. የታተመ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያዬን እንዴት ማግኘት እችላለሁ?

በብሔራዊ መታወቂያ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ዲጂታል መታወቂያ የሚባለው ለግለሰቡ የሚሰጠው ልዩ መለያ ቁጥር ሲሆን ይህ ቁጥር ምዝገባዎን ካጠናቀቁ በሰዓታት ወይም ከጥቂት ቀናት በኋላ በነፃ በሞባይል ቁጥርዎ የሚላክልዎ ይሆናል፡፡ የዲጂታል መታወቂያ በሚጠየቁበት ጊዜ ይህን ልዩ ቁጥር በመስጠት ማንኛውንም አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡፡

በቅርቡ የዲጂታል መታወቂያ ህትመት አገልግሎት በመጀመር የምናሳውቅዎ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ለህትመት ዝግጁ የሆነውን መታወቂያዎን በቴሌብር ሱፐርአፕ ላይ መለያ ቁጥርዎን ተጠቅመው ማግኘት ይችላሉ፡፡

  1. የቀበሌ የነዋሪነት መታወቂያ በፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ይተካል? ያላቸው ግንኙነትስ ምንድነው?

አይተካም፤ የከተማ እና የክልል የመንግስት ነዋሪ መታወቂያ ካርድ የሚሰጡት በአካባቢ አስተዳደር ነው። ነገር ግን “ፋይዳ” ዲጂታል መታወቂያ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጥ ነው። ሁለቱም “ቀበሌ” እና “ፋይዳ” እጅ ለእጅ ተያይዘው እንዲሰሩ የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው። ዲጂታል መታወቂያ ማንነትን የሚያረጋግጥ መሠረታዊ መታወቂያ ሲሆን የቀበሌ መታወቂያ ግን ተግባራዊ መታወቂያ (አገልግሎት ለማግኘት የሚጠቅም) ነው። ዲጂታል መታወቂያ የመኖሪያ አካባቢ ገደብ ሳይደረግበት በሀገሪቱ ውስጥ በየትኛውም ቦታ በተፈቀደ አካል ሊሰጥ የሚችል የአንድ ሰው ልዩ መለያ ነው። በአንፃሩ የቀበሌ መታወቂያ ሊሰጥ የሚችለው በሚኖርበት ቀበሌ ብቻ ነው።

በኢትዮ ቴሌኮም ሪጅኖች የሚገኙ የምዝገባ ማዕከላት

ተቁ የኢትዮ ቴሌኮም መዋቅራዊ ሪጅን የአገልግሎት ማዕከላት የሚገኙበት አካባቢ
1 ማዕከላዊ ምስራቅ ሐረማያ
2 ማዕከላዊ ምስራቅ ሐረር አራተኛ
3 ማዕከላዊ ምስራቅ ሐረር -2
4 ማዕከላዊ ምዕራብ አምቦ 2
5 ማዕከላዊ ምዕራብ ሆለታ
6 ማዕከላዊ ምዕራብ አምቦ
7 ማዕከላዊ ምዕራብ ቱሉቦሎ
8 ማዕከላዊ ምዕራብ ወሊሶ
9 ማዕከላዊ ምዕራብ ሰበታ
10 ማዕከላዊ ሰሜን ደብረ ብረሃን
11 ማዕከላዊ ሰሜን ሰንዳፋ
12 ማዕከላዊ ሰሜን ለገጣፎ
13 ማዕከላዊ ሰሜን ፊቼ
14 ምስራቅ ምስራቅ ጎዴ
15 ምስራቅ ምስራቅ ቀብሪዳሃር
16 ምስራቅ ምስራቅ ጅግጅጋ ፕሪሚየም
17 ምስራቅ ዞን ድሬዳዋ ኪዮስክ
18 ምስራቅ ዞን ቱሎ
19 ምስራቅ ዞን ድሬዳዋ ፕሪሚየም
20 ምዕራብ ባኮ
21 ምዕራብ ደምቢ ዶሎ
22 ምዕራብ ጊምቢ
23 ምዕራብ ነጆ
24 ምዕራብ ነቀምት
25 ምዕራብ ነቀምት2
26 ምዕራብ ሻምቡ
27 ምዕራብ ምዕራብ ባምባስ ኪዮስክ
28 ምዕራብ ምዕራብ አሶሳ ፕሪሚየም
29 ሰሜን አዲግራት
30 ሰሜን መቀሌ
31 ሰሜን አድዋ
32 ሰሜን አክሱም
33 ሰሜን እንደስላሴ
34 ሰሜን ማይጨው
35 ሰሜን መቀሌ 1
36 ሰሜን ኩይሃ (መቀሌ)
37 ሰሜን መቀሌ 2
38 ሰሜን ምስራቅ አኬስታ
39 ሰሜን ምስራቅ ባቲ
40 ሰሜን ምስራቅ ደሴ 2
41 ሰሜን ምስራቅ ደሴ ሰኞ ገበያ
42 ሰሜን ምስራቅ ሃይቅ
43 ሰሜን ምስራቅ ከሚሴ
44 ሰሜን ምስራቅ ቆቦ
45 ሰሜን ምስራቅ ደሴ
46 ሰሜን ምስራቅ ላሊበላ
47 ሰሜን ምስራቅ ወልድያ
48 ሰሜን ምስራቅ ኮምቦልቻ
49 ሰሜን ምስራቅ ምስራቅ አዋሽ 7
50 ሰሜን ምስራቅ ምስራቅ ሎጊያ
51 ሰሜን ምስራቅ ምስራቅ ሰመራ
52 ሰሜን ምዕራብ አባይ ማዶ
53 ሰሜን ምዕራብ ባህር ዳር 3
54 ሰሜን ምዕራብ ቢቸና
55 ሰሜን ምዕራብ ቻግኒ
56 ሰሜን ምዕራብ ዳንግላ
57 ሰሜን ምዕራብ ደብረ ማርቆስ 1
58 ሰሜን ምዕራብ ፍኖተ ሰላም 1
59 ሰሜን ምዕራብ ኮሶበር
60 ሰሜን ምዕራብ ሞጣ
61 ሰሜን ምዕራብ ባህር ዳር 1
62 ሰሜን ሰሜን ምዕራብ ጭልጋ
63 ሰሜን ሰሜን ምዕራብ ደባርቅ
64 ሰሜን ሰሜን ምዕራብ ደብረ ታቦር
65 ሰሜን ሰሜን ምዕራብ አዘዞ
66 ሰሜን ሰሜን ምዕራብ ንፋስ መዉጫ
67 ሰሜን ሰሜን ምዕራብ ጎንደር 1
68 ሰሜን አዲስ አበባ ፈረንሣይ
69 ሰሜን አዲስ አበባ 6 ኪሎ
70 ሰሜን አዲስ አበባ ኮተቤ
71 ሰሜን አዲስ አበባ መገናኛ/የካ
72 ሰሜን አዲስ አበባ ጉርድሾላ
73 ሰሜን አዲስ አበባ ሽሮ ሜዳ
74 ደቡብ አዶላ
75 ደቡብ አርሲ ነጌሌ
76 ደቡብ ቤንሳ
77 ደቡብ ዲላ
78 ደቡብ ነገሌ ቦረና
79 ደቡብ ሻኪሶ
80 ደቡብ ያቤሎ
81 ደቡብ ይርጋጨፌ
82 ደቡብ ይርጋለም
83 ደቡብ ሀዋሳ ግራንድ
84 ደቡብ ሀዋሳ ፕሪሚየም
85 ደቡብ ሻሸመኔ ግራንድ
86 ደቡብ ምስራቅ አዳማ 4
87 ደቡብ ምስራቅ አሰላ
88 ደቡብ ምስራቅ ባሌ ሮቤ
89 ደቡብ ምስራቅ ባቱ
90 ደቡብ ምስራቅ መቂ
91 ደቡብ ምስራቅ መተሐራ
92 ደቡብ ምስራቅ ሞጆ
93 ደቡብ ምስራቅ አዳማ 2
94 ደቡብ ምስራቅ ቢሾፍቱ 1
95 ደቡብ ምዕራብ በደሌ
96 ደቡብ ምዕራብ ጅማ ፕሪሚየም
97 ደቡብ ምዕራብ ጅማ 2
98 ደቡብ ምዕራብ መቱ
99 ደቡብ ምዕራብ ቦንጋ
100 ደቡብ ምዕራብ ሚዛን
101 ደቡብ ምዕራብ ምዕራብ ባሮ ሜዳ
102 ደቡብ ምዕራብ ምዕራብ ጋምቤላ ፕሪሚየም
103 ደቡብ ምዕራብ ምዕራብ ኒውላንድ ኪዮስክ
104 ደቡብ ደቡብ ምዕራብ አርባምንጭ 1
105 ደቡብ ደቡብ ምዕራብ አርባምንጭ 2
106 ደቡብ ደቡብ ምዕራብ አረካ
107 ደቡብ ደቡብ ምዕራብ ቡታጅራ
108 ደቡብ ደቡብ ምዕራብ ዱራሜ
109 ደቡብ ደቡብ ምዕራብ ጂንካ
110 ደቡብ ደቡብ ምዕራብ ሆሣዕና 1
111 ደቡብ ደቡብ ምዕራብ ወሎያ ፕሪሚየም
112 ደቡብ ደቡብ ምዕራብ ወልቂጤ

በአዲስ አበባ እና አዋሳኝ አካባቢዎች የሚገኙ የምዝገባ ማዕከላት

ተ.ቁ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል
1 ባምቢስ
2 ጌጃ ሰፈር
3 ካዛንቺስ
4 ልደታ
5 መስቀል ፍላወር
6 ስታዲየም
7 ተክለኃይማኖት
8 ቴሌ ጋራጅ
9 ውሃ ልማት
10 አያት አደባባይ
11 አያት ሲኤምሲ
12 ቦሌ መድሃኒያለም
13 ቦሌ ሚካኤል
14 ቦሌ ኖቪስ
15 ፊጋ
16 ገርጂ
17 ሀያ ሁለት
18 ሰሚት 72
19 6 ኪሎ
20 ፈረንሳይ
21 ጉርድሾላ
22 ኮተቤ
23 መገናኛ/የካ
24 ሽሮ ሜዳ
25 አቃቂ 2
26 ቃሊቲ
27 ንፋስ ስልክ
28 ሳሪስ
29 አቃቂ1
30 አልማዚዬ ሜዳ
31 ገላን
32 ቂርቆስ
33 ንፋስ ስልክ
34 ሳሪስ
35 አለምገና
36 አየር ጤና
37 ቤተል
38 ጀሞ
39 ጀሞ 1
40 ለቡ
41 መካኒሳ
42 ጦርሃይሎች
43 ቀለቴ
44 ቲፒዮ
45 አዲሱ ገበያ
46 አድዋ መታሰቢያ
47 አራዳ
48 አሸዋ ሜዳ
49 አስኮ
50 አውቶቢስ ተራ
51 ቡራዩ
52 እንቁላል ፋብሪካ
53 ቀጨኔ
54 ኮልፌ
55 መርካቶ 02
56 መርካቶ
57 መሳለሚያ
58 ሸጎሌ

በኢትዮ ቴሌኮም ሪጅኖች የሚገኙ ጊዜያዊ የምዝገባ ማዕከላት

ተ.ቁ ሪጅን የምዝገባ ማዕከል
1 ማዕከላዊ ምስራቅ ሐሮማያ ዩኒቨርስቲ
2 ማዕከላዊ ምስራቅ የሐረር ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት
3 ማዕከላዊ ምስራቅ ሰዎች ለሰዎች ዩኒቨርስቲ
4 ማዕከላዊ ምስራቅ ምስራቅ ሐረርጌ ገቢዎች ቢሮ
5 ማዕከላዊ ሰሜን አረርቲ
6 ማዕከላዊ ሰሜን ጠባሴ ክፍለ ከተማ
7 ማዕከላዊ ሰሜን ሱሉልታ
8 ማዕከላዊ ሰሜን ጫጫ ክፍለ ከተማ
9 ማዕከላዊ ሰሜን ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ
10 ማዕከላዊ ሰሜን ደብረ ብርሃን ኢንደስትሪ ፓርክ
11 ማዕከላዊ ሰሜን ለገጣፎ
12 ማዕከላዊ ሰሜን ደብረ ብርሃን መምህራን ኮሌጅ
13 ማዕከላዊ ምዕራብ አምቦ ዩኒቨርስቲ ጉደር ካምፓስ
14 ማዕከላዊ ምዕራብ አምቦ አውቶበስ ተራ
15 ማዕከላዊ ምዕራብ አምቦ ዩኒቨርስቲ ሃጫሉ ሁንዴሳ ካምፓስ
16 ማዕከላዊ ምዕራብ አምቦ ዩኒቨርስቲ ዋና ካምፓስ
17 ምስራቅ ምስራቅ ጂጂጋ ዩኒቨርስቲ
18 ምስራቅ ምስራቅ ጂጂጋ ሪፈራል ሆስፒታል
19 ምስራቅ ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ
20 ሰሜን ምስራቅ ምስራቅ ሰመራ ዩኒቨርስቲ
21 ሰሜን ምስራቅ ምስራቅ ኮምቦልቻ ጨርቃጨርቅ
22 ሰሜን ምስራቅ ምስራቅ ወሎ ዩኒቨርስቲ ደሴ ካምፓስ
23 ሰሜን ምስራቅ ምስራቅ ደሴ መምህራን ኮሌጅ
24 ሰሜን ምስራቅ ምስራቅ ደሴ ፔፕሲ
25 ሰሜን ምስራቅ ምስራቅ ደሴ ሪፈራል ሆስፒታል
26 ሰሜን ምስራቅ ምስራቅ ወሎ ዩኒቨርስቲ ኮምቦቻ ካምፓስ
27 ሰሜን ምስራቅ ምስራቅ ኮምቦልቻ ኢንደስትሪያል ፓርክ
28 ሰሜን ሰሜን ምዕራብ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፒያሳ
29 ሰሜን ሰሜን ምዕራብ ጎንደር ሆስፒታል
30 ሰሜን መቀሌ ኒቨርሲቲ አዲ ሃቂ ካምፓስ
31 ሰሜን መቀሌ ኒቨርሲቲ አሪድ ካምፓስ
32 ሰሜን መቀሌ ከተማ የትራንስፖርት ቢሮ
33 ሰሜን ዶ/ር ተወልደ ጤና ኮሌጅ
34 ሰሜን ምዕራብ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ፖሊ
35 ደቡብ ምስራቅ አፄ ገላውዲዮስ ከፍተኛ እና ቴክኒክና ሞያ ት/ቤት
36 ደቡብ ምስራቅ አዳማ ኢንዱስትሪየል ፓርክ
37 ደቡብ ምስራቅ ሪፍት ቫሌ ዩኒቨርሲቲ
38 ደቡብ ምስራቅ አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
39 ደቡብ ምስራቅ ናዝሬት ልብስና ጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ
40 ደቡብ ምስራቅ ሐራምቤ ዩኒቨርሲቲ
41 ደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ
42 ደቡብ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋና ካምፓስ
43 ደቡብ ሀዋሳ መምህራን ማስልጠኛ ኮሌጅ
44 ደቡብ ሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል
45 ደቡብ ሀዋሳ መምህራን ማስልጠኛ ኮሌጅ
46 ደቡብ ሀዋሳ ካምፓስ ግብርና ኮሌጅ
47 ደቡብ ሀዋሳ ነርስ ማሰልጠኛ
48 ደቡብ ደቡብ ምዕራብ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
49 ደቡብ ደቡብ ምዕራብ ወለይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ
50 ደቡብ ደቡብ ምዕራብ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ
51 ደቡብ ምዕራብ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ካምፓስ
52 ደቡብ ምዕራብ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ዋና ካምፓስ/የተማሪዎች መመገቢያ አካባቢ
53 ደቡብ ምዕራብ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ኮሌጅ
54 ደቡብ ምዕራብ ጅማ ማዘጋጃ
55 ደቡብ ምዕራብ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ዋና ካምፓስ/የተማሪዎች መመገቢያ አካባቢ
56 ደቡብ ምዕራብ ጅማ ሪፈራል ሆስፒታል
57 ደቡብ ምዕራብ ጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ
58 ደቡብ ምዕራብ ምዕራብ ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ
59 ደቡብ ምዕራብ ምዕራብ የጋምቤላ ክልል አስተዳደር
60 ምዕራብ አዋሽ ለካ ቅርጫፍ
61 ምዕራብ ምዕራብ ወለጋ ዞን ማረሚያ
62 ምዕራብ ነቀምት ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
63 ምዕራብ ንግድ ባንክ ነቀምቴ ዲስትሪክት
64 ምዕራብ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ-3
65 ምዕራብ አዋሽ ለካ ቅርጫፍ
66 ምዕራብ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ-1
67 ምዕራብ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ-2
68 ምዕራብ ነቀምቴ ከተማ አስተዳደር-2
69 ምዕራብ ምዕራብ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ
70 ምዕራብ ምዕራብ የክልሉ ኪራይ ህንፃ ላይ

በአዲስ አበባ እና አዋሳኝ አካባቢዎች የሚገኙ ጊዜያዊ የምዝገባ ማዕከላት

ተ.ቁ

የምዝገባ ማዕከል
1 ልደታ ክ/ከ ወረዳ 7
2 ልደታ ክ/ከ ወረዳ 3
3 ልደታ ክ/ከ ወረዳ 1
4 ቦሌ ክ/ከ ወረዳ 5
5 ቦሌ ክ/ከ
6 ጉለሌ ክ/ከ ወረዳ 2
7 የካ ክ/ከ ወረዳ 04
8 የካ ክ/ከ
9 አራዳ ክ/ከ
10 አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ
11 ሙለጌ ሕንጻ
12 ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ
13 ቄራ
14 አዲስ ኢንደስትሪ ቪሌጅ (ካዲስኮ)
15 ግሎባል ሆቴል
16 ኮልፌ ወረዳ 9
17 ንፋፋ ስልክ ላፈቶ ወረዳ 2
18 አለምገና
19 ጉለሌ ክፍለ ከተማ
20 አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3
21 ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9
22 አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13
23 ፊሊ ዶሮ ወረዳ ጽ/ቤት
24 ቡራዩ ከተማ አስተዳደር
25 አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ
26 ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10
27 ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05