የምትተክል ሀገር፤ የሚያፀና ትውልድ በሚል መሪ ቃል በሃገር አቀፍ ደረጃ፣ በኩባንያችን ደረጃ ደግሞ ለ6ኛው ዙር ለአረንጓዴ ኢትዮጵያ በሚል መሪ ቃል በአካባቢ የተፈጥሮ ጥበቃ እና ዘላቂ ልማት ላይ የራሱን አሻራ ለማሳረፍ የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት ሲያደርግ የቆየ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለት በመላው የሃገራችን ክፍሎች በሚገኙ የኩባንያው ጽ/ቤቶች የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብሮችን በይፋ አስጀምሯል፡፡

በ6ኛው ዙር አገር አቀፍ አረንጓዴ አሻራን የማሳረፍ ዘመቻ መርሃ ግብር ወደ 500 ሺህ የሚደርሱ ችግኞችን በኮርፖሬት፣ በዞን እና ሪጅን ደረጃ ከ5 ሺህ በላይ የኩባንያው ሠራተኞችን በማሳተፍ በአዲስ አበባ በከተማ መስተዳድር ውበት እና አረንጓዴ ልማት ቢሮ በተመረጡ በአራት የተከላ ጣቢያዎች እንዲሁም በኩባንያው የሪጅን ጽ/ቤቶች ደረጃ ደግሞ ሪጅኖቹ ከሚገኙባቸው የከተማ መስተዳድሮች ጋር በመቀናጀት በተመረጡ የተለያዩ የችግኝ መትከያ ቦታዎች ተገቢውን ዝግጅት በማድረግ የችግኝ ተከላ መርሃ ገብሩን አከናውኗል።

በዚህም መሰረት ኩባንያችን በኮርፖሬት እና ዞን ደረጃ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 15 ጋርመንት አደባባይ ሃጫሉ መንገድ እና ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ሳሚት ኮንዶምኒየም አካባቢ እንዲሁም በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ሳለሁ ጎራ አካባቢ እና በወረዳ 2 ዩኒሳ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ በተዘጋጁ ቦታዎች የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ያከናወነ ሲሆን፣ የኩባንያው 17 ሪጅኖች ደግሞ በከተማ መስተዳድሮች በተረከቧቸው ቦታዎች ላይ የችግኝ ተከላ ዘመቻ አካሂዷል፡፡

ኩባንያችን በዚህ በስድስተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከሐምሌ 11 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ከ500 ሺህ በላይ ችግኞችን በመላው ኢትዮጵያ ለመትከል ከ51.5 ሚሊዮን ብር በላይ ለችግኝ ተከላ እና እንክብካቤ ወጪ የሚያደርግ ይሆናል፡፡

ባለፉት አምስት ዓመታት በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ 700 አካባቢዎች ከ3.8 ሚሊዮን በላይ የጥላ፣ የፍራፍሬ እና የውበትና ቅመማቅመም ችግኞች በመትከል አረንጓዴ አሻራውን ያኖረው ኩባንያችን፣ በአማካይ ከ82 በመቶ በላይ ችግኞችን በማፅደቅ የተራቆቱ አካባቢዎችን በልምላሜ በመቀየር ለዘላቂ ልማት የበኩሉን ጥረት ከማድረጉም በላይ ከ20ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ጊዜያዊ የስራ ዕድል መፍጠር ችሏል፡፡

ኩባንያችን ከኮኔክቲቪቲ አገልግሎት ባሻገር ዓለም የደረሰበትን የዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማህበረሰባችን በማቅረብ እንዲሁም በዲጂታል ፋይናንስ ዘርፍ የዜጎችን የፋይናንስ አካታችነት ለማረጋግጥ ጉልህ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ከዚሁ ጎን ለጎን የማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣትም ከለያቸው የፖሊሲ ዋና ዋና አምዶች (Pillars) መካከል አንዱ ለአካባቢ ጥበቃ እና ዘላቂ ልማት ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደመሆኑ መጠን ለአረንጓዴ አሻራ እና የኢኮ ቱሩዝም ፕሮግራሞች ላይ በንቃት በመሳተፍ ዘመን ተሻጋሪ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል::

ሃገራችንን ለ130 ዓመታት በቁርጠኝነት በማገልገል ላይ የሚገኘው ኩባንያችን፣ ሁሉን አቀፍ የሀገራችንን እድገት ለመደገፍና ተወዳዳሪነትን ለመጨመር የአስቻይነት ሚናውን ለመጫወት በየጊዜው አዳዲስ አገልግሎቶችን እና ቴክኖሎጂዎችን ከማቅረብ ባሻገር ለማህበረሰባችን እና ለሃገራችን ፋይዳ ያላቸው ልዩ ልዩ ፕሮግራሞችን በመቅረጽ፣ ሃገራዊና ማህበራዊ ድርብ ኃላፊነቱን መወጣት አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

 

ሐምሌ 11 ቀን 2016 ዓ.ም

ኢትዮ ቴሌኮም

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives